አይዋ ምንትሶ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።
አይዋ ምንትሶ።
„በክፉዎች ምክር ያልሄደ በሃጢያተኞች መንገድ ያልቆመ
እሱ የተመሰገነ ነው። በእግዚአብሄር ህግ ደስ ይለዋል።“
መዝሙረ ዳዊት ፩

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 18.02.2019
                                    ይህ ለከብት ህልውና ብቻ ነው።

እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ከዚህም ከዚያም፤ ከዚያም ከዚህም፤ እንዲህ ወደ ማዶ፤ እንዲያ ወደዛም ወደ ፈረፈሩ ... ቅይጥ ቅብጥር ምንትነት ይደመጣል። ምኑ ተጨውቶ? በዚህም በዛም ቢመጣ። በዚህም በዛም ቢባዛም ጽናት በሌለው ዓላማ ዘመን ሰጥ ገጠመኞችን ዳክሮ ማዳከር አይዋ ምንትሶ ዛሬም እንደትናቱ እያስተናገደ ነው።

በየሉም የሌሉዮሽ አዲስ ጠናና ቅብጥርሶ፤ ብልዝ ብርዳብርድ ባለው ሞድ ባልተሰራለት ትናጋ ቢሉት ያም መብት ነው። ይቻላል እንደማለት። መብት ሲሆን ታዲያ በዬለም በተከዘነው አምክንዮ ውስጥ እንደ ቀደመው በማባጨል መሆን አይገባውም ነው ቁምነገር።

ቅድሚያ አንድ ሁሉት ነገር ይዞ ብቅ ከማለት እራስ በዛ አመክንዮ ውስጥ ስለመኖሩ ፈተሽ ማድረጉ የተገባ ነው። ታዛቢዎች ስላለን። ያው የምንትሶ ነገር ሲረታ ደግሞ በምናምንቴው እሰኪጋፍን ድረስ … አይዋ ምንትሶ አዚማም ነው። መቀመም ያውቅበታል። ቀምሞ ድብን ያደርጋል። የዋዛ ለሴራ ማን ብሎት ተፈጥሮበት የለም።
   
ለነገሩ አድጦ አድጦ አንደላልጦ አንደላልጦ አሁን መለመላ ሲቀር ያው በፈረደበት ፍርደኛ ወደ አይዋ የኔታ የዋህዮት ተዝካሬን አውጣልኝ በሏል። ሲፍከረክ እንደለመደበት ማጣፊያው ሲያጥረው ጥግ ሁነኝ የሙጥኝ መባል የተለመደ ነው። 

አይዋ ምንትሶ ትናንትም ምንትሶ ዛሬም ምንትሶ ነገም ምንትሶ ነው። መስፈሪያ ቁና ወይንም ክናድ አልተበጀለትም። ማተብ ብሎም አልተሠራለትም። ወደፊትም አይሰራለትም። ሙልጭ ነው ሙልጭልጭ የጥላዬ የላንቅሶ ትልም።

ብቻ ያቺ አራት እግር ግዢ ትድራ። ያቺን ጠረኗን የሚያስገኝ ግብጦ ከተገኘ እንዲያ ነው የምንትሶ ነገር። ዳርዳር ብቻ ሆና ቀረች እንጂ። እዬራቀች እዬራቀች ሄደች እንጂ። … የሚገፋ ከተገኜ ሰካ ነው። ለዚህም አንጋጦ እግዜሩን እዬለመነ ነው። ትናጋው ጋጥ እስኪል ጦም ጠሎቱን ያስከነዳዋል። እባክህ አንድ ማት ፍጠርና ይህን የሉላዊውን ሚዲያ ያሰከነዳውን ቢና ጢና አውጥተህ እኔን እንደተመኘሁት ቁብ ... 

ታዲያ ጦም ጠሎት የሱ ሸር ነው። ሽርብ ሸር በሽርዳዳ። ያች ቀን እስኪገኝ ድረስ ተገፊውን በውስጥ መንጥርልኝን ተንትርሶ ጠጋጠጋ ግን አይቀሬ ነው። ጮሌው ጭልፊት ነው። ከልብ ገብቶ ቅጥ ቅብጥ ያሰኛል። ተሁን ተሁን ሲደመጥ በ አንድ ነፍስ መተንፈሰም ተሁኗል ትላላች ወፍዬ። ብቻ ነገረ ሥራው ይገርማል። ልብጥ ተፈጥሮ ይኼው ነውና።  ገጥ በግልብጥ የተከነዳ ነው። ወይንም በስተማጅራት።
  
ምንትሶ ድንብልብል ነው። በተጨማሪነት ልሙጥ ነገር። ልሙጥ X ድንብልብል=  ድንብልብል በልሙጥ ሲባዛ ደግሞ ልሙጥበድንቡልቡል ይሆናል ማለት ነው። ዘመን የሳተው አይዋ ምንትሶ በተለመደው ዝብርቅ ቅኝት እያመለጠ በሄደ ዕድል መገለባበጥ አዲስ የመሰናክል ሩጫ መጀመር የተለመደ ነው። መሰናክሉ ግን ያው ለሎሌነት ራሱን ዝቅ አድርጎ አደግድጎ ለተሰናዳው ለዬኔታ የዋህዮት  ይሆናል። መጥኔ ለእሱ።

ተሸከሙኝ፤ እዘሉኝ፤ አሽኮኮ አድርጎኝ የማይሰለቸው ልሙጥድንብልብልም ዘመን ካልሸኘው በሰተቀር ዘመን ታከትከኝ ብሎ ካላሰናበተው በስተቀር ሁልጊዜም ጥገት ሁኑኝ ነው። አይጠግብም ስላችሁ። እሱ ዘመን ይዞ ተዘመን ወድቆ በተፈጠ ቁጥር ተነኝፎ መጠበቅ። ምን ይባል    ?

በወደቀ ቁጥር ምርኩዝ ሁንኝ ከማለትም ቦዝኖ አያውቅም። ለዛውም አንጡራ ጠላቴ ብሎ በልሳኑ ለሉላዊው ዓለም ዝበትን በፈጠረበት በራሱ ኩሸት ውስጥ አድብቶ ያነን ጨርቅም ማቅም አድርጎ መኮፈስ። አቤት እንዴት እንደሚጠዬፈው የኔታ የዋህዮትን። ግን የጠሉት ይወርሳል ሆኖ መንጠላጠያ ብጣቂ ራፊ ጠፋ እና አሁንም ተዛው ተለጥፏል። ዓይኑን በጥሬጨው ያሸ ጉደኛ ... ለነገሩ ንግድ ህህህህህህ ... 

በዚህ እውነት ውስጥ መቼውንም ቢሆን እርቀሰላም የለም። እርቃኑን በቀረ ውስጥ ውስጥነት በቅሎ አያውቅምና። ብቻ በበዛው በሹልከቱ ልክ ቀዳዳ ወታፊም፤ ጣፊም አንጣፊም ጎዝጓዥም አያጣም። ለዚህስ ዕድለኛ ነው ዕድሜ ለየዋህዮት የኔታ።

ዘመን ተዘመን በዝላይ ብቻ ዘላዝሎ መኮፈስ ነው የአይዋ ምንትሶ ነገር። በመኮፈሱ ውስጥ ደግሞ ያው በተገኘው ቦታ ንደቱንም ክህደቱም አይቀሬ ነው። ስለምን? ፍጥረተ ነገሩ ሙልጭልጭ ስለሆነ። በተጠጋው ልክ ፍርሰት፤ በተጠጋው ልክ ንደት። በተጠጋው ልክ የማይሸከሙት ውርዴት ነው። 

ግን ውርዴት እና ሽንፈት ክብር እና ልዕልና ሆነው በምት ሽብቦ ተሸብሽቦም አለበት። አያልቀበትም እና በሉልኝ „ጉሮ ወሸባዬ¡“ ደግሞ አይቀሬ? አቤት?!

ፊታውራሪ „ጉሮ ወሸባዬ“ ምን ሲቸግረው ያሻው ቢያንጠለጥለው፤ ያሻው ቢያሽቀብጥለት ያሻው መሰንቆ ደቅኖ ቢያስደነክርለት ብቻ ያሟሙቅለት ለዛ ዕለታዊነት ለደራበት የገብያ ውሎ። ብቻ ያሸብሽለት ለዛ የሰሞናት የሳሙና አረፋት ውሎ። 

ውልማ ተውሎም አያታውቅም። በኪዳን መገኘትም ለአይዋ ምንትሶ አልተፈጠረለትም። ሲሾልክም ሲያሾልክም፤ ሲፈርጥም ሲነኩትም ያም ክብር ነው የሚያስጨበጭብ „ጀግና¡“ አሰኝቶ የሚያስደነክር … አርቲ የሚያስጨስ …

በሞቀቤት ዱቅስ? ማን ቀድሞት? የሞቀን ቤት ተርትሮ መበተነስ? አያዋ ምንተሶ ለዚህም የወጣለት ሻንፕዮን ነው። ይህ መቼም ብልህነት ብስለት ማስተዋል ተብሎ ለጀማሪ ፊደለኛ ሊሆን ይችላል።  ለእድሜ ጠገብ ፖለቲካ ግን ፉርሽካ ነው … ግርድፍ። ከሞቀ ለመጠጋት ከሁለት ከሦስት ተርትሮ ሌላውን በትኖ በዛ ውስጥ ራስን ማስኮፍ? ሃጢያት - አይደለምን?  

መሽቶ እስኪነጋ ይኸው ነው የምንትሶ ነገር። መለል። መለል። መለል። መሰሰል፤ መሰሰል። መለል መለል። ፍጥረት ልል። ካለሞግዚት አንዲት ስንዝር አይችላትም።
በመለል ውስጥ ያለው አንድ ነገር ነው ፊጥ ማለት። ቁሞም ተቀምጦም፤ ተኝቶ ተነስቶም የሚያብትተው፤ የሚያባንነው ፊጥነት ነው። በቁሮም ይሁን በጥፎ። ልጥ ሲላጥ መገላበጥ ነው። ግልብጥብጥ። ይልቅ ፊፋ የግልብጥብጥ አንድ የሥፖርት አርት ቢፈጥር ምን ነበር? ዋንጨው ያው ለአይዋ ምንትሶ ይሆን በነበረ። ተዓለም ሁሉ አሸናፊ በሆነ ነበር። ሪከርድ በጣሽ። ለውሸተም አይኑን በጥሬጨው ያሸ ነው። 

ጁባ ላይ ይሆን እጀ ጠባብ ላይ ብቻ ተሆነ ቦታ ላይ ፊጥነት ራዕዩ ነው። ኮረቻው ደግሞ ያ የተለመደው አይዋ ዝክር  የዋህዮት የኔታው ነው። እዬተጠዬፈው ነው የሚጠጋው፤ ግን ተሱ ሌላ አማራጭ ጠፋ። የበታችነቱ እዬነሰተው፤ የበታችነቱ በውጋት ሰቅዞ ቢያጣድፈውም እያቃሰት እዛው ሄዶ ልጥፍ ግድ ሆኖ ተገኜ። የኔታ የዋህዮት ደግሞ አንዲት ምናምንቴ የትናጋ ኩሸት ጠብ ባለችለት ቁጥር ያቺን አንጠልጥሎ ማርገድ ነው።

ለነገሩ ተመስገን ነው ተዛሬ ላይ። እሱም እንደሌላው ተኩል ለይ መገኘቱ። ዝቅታ ላይ ተገኝቶ ልመና ላይ መገኘቱም አንዱ የፈጣሪ ታምር ነው። ለዚህ ይመስገን እግዜሩም።

ውሸት በረከተ እዬተተረከ!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ውሎ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።