ዕውነት ላይ ያለመቆም ችግር የትውልድ ብክነት ፋፍሪካ።

እንኳን ደህና መጡልኝ
„ከአፌ ቃል ፈቀቅ አትበል፤ አትዋትት፤ ትደግፍህምአለች።
ውደዳት ትጠቅምህምአለች። ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና
 ጥበብን አግኝ። ከሃብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ከ፭ እስከ ፯

ዕውነት ላይ ያለመቆም ችግር
የትውልድ ብክነት ፋፍሪካ።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ፏ ብላለች ልዕልት ጠሐይ። አላዛሯ ኢትዮጵያስ?

በዘመናት መካከል የጠፋው፤ የከሰለው፤ የባከነው ትውልድ የሊሂቃኑ ዕውነት ላይ ያለመቆም ችግር ነው ብዬ አምናለሁኝ። አብሶ ከራስ ተሰማ ናዳው የሴራ ፖለቲካ ማግስት ይህን መሰሉን ሴራ ውርስ ቅርስ በማድረግ ፖለቲከኞች ሲጠቀሙበት ትውልድ በጎራ ተለያይቶ የሳት ራት ሆኗል። ታጭዷል። ፈልሷል። ተጎርዷልም። አሁንም ዘልቋል መከታከቱ። ስለምን? ሴራ የዲያብሎስ ስለሆነ ከፈጣሪ አምላኩም ጋር ስለተለያዬ መንፈሱ። ፈጣሪ እፍ ብሎ መርቆ ከፈጠራቸው ጥባበት ጋርም ተፋልሷል የሊሂቃኑ ምህንድስና ። ማህከነ!

ትውልድን በማበርከት የስካንድንብያ አገሮች እና ሲዊዘርላንድ የኢትዮጵያን ያህል የቀደመ የሊቃናት ሰማይ እና ምድርን የመረዳት ጥበብ ቢኖራቸው ከአሁኑ የበለጠ ሰውኛ ያልሆነ መንፈስኛ የሆነ ምጥቀት በተገኘባቸው ነበር። 

ለእነሱ ስክነቱን ሲሰጥ ጥበብ ደግሞ ለኢትዮጵያ ተስጥቶ ባልተገናኝቶ እኟ አረንቋ ላይ እንገኛለን። እነሱ የሰላምም የስክነትም የስልጣኔ ባለቤት ናቸው ዛሬ። እኛ ደግሞ ካለንበት ከነበርንበት ወርድን ከእንሰሳትም ዝቅ ብለን ፈጥሮን እና የሰው አፈጣጥርን ስንታገል እንገኛለን። ውሻ እንኳን ከለመደ በሆዋላ ለለደመደው የሰው ልጅ ጥበቃ እና ታማኝ ይሆናል። የእኛው ግን ከዚህም በታች የወረደ ነው። ተሳህለነ!

ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙአቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019

አቶ ለማ መገርሳ አንድ ሚሊዮን ኦሮሞዎችን አዲስ አበባ ለማስፈር ሲባል ሆን 
ብለው ከሶማሌ ክልል ራሳቸው እንዳፈናቀሏቸው ተናገሩ

ኢትዮጵያ በቀደመው ዘመን የነበራት የጥበብ ልቅና ብርታት እና ጥንካሬ ከእጬጌው ግዕዝ ጋር በእጅጉ የተቆራኜ ነበር። ይህን ተጻሮ የወጣው መንፈስ ደግሞ የሰማይ በረከቱን አሽቀንጥሮ በመጣል የትውልድ ብርንዶ ቅርጫ ቤት ከፍቶ ካለ አንዳች እውነት ለአንተ ስል፤ ለአንቺ ስል በማለት የሥም ንግሥና ኢጎ ላይ ተቆልሎ ከአባት ከቅድመ አያቶቹ ትውፊት ውጥቶ እንሆ ዛሬም ይተራመሳል። አሁንም ትውልዱ በማያበራ የመንፈስ የጦርነት ውቅያኖስ ውስጥ ጉግስ ላይ ይገኛል። እግዚኦ!

እናቴ እዚህ ሲዊዝርላንድ መጥታ በመነበረችበት ጊዜ ሥጋ እንድትበላ ስጠይቃት "አልበላም ያልተባረከ ነው" አለችኝ። ያን ጊዜ ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ በህይወት ነበሩ እና ሥጋ ሲበሉ አይቼ ስለነበር እሳቸው እኮ ሥጋ ውጥ በእንጀራ ሲበሉ አጠገባቸው ሆኜ አይቻቸውላሁን ውጭ አገር አልኳት። በነገራችን ላይ እሳቸውንም በአካል አውቃቸዋለሁኝ። ቃለ ምልልስም አድርጌላቸው ነበር።

ወደ ቀደመው ስንመለስ እናቴ ያለችኝ "ፈጣሪ ስለሳቸው ሳይሆን ስለራሴ ነው የሚጠይቀኝ። በሌላ በኩል አይደለም እንሰሳው ምድሪቱ እጽዋቱ በሙሉ የተባረከ ነው ኢትዮጵያ። በረከቱን የጠጣ አዝእርት እና እጽዋት እና እንስንሰሳት ነው ኢትዮጵያ ያላት ከዚህ ግን እንደዛ አይደለም። ከብቶች፤ በጎች፤ ፍዬሎች የሚበሉት እሳር ሳይቀር የተጸለዬበት ነው ኢትዮጵያ ። አፍሩ የተጸለዬበት ነው። ዘር ገበሬ ሲዘራ ጸልዮ ነው። ወንዞች ተባርከው ነው። ሳይብራክ ውሎ የማያድር አንዳችም ነገር የለም፤ መደበኛ ሥራ ነው ይህ በእኛ ምድር አለችኝ።" ተመስገን!

እውነትም ነው። ቅዱሳን፤ ብጹዕን፤ ደናግላን እናት እና አባቶቻችን ለሁሉ ለፍጥረታት ሁሉ ነው የሚጸልዩት። በረከቱ ደግሞ ዳር ደንበር የለውም። ይህን ትውፊት በጥልቅት ስመረምረው እሷ በቀደመው ትውፊት ውስጥ ስለመሆኗ እና አገር ብትለቅም ከዛ ትውፊት ላለመውጣት መቁረጧን፤ መወሰኗን አቋሟ ጥርት ያለ ስለመሆኑ ተርድቻለሁኝ። 

እውነት ባለችው ነገር ጽናቷን የሥጋ ፈቃድ አላታላላትም። በቃል ውስጥ ያለውን ሃይል ከልቧ ሆና መርመራለች። ቃል ዝም ብሎ አይፈስም። አንዷ ቃል ለተናጋሪውም ለአድማጩም ህይወት መስጠት ካልቻለ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው መጸሐፈ ሲራክ እንዳለን።፡

የእኛ ችግር ደግሞ ሁሉን ነገር ሸሽተን ነው። መዳኛችን ሸሽተን። መልማታችን ሸሽተን። በረከታችን ሸሽተን። ረድኤታችን ሸሽተን። ምርቃታችን ሸሽተን። ነፍሳችን ሸሽተን። ቃላችን ሸሽተን። ዕውነታችን ሸሽተን። ሃቃችን ሸሽተን፤ መክሊታችን ሸሽተን በሽሽት ውስጥ እዬተረጋጋጠ የቀረው የራሳችን የሆኑ ዕንቁ ነገረ ሚስጢራትን ተረግጠን እንሆ እንደለመደብን አሁንም አንተራመሳለን። ሎቱ ስብሃት!

ከፍ ባለው ሁኔታ ስናስበው ዛሬ በምድራችን ፈጣሪ በአምሳሉ በፈጠረው ፍጡር ላይ እንዲኖር በተደነገገለት መሰረታዊ ምርቃት ላይ ሁሉ እሳት እና ጭድ፤ ቤንዚንና ክብሪት አሰናድተንን ለድንኳኗ ኑሮ ጭካኔን ውጠን፤ አረመኔነትን ተጎናጽፈን፤ ሲኦልነትን ተንፈስን መኖርን እናርሰዋለን።

OMN: ቆይታ ከለገ ጣፎ ለገ ደዲና ከሰበታ ከንቲባዎችና ከከተማ ፕላን ባለሙያዎች ጋር (Feb 24, 2019)


ዕውነት በቃል ውስጥ ጠፍቶ፤ ዕውነት ላይ መቆም ተስኖ መሪውም ተመሪውም አንድ ላይ በተሰበረው መርከብ ውስጥ ሆነው ያው የፈረደበትን ትወልድ መከራ ውስጥ አምሰው ያተራምሱታል።

አቤት ያንት ያለህ የእኛ ጌታ
 የህዝብህ እንባ ሆነ ከርታታ!

በመወገን እና ባለመወገን፤ በመደገፍ እና ባለመደገፍ ማህል ያለው ጥሬ ሃብት መዋለ ሃብት የሰው አቅም ነው። ይህ የሰው አቅም ባልተፈለገ ጉዳይ እሰጣ ገባውን እንዲያደርግ በመደረግ የህዝብ ሥነ - ልቦና በጭንቀት እና በስጋት ጥሪት እንዲፋፋ፤ እንዲለመልም እየተደረገ ነው። መስከረም ላይ የነበረውም ትርምስ ይኸው ነው።

የሁሉም ሊሂቃን መከራ አንድ እና አንድ ነው። የቀደሙት የጥበብ ሊቀ ሊቃናት   የዕድምታ የሚስጢር ማህደር የስሜን ሰው ነው ብለው ያምናሉ። ስለዚህ በዚህ በጠቃሚው ነገር ውስጥ ለመኖር እራሳቸውን ለማሸነፍ አልቻሉም። የተዋረዱ ወይንም የጠፉ ይመስላቸዋል።

ስለምን ብትሉ የበታችንት ስሜት የወለደው መከራ ነው። ያን እዬደለዙ በዛ ዙሪያ አቅም በማስባሰብ ብቻ ሳይሆን፤ የተሰበሰበውን አቅምም በራሳቸው አቲካራ እዬተረተሩ አዳዲስ አጀንዳ እየቀረጹ ትወልድን እንሆ አባካኑት። ብዙው ትርምስ የግጭት ዓውድ እኮ ራሳቸው የሚሠሩት ተውኔት ነው ወጀቡን የሚፈጥረው።

አቶ ታከለ ኡማን ሥልጣን ለመስጠት አዲስ ህግ ታረቃለህ፤ ታጸደቅለህ። ይህን ተቃውሞ የሚወጣውን ደግሞ ሁሉ ተሰጥቶህ ዘውድህ የትሜና ትቤያላይ አስቀምጠህ እንደ ካድሬ ሆነህ ወርደህ ከእዮራዊው ቅባህ ታስፈራራለህ። በዚህ ውስጥ የፈጣሪ ቅብዕ እና ምርቃት ምን ያህል እንደሚጎሳቆል። መጎሳቆል ብቻ አይደለም። አቤትም ይላል ለእዮር ።

ለዚህ እኮ ነው የባለደራስ የጭቁኖች ጉባኤ፤ የቤተመንግሥት የቅንጦተኞች ባለጠበንጃ ጉባኤ፤  እና የቦይንግ 737 ማክስ 8 ጥምረት በአንድ ላይ የተስተናገዱት። ለአንድ አቶ ታከለ ኡማ ሲባል ዓለም በሃዘን ተመታች። ቦይንግም ከማይችለው ማጥ ውስጥ ወደቀ። ወላጅም እንደዛ ባለ አሰቃቂ መከራ ውስጥ ሰመጠ። ለአንድ አቶ ታከለ ኡማ ሲባል ጥገናዊ ለውጡ ከማይችለው ቅርቃር ውስጥ ተዶለ። ገና ያላለቀ መከራ ውስጥ እንሆ እንገኛለን። 

ለአንድ አቶ ታከለ ኡማ ሲባል አዲስ አባባ በደም ታጠበች መስከረም ላይ፤ ወጣቶች ለካቴና ተዳረጉ መስከረም ላይ። ግን እሳቸው ሰው ናቸው ምንድን ናቸው? ስለምን ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው አይለቁም? አገር እኮ ልትፈርስ ጣር ላይ ናት በሳቸው ምክንያት። አቶ ታከለ ቢነሱ ምንድን ነው ኢትዮጵያ የምታጣው? ምንም? ቀድሞ ነገር ምን የተለዬ ጸጋስ አላቸውና። ለሰከንድ መንፈስን የመያዝ አቅም እንኳን የላቸውም። 

አዲስ አባባ እኮ የመንፈስ ሃብት ዲታ ናት። ያ የመንፈስ ዲታነቷ ደግሞ ታምራት አለበትታምራቱ ደግሞ ያልተለበጠ፤ በኢጎ ሸቀጥ ያልረከሰ ማንነት ያለው መንፈስ አንቱ የሆነበት ነው። ስለዚህ ይህ አንቱ መንፈስ የመንፈስ ቅዱሱን በረከት በጥንቃቄ ከያዘው ምን አልባትም ዘላቂ መፍትሄ፤ ቋሚ መፍትሄ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ያስገኝላት ይሆናል። በጭካኔ የናወዘ መንፈስ የቆንስላ፤ የኢንባሲ ቢሮዎችን ስለማይምር ዘግተን እንሄዳለን ቢባል ምን ሊሆን ይሆን  የዶር ለማ መገርሳ ሌጋሲ … ምህንድስና ... 

ኢትዮጵያን ደቡብ ሱዳን ለማድረግ በተጠና እና በታቀደ ምህንድስና እዬተሠራበት ስለሆነ ይህን አፍርጦ የዲፕሎማሲያዊ ተጋድሎ ቢደረገብት ትርፍ ይገኝበታል። ዝም የተባለው ትርፉ በስሜን ኢትዮጵያ ጠል መንፈስ በግርግር እጅ እንዳይወድቅ፤ ሌላ ጣጣ ደግሞ እንዳይመጣ  ይህንም ተሰልቶ ነው እንጂ ጉዞው እኮ ቁልጭ ያለ ነው ጸረ ሰው፤ ጸረ ተፈጥሮ፤ ጸረ ዳይበርስቲ፤ ጸረ መቻቻል፤ ጸረ አብሮነት ነው።

በዚህ ጠማዳ ጉዞ በማስተባበል የሚገኝ የህሊና ትርፍ የለም። የጠ/ሚር አቶ ለማ መገርሳ ምህንድስና አፍሪካንም መከራ የሚያሸክም መሆኑን አሳምረን እናውቃልን። የሥም ጠ/ሚር አብይ አህመድም አውሎ እንደሚንጠው ዛፍ አቅጣጫው ጦዞ የሚታዬው በዚህ መጠራቅቅ ውስጥ ስለሆነ ነው። ዕውነት በተፈራ ቁጥር እራስም እዬተረሳ እንደሚሄድ ልብ አልተባለም። የፈጣሪ ቅብዕ የዳንኪራ መሸታ ቤት አይደለምና።

የኢትዮጵያ ሚስጢርነት የሁሉም ጥሪት ሆኖ ሳለ በሽተኛ አደረጋቸው። ከበሽታው ለመፈወስ ደግሞ የበሽታውን መንስኤ ማወቅ ሲገባ ይልቁንም ያን የነቀዘ ጥላቻ በውስጥ አምቆ እና ጨፈላልቆ ድጦ እና ሰርዞ የእኔ በሚሉት ሰው ሰራሽ መንገድ ለማራመድ መሞከር ነው ዬዘመኑ መከራ ትውልድ እንዲሸከም እዬተደረገ ያለው። አትዮጵያ የተሰደደ ማንንነት የላትም። ኢትዮጵያ ቅኝ የተገዛ ማንንት የላትም። ስለዚህ የትውስት መንገድ አያስፍልጋትም።

አሁን የኦነግ ቅኝቶች መከራቸው ይኸው ነው። መሪዎች እነሱው ስለሆኑ እንጂ አለሁ የሚለው የፖለቲካ ድርጅት ቢሆንም መከራም ከዚህ ዙር ተመለስ አረንቋ የሚወጣ አይደለም። ሁሉም በበታችነት የሚናጥ ነው። ከሌላ ከዬት ይመጣል። ሺህ ዘመናትን መልሶ ማግኘት አይቻልም። አትዮጵያን ያበጇት እጆች መንፈሳቸው ብቻ ነው ያለው። ያ ጥሰት ሲፈጸም ደግሞ ውልቅልቅ አድርጎ መቀጣጫ ያደርጋል። 

 ስለሆነም አሁም ብዙ ሰው ፍኖተ ካርታ ወዘተ የለም ይላል በኦሮማማ በገዳ ሥርአት ነው ሽግግሩ የተወጠነው። ከተቀበልክ ትቀጥላለህ ካልተቀበልክ ደግሞ ትናዳለህ። ጨዋታው ይኸው ነው። ለዚህም ነው ከአባቶቻችን ሌጋሲ እንነሳለን የሚለው መንፈስ የግራ ቀኝ ወጀብ የበዛበት። ተፈሪም የሆነው። ግን የፈጣሪ ጥበቃ ስላለው ፈተናዎችን ሁሉ ጥሶ ይወጣል።

አቅም፤ ክህሎት፤ ችሎታ፤ የምርምር ሰውነት መነሳት ያለበት ከኢትዮጵያዊነት ማንነትን ከሳገኘው የበረከት መሰረት መሆን ይኖርበታል። ያ ካልሆነ ትናንት እንዳዬነው ይህም አይበረክትም። በነገራችን ላይ ወጥ የኢህዲግ ፓርቲ ጥንስስ የሚባለውም በዚኸው ኦሮማማ መሰረተ ሃሰባ የታነጸ ነው። ኦዴፓ አዴፓ ቀጣዩ ኢዴፓ / የኢትዮጵያ ዴሚክራሲያዊ ፓርቲ/ የአፍሪካ ቀንድም በዚኸው ነው ህልሙ … እዚህ ላይ ጠ/ሚር ዶር ለማ መገርሳ ስለመሆናቸው ልብ ማለት ይገባል። ማህንዲሱም እሳቸው ናቸው። ከዶር ገዱ ጋር የነበረው የተከደነው ውስጠትም ይህን ስለያአውቁ እንደነበር ይገባኛል። 
  
ወደ ቀደመው ምልሰት ስናደርግ ከአባቶቻችን መንፈስ መነሳት ጠ/ሚር አብይ አህመድን ምን ያህል ጠቅሞ እንደነበር ዛሬ ሳይሆን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ስኬት በማስተዋል መመርምር ያስፈልጋል። ያን ጊዜ ነፃነት ነበራቸው። ዛሬ ግን እስረኛ ናቸው። አሁንም ያ ቢሮ በዛ በረከት ውስጥ ነው። የዘመን መለወጫ ላይ የነበረውን ሥርዓት ተመልክቻለሁኝ።

በዚህ መልክ ኢትዮጵያን ለመቅረጽ አስበው ተነስተው ነበር ከመጋቢት እስከ ሀምሌ በነበረው ጊዜ። ያ መንፈስ ተቀለበሰ። ስለዚህ ምርቃቱ በሙሉ ተነሳ። የተሰጠን ቅብዕ ለሌላ አሳልፎ ሲሰጥ አቅሙም ትልሙም ተነነ ...  

ያ እንደ ማህሌት ሰውነትን ይፈውስ የነበረው አንደበታቸው ዛሬ ለመስጠጋት እጅግ ከባድ ነው ለመንፈሳዊ ሰው። ይኮሰኩሳል። እሳቸውም እንደቀደመው ልሁን ቢሉ የሚችሉ አይሆንም። ስለምን? ቢባል ከጸጋቸው በመውጣታቸው ምርቃታቸው ስለተነሳ ነው።

ትናንት ዶር ደብረጽዮን ገ/ሚኬኤል አትችለውም ብዬ ነግሬው ነበር የሚል ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል። መክሊት፤ ክህሎት፤ ብቃት፤ ተመክሮ፤ ሰብዕና፤ ሁሉም አላቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ።
https://www.youtube.com/watch?v=qQZgnjvpukQ
#Ethiopia #EthiopianNews

Ethiopia: የኢትዮታይምስ የእለቱ ዜና EthioTimes Daily Ethiopian News

 | Debretsion, Beyene, Abiy, አብን Belete


Published on Mar 27, 2019

ይህን ያሉበት ምክንያት ህወሃቶች ያጠመዱትን ፈንጅ አሳምረው ስለሚያውቁት ነው። በዚህ በተጠመደ ፈንጅ ደግሞ ቀስ ብለው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ገብተው እንደሚወድቁ ያውቁ ነበር። ስለዚህ ተንብያለሁ ይሉናል ዶር ደብረጽዮን። 

የጠ/ሚር አብይ አህመድ ችግር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በነበራቸው የምርቃት ልክ ለመጓዝ ከመክሊታቸው ጋር መቃረናቸው ነው ይህን የፈጠረው። ሚሊዮን ደጋፊው እኮ ሉላዊ ነበር።

ያን ሁሉ ሰው ቀስቅሶት አልነበርም ድጋፍ የሰጠው። በግራ በቀኝ ከ አሁን በከፋ መልኩ ወጀብ ነበር። ያን ወጀብ ጥሶ የወጣው ምኞታችን ምርቃት ስለነበረ ነው። መንፈሳቸው በአባቶቻችን ጥበብ አክብሮት የተነሳ፤ በዛም ጸበለ ጻዲቅ የተቃኘ ነበር። ያን የሳቱ ዕለት ወይንም መስዋዕትነቱን ለመቀበል ያልፈቀዱ ዕለት ምርቃቱ ተነስቶ አሁን በተቃርኖ ለቆመው ነፍስ ሁሉ መኖ እያቀረቡ ራሳቸውን በራሳቸው ታገሉት። ይህ ሲሆን ደግሞ እርጋታን መቃኘት ሲገባ ነጋ ጠባ ስብሰባ እያሉ በዛም እዬተገኙ መሪነታቸውን ወደ ተራ ካድሬነት ለውጡት፤ ብስጩም ሆኑ ... 

አሁን እንደገና ለመመለስ ጥጋናውም የሚሰራ አይመስልም። ስለምን? ቢባል ሃብቱን የሰጠው ፈጣሪ ዕውነት ስለሆነ ዕውነት ስለተሰቀል ስላዘነባቸው። በዚህ ውስጥ ብዙ ንጹሃን፤ ቅኖች፤ ደጎች፤ ንዑዳንም አዝነዋል። መስዋዕትነቱ ቀላል አልነበረም አንድ አዲስ ፖለቲከኛ ሰው ወደ ሥልጣን መጥቶ ቅቡል ለማደርግ። 

ያን የሰጠ መንፈስ ሊከበር ሲገባ እንሆ ተዋረደ። ይህ ደግሞ ወዲያውኑ ነው ያዬነው ያዋረደው ሲከበር ያነገሰው ሲዋረድ ወይንም ሲቃላል እንዳልተፈጠረም ሲታይ። በመንፈሳዊው ዓለም ፈጣሪ እኩል ነው። በደልም ተበዳይንም ይዳኛል ... 

ለዚህ ነው አንደበታቸው እራሱ የመናገር አቅሙ የላላው። በኬክ ቆረሰው በዘመናዊው ኦነገዊው ኦዴፓ ላይ ገና አፍ ፈቺ ሆነው ነው ያዬኋዋቸው። ውስጣቸውን የሰጡት ዕብለታዊ ምህድስና ድፍረታቸውና ያን ብርቱ በራስ የመተማመን አቅም ክፉኛ ፈትኖ አላላው … እና አሁን ከሆነ ወይ በተማህጽኖ በመልመጥመጥ፤ ወይ ደግሞ በብስጭት ሆነ መደወርያው። ሁሉም ስስነት እና ትነትን የሙጥኝ አለ። 

በውስጣቸው ውድቀታችን ለሰሩትም ድል እርካብ አጎናጸፏቸው፤ ክብር እና ልዕልና ተሰጠ በገፍ፤ እና በአዲስ አቅም እንደገና ለመውጣት እያቆበቆቡ ይገኛሉ። የኦሮሞ ፖለቲካ መውደቅ ለብዙ ህሊና ትፍስህት ነው። ሰው ከአራጁ ጋር እንዲውል እንዲሉ የ11 ወራት ሠርግና መልስ አሁን መንፈስ ሲራቆት ስለቴ ሰመረ መሆኑን እያስተዋልን ነው። ቁፋሮ ምናምን ... ነገር ... 

ብልህ መሆን ተሳናቸው። በመስመራቸው ላይ ደንቀራ ነገር ካለ፤ ተጨማሪ ተደራቢ አመራር ከኖረ፤ መጠለፍም ከገጠመ ይህን ቀድመው ለህዝብ ይፋ ማድረግ ግዴታ ነበረባቸው። ለህዝብ ዕውነቱን ተናገረው ጸንተው መቆም ይገባቸው ነበር በ ኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ውስጥ እንዲህ የዲስክርምነሽን ምህንድስና ባልደረባ ከመሆን። ሁለት ወዶ አይሆን። አንዱን መምረጥ ነው። 

ሁሉ ሰው መብት አለው። የመውደድም፤ የማክበርም። ያለመውደድም ያለማከብርም። መከበር መወደድ ያለበት ዕውነት እና ጽናት ብቻ ነው። ትናንት መልካም ነገር ከተሰራ ቀጣይነት ከሌለው ራሱ መልካምነቱ እራሱን እያተነነ ይሄዳል።

ትናንት ሺዎች ከእስር ሲለቀቁ ስጋት የማይጎበኛት አገር ለመመሰረት ከሆነ አሁን ፉከራ ሲመጣ የትናንት እስረኞችን ለማስፈታት የተደረገው ተጋድሎ አቅም ይባክናል። የ18 ቀኑ ዘግቶ ምክርም ከንቱ ይሆናል። መስዋዕትነቱም ይተናል። ይህን አስታርቆ ለመሄድ ደግሞ ውስጡን የገለጠ አድሏዊ መዋቅር አፍጦ አለ። ስለዚህ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሌላ ጠ/ሚር እዬተመሩ እንዳሉ ምንም ምስክር አያስፍልግም።
 ለመከላከያ ሠራዊት ንግግር ከማድረግ በላይ ምን ሊመጣ ነው። ውጭ ጉዳይ ተቀምጦ አዲስ ቆንስሊ ጽ/ቤት መርቆ መክፈትስ? የተፎካካሪ ፓርቲዎች የመጀመሪያ ግንኙነት መገኘትስ? የ አባቶች ወደ ትግራይ እና ወደ አማራ ክልል ለመሄድ ቃለ ምህዳን ጉዳይስ? ሁሉም ሲሰላ ኢትዮጵያ በሞግዚት እንጂ በ አውንተኛ ጠ/ሚር የተመራች አለመሆኗን እናስተውላለን። ልብ አለን። 

በቀደመው ቅንነት ቢሆን ምንም አልነበርም። 


አቶ ለማ መገርሳ አንድ ሚሊዮን ኦሮሞዎችን አዲስ አበባ ለማስፈር ሲባል ሆን 
ብለው ከሶማሌ ክልል ራሳቸው እንዳፈናቀሏቸው ተናገሩ
February 26, 2019
ግን ይህን ተሸክሞ ራሱ ኢህአዴግ እንደግንባርም ፈተና ውስጥ ነው ...ይህ ዓለም አቀፍ ህግጋትን ድንጋጌዎችን የጣሰን መንፈስ ተሸክሞ እስከምን ድርስ? 

ለዚህ ለውጥ በግልም በድርጅትም ሁሉም ዋጋ ከፍሏል። ሁላችንም ያደረገውን ተጋድሎ ለኦነግ ዓላማ ስኬት አልነበረም። በፍጹም። አነግ እኮ ጨካኝ ድርጅት ነው። ኦነጋውያንን ከመንበር ለመስቀል ኢትዮጵያን በጠራራ ጸሐይ ለማሰቀል አይደለም አልነበረም ልፋታችን።  እውነት ከሆነ ታገድሎው ዲሞግራፊ ለመለውጥ ያለው ዘመቻ ተቀይሮ የመጡ ሰዎች ወደ ነበሩበት መመለስ ግድ ይላል። ዲስክርምኔሽን ስለሆነ።



አንዱን ከሥነ - ልቦና በመንቀል፤ ሌላውን ደግሞ በሥነ - ልቦናው ላይ ለመጫን፤ በሌላ በኩል ከሱማልኛ ቋንቋ ጋርም ለማፋታት የተሰራ ሴራ ነው። ስለዚህ ደርብ ንብርብር ዲስክርምኔሽን ስለሆነ ስህተትን አርሞ ወደ መጡበት ወገኖቻችን ወደ ኖሩብት ቀዬ መመለስ ግድ ይላል … በስተቀር ግን ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው የሚሆነው። ህወሃት ወርዶ በአዲስ አቅም እና ጉልበት ትውልድ የሚባክንበት ምንም ምክንያት የለም። 

ለነገሩ የምህንድስናው መርዙ እጅግ ረቂቅ ነበር። በሙሉ የተፎካካሪ/ የተቃዋሚ/ የተቀናቃኝ ድርጅቶችን በሙሉ አልዞ አዝሎ መጠጊያ ነስቶ የተከወነ ነው። አስገባን ወደ አገር የሚባለው ያው ሌላው የዴሞግራፊ ምህንድስና ሰለባ ነው የሆነው የነጻነት ተጋድሎ መንፈስ ነፍስ ሁሉ በርድ ነው የተለቀቀበት። የ ኦሮሞ መንፈስን ደግሞ በተለዬ አያያዝ እና ጥበብ ወጥ መንፈስን እንዲፈጠር በትጋት ተሰርቶበታል። ማንም ሳይጨመርበት። ብቻ ጉዟችን ለብለብ ስለሆነ ይህን እንኳን በጥሞና ለማዳመጥ አልተቻለም። 

በሌላ በኩል ሊስተካካል ይገባል የምለው አሁን ከሆነ አማራ ክልልን እና አዲስ አባባን የመዝለፍ እና የመወረፍ ጉዳይም ይቅርታ ሊጠዬቅበት ይገባል። ብአዴን አጋር ሆኖ የሚቀጥል ከሆነ። ብአዴንም ቆፍጠን እመራዋለሁ የሚለው ህዝብም ልጆቹም እዬተወረፉ ስለሆነ። እንዲያው ይህን እኔ የምለው  በደመነፍስ ነገን እንይ ከተባለ ነው ይሄ

 … ሌላው መሰረታዊ ጉዳይ ኢትዮጵያን ኦሮማማ የማድረግ የሴራ ሹረባ፤ የደባ ታሬና ቁንጮ በአስቸኳይ ሊቀም ይገባል። 

ኢትዮጵያ የ80 ብሄር ብሄረሰቦች ባህል፤ ወግ፤ ልማድ፤ ትውፊት አገር ናት። ለዚህ ማዕከሏ ደግሞ አዲስ አበባ ነው። ስለዚህ አዲስ አባባ ላይ የተጀመረው የኦሮማማ ዲስክርምኔሽን በአስቸኳይ መቆም መቋሚያን ማሰመርም ነው። እማማ አፍሪካ አራሷ ቤቷ በራሷ ላይ እዬፈረስ ስለመሆኑ ልብ ልትለው ይገባል። ሂደቱን በጥንቃቄ ልታዬው ይገባል።

የዚህ መከራ ምንጩ የአባቶቹን የጥበብ ልቅና ተስጦኦ እና ተመክሮ ተጻሮ የወጣው የ66ቱ ፖለቲከኛ እንደ ኩሬ ውሃ ባለበት ሲባዝን ራሽያ እና የቻይና ርዕዮት ተመልሰው የአባቶቹን ቅኝት በማክበር እና ዝቅ ብሎም ለማደር ወሰነ። በዚህም የተደላደለ የተረገጋ ሥርዓትን እዬመሩ ይገኛሉ። ተወዳዳሪም ተፎካከሪም ናቸው። እኛ ደግሞ በዬዘመኑ እንደጥንቸል ኢትዮጵያን መሞከሪያ ጣቢያ በመድረግ እያመስናት እንገኛለን። ለኢትዮጵያ ኦሮማማ ብቻውን አይበጃትም።

 አካልነቱ በበላይነት ሳይሆን ብህብርነቱ ደረጃውን ጠብቆ መሆን እንጂ እጬጌ ሆኖ እንዲገዛ ሊፈቀድለት አይገባም። መጀመሪያ ፍቱን መዳህኒት ከሆነ በዛው ክልል ለሚኖሩት ሚሊዮን የሌላ ብሄር ብሄረሰብ ምንዱባን ሰው ናችሁ ብሎ ይቀበል ኦሮማማ … ሰው ገድሎ ዘቅዝቆ ሲሰቀል፤ ሰው ተገድሎ ሲቃጠል እያዬን ነውና።  

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በ66ቱ አማሽ ፖለቲከኞች ቅኝት ጊዜ የነበሩ እንኩቶ ዕሳቤዎችን አግንኖ የምክር ቁንጮ በማድረግ ያለው የመገፋፋት ሹርባ የሴራ ድር አሁንም የትውልዱ ብክነት ላይ መደበኛ የመተንፈሻ ቧንቧ ሰርቶ በተገኘው አጋጣሚ ቀን ሲገነባ፤ ሌት ሲናድ ... 

ጥላቻ ነግሶ፤
ፍቅር ተደቁሶ፤
ቃል ባከኖ፤
መታመን ተኖ፤ እንደገና ወደ ለመደብን እንጦርጦስ ደግሞ ዘብጠን እንገኛልን።

ቢያንስ የአገር ሙሴ መሪ ዕውነትን መድፈር ተስኖት መርከቡ አቅጣጫውን ስቶ በወጀብ በመንገላታት በአቆበቆቡ አዲስ የሰለባ ድሎች ሟተት - ንደተ ምኞት ላደረጉ ነፍሶች ቦታውን ለመልቀቅ ራሱን አሰናድቶ ይገኛል።

መፍትሄው አንድ ነገር ብቻ ነው። በዕውነት ውስጥ ጸንቶ መቆም። ዕውነትን መድፈር። ዕውነት የሆነው ነገር ኢትዮጵያ በሸቀጥ መልክ ከውጭ ተጭና የመጣች አገር አለመሆኗ ነው። ኢትዮጵያን የፈጠራት የቀደመ የሰለጠነ የተጠበበ የዘመነ የታሪክ ምኸዋር አለ። ያን የታሪክ ምኽዋር ተጠይፈህ፤ አግልለህ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማስቀጠል ዳጥ እና ምጥ ነው። ልብ ይስጣቸው መሪዎችን።

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።