እርፍ! እልልልል ይታከል … እውነት ስለተሞሸረች …

እርፍ!
እልልልል ይታከል …
እውነት ስለተሞሸረች

„በውን ጠበብ አትጮኽምን?“
 ምዕራፍ ፰ ቁጥር  ፩
መፅሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
የራስ ነገር ከሌለ በዬዘመኑ እንዲህ ነው! ቅልውጥ!
ሚሊዮን ልጅን መንፈስ ጎዳና ተዳደሪ ማድረግ!



·       ተህሊና ትቀምጥ ይህቺ ወግ!
/ ብርሃኑ፤ ኦዲፒ እና አዴፓ (ሚኪይ አምሃራ)

ኢንጂነር ታከለ ኡማ አዲስ ፕሮፖጋንዲስት አገኙ …በነጣ ዙፋናቸውን ተሸካሚም አገኙ በብላሽ! እንግዲህ ለኢንጀነሩ ቀይ ምንጣፍ ይጉዙላቸው… ሲያጋጥም የግንብ ጉድጓድ አርቲቡርቲ ግጥም!

ዋው¡ፍቅሩ ደርቷል
በአማራ ላይ ተዶልቷል! 
አክ! እንትፍም በቀናቀኑ ተበጅቷል!

የሰንበቱ ግርግር ከባህርዳር ከዚህ ጋር ይታይ የእጃችን አውጣን የሜንጫና የክላሽን ሸበላ … ሚዛን የማስጠበቅ ትውና … ብአዴንን የማሰጣት ድርማ … ፐፐፐፐፐፐፐፐፐ

ባለአደራ ምናምን የሚባለው ነገር ለኔ ትክክል አይመስለኝም/ ብርሃኑ
March 28, 2019
<<ባለአደራ ምናምን የሚባለው ነገር ለኔ ትክክል አይመስለኝም። አቶ ታከለ ይሄን የማሸጋገር ሂደት በሚመለከት በትክክል ያልሰራው ነገር አለ ከተባለ ሂስ ማቅረብ ጥሩ ነው።>>
/ ብርሃኑ ነጋ

ምን ሲነጋ ማን ሲያነጋ ጨለማ ሲያወጋ ቀጥሎ ሊያዋጋ ለዚህ ነበር በሂልተን ሆቴል  አማራ ህዝብ የተወረፈው ለ አንድ ክልል ብለን ህገ መንግሥት አናሻሽልም ብቻ አይደለም ልበ ቢሶች መንግሥት እንሆናል ብላችሁ ታስባላችሀን ተብሎ የተላገጣው፤ ለዚህ ነበር በዬተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አማራ እሚቃልለው … እም … ያዝልቅ ፍቅር ብለናል። የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሊንክነት በደማማዊነት እንዲህ በአርሲነት ጃዋርዊነት መስመሩን እስጠብቆ እዬሄደ ነው ... የብአዴን መከራም ተዚህ ይዘረዘራል .. አልገባውም እንጂ ... ነገን ይጠብቅ ግርባው ብአዴን ...

 … ገና ሌላም መተርትር ጠብቁ … አሁን ከከአቶ ንጉሱ ጥላሁን ጃዋርውያን ዳግሞ ይደገም ሌላ ባለዳግም አናጋጋው ተከሰተ እኛም ብለናል እኮ ሰልፍ ላይ እንደተነበር … ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ከተገኘ ደግሞ ኢትዮጵያ ለጨረታ - ለቀረመት  - ድርድር ትውላለች … ስኬት እና ነፍሱ አራባ እና ቆቦ ስለሆነ... የሥም ቁልል ሲናድ አገር ያነድ ... ቃል የዕምነት ዕድ ላልሆነበት ነፍስ ቀላሉ እና አቋራጩን መንገድ መከተል ነው … ከሞቀው መጣድ፤ የተጣደው ሲቀዘቅዝ ደግሞ መብርድ …. እትትት እትትት … መሹለክም። 

እልልል አንድ! እልል ሁለት! እልልል ሶስት! … እኔ የአሁኑ ትርምስ እንደ መልካም አጋጣሚ ነው እማዬው ብዬ አልነበረም … አዎን! እንዲህ እዬተንገዋለለ ምርጥ ዘር እና እንክርዳድ ይለያል። 

"አብይ ሆይ" 

እንግዲህ አትምባት አደራህን የልብህን አግኝተኽ የለንም? ተዛች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ላይ ወይንም በስውር አንሸራሽረው ግልቡን መንፈስ። መላሾ ተሰጥቶህ የለም ወይ? ለነገሩ በፍቅር እብድ እና ክንፍ ተብሎ ነበር … እኔ ተቃቅፈው ቢተኙ ምንአለ እስክል ድርስ አሁንም ቅድምም የአፍ ማሟሻ ነበር። 

ሌላ ድርጅት የተፈጠረ አይመስልም ነበር ... ለነገሩ በሳምንት ሦስት ቀን እጅ መንሳት እጅግ ብዙ ነው ... ሌላው ሁለት ጊዜ ደጅ መጣናት ይህም ብዙ ነው ለአብይወለማ አንድያ ልጅ ተዛም አንድ ቀን ተገኝቶ መሳላም ....ሲያሰፈልግመ ሸርተቴው ቀን አይቶ ያንገዋልለዋል ወይ ወደ ዲሲ መጪ ... እእ ኤርትራዬስ? 

 ያው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገፋ ተደርገው ዶር አንባቸው እዛ አንዲሄዱ የተደረገበት አምክንዮ ይኸው አይደለ …? ነው ዋናው ጠ/ሚር ይይዙት ይሆን ደርበው … ተለዋጩ ጠ/ሚር አይደለም ያልኩት ዋናው …
  
እኔ ከጥዋቱም ብያለሁኝ። የመግለጫው ብዛት ወዘተረፍነት፤ የሊቀንበሩ ቃለ ምልልስ፤ የጸሐፊው አቋም የእስክንድር ንቅናቄ ስለመሆኑ… ከእንቅልፍ ቀስቃሹ።   ግንቦት 7 እንዲህ ነው። አሁን የጠ/ሚር ቢሮም አብሮ ተቀናጅቶ እዬሠራ ነው። እዛው ቢሮ አላቸው ግንቦቶች።

ግንቦት 7 የለመደበት ነው መለጠፍ የእኔ የሚለው ሃሳብ የለውማ። የሞቀ ሲያገኝ ጠጋ ሲቀዘቅዝ መለጥ ነው። የሚያሳዝኑት እሱን አምነው እሱን የሚጠጉት ነፍሶች፤ በዬዘመኑ የተደገማባቸው ይመስል ፍዳቸውን ማዬት … ሞመትም አለበት። ስንት ትንታጎች እኮ ነበሩት። ግንቦት 7 ያመነ ጉም የዘገነ ነው … ብቻ ተጽዕኖ ፈጣሪ ያግኝ ሾከክ ነው … አንዱ መለያው ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን መልቀም ነው። ግን ይኸው ባዶ እጂን እዬተንኮረኮረ አገር ገባ ... ነገ ደግሞ ይታያል ... 

ወዮልህ ብአዴን! ወዮልህ አብን! ወዮልህ እስኬው! አየኸው ተሜ … አዲስ መልክ እሻለሁኝ ብሎ ተሜ ማን ሲባል ግንቦት ሰባትን ለዋቢ አቅርቦ ነበር፤ እንዲህ ቀን አዋራርዶ አሳዬኽ እንደ ወረደ …. እኔ እኮ ብዬህ ነበር። እዚህ ባለፍዳዎች አለንና።

 „ጠ/ሚር አብይ አህመድ አምነዋለሁኝ ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ።“ የአገርዊ ንቅናቄው ሰርግና ምላሽ፤ የጫጉላ ሽርሽር በነበረበት ጊዜም ደግሞ „ሌንጮውን አምነዋለሁ ብለው ነበር፤ „ያቺ የብራስልስ ላይ የተበሰረችው የኦሮሞነት ደም አለብኝ ትንሽ የረዳም ይመስላል … ገበሮነት ይሁን ገበርነት አይታወቅም። አቶ አበበ በጋለ ከአቋሙ ግር ቀለበት አሳስሯል።. ሌላ ኩዴታ በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህምድ ከመጣው ደግሞ አዲሱን ሥም የለሹን „አምነዋለሁኝ“ አይቀሬ ነው። 

እሺ አሁንስ ልደቱ ክህደቱ ወይንስ አንጋጋው ክህደቱን የቱ ላይ ነፍስ ትረፍ ይሆን? ትውልድ እንዲህ ነው የሚባክነው … ለዚህ ነው እኔ አፍንጫህን ላስ አቶ ሂደትን፤ እጬጌው ሂደትን የጣፍኩት …

አፍንጫህን ላስአቶ ሂደት።

March 21, 2014

እጬጌው ሂደት።

08.04.2018
እሺ አቤቶ ኢሳት ደግሞ የት ይሆን አድርሻኽኽኽኽኽ …  የታች ዓመናውንም የላይ አምናውም፤ የዘንድሮውን  … አስኬዱት ….

ሌንጮ ለታ ከዶ/ ዲማ ነገዎ ጋር ካርቱም ለምን እንደሄዱ ተናገሩ | / ብርሃኑ ነጋ የኦሮሞ ቄሮዎችን ትግል አደነቁ

ESAT Tikuret with ENM leaders October 23 2017

 

„የመጨረሻ አድርባዮች … ይህን ሥርዓት ሲያስፈጽሙ የነበሩት እንኳን መርከቡ እዬሰመጠ ነውና እንዝለል ብለው ሲሄዱ እንደ እኛ ለውጥ የሚፈልግ ሃይል ኦ! እነኝህ እንዲህ ነበሩ እንዴት እናምናቸዋለን ከሚል ይህን የማዳከሙን ነገር እንዲቀጥሉ አብረው እዬሰሩ „እነዚህ ሰው ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ ሳንረሳ ኦል ኦፍ ዘሰደን የዴሞክራሲ ጮራዎች እኛ ነን ብለው ቢናገሩ ማንም እንዳማያምናቸው፤ እንደማይሰማቸው፤ ግልጽ ሆኖ ግን አገር ለማዳን አገር እንትን ለማድረግ እንደ እነኝህ አይነት ሃይሎችም ትግሉን ይጠቅማሉና እንትን ማድረግ አለብን ከሚል ነው ይሄ ከነብአዴን ውስጥ ስንሰራ የነበረው ኦህዴድም ውስጥ ሌሎች ሃይሎች ሲሰሩ የነበረው  …

"እንትን" ይህቺን የጉለሌለው ሉዑል አቶ ዳውድ ኢብሳ ሲሏት ነበር ይሂቺ "እንትን" የ የኤርትራ ዜዬ ሳትሆን አትቀረም? ጋዜጠኛውም ምንድናት ይህቺ "እንትን" ብሎ አይጠይቅም። 

አንድ ነገር ዛሬ ጋዜጠኛ ሰሜነህ ባይፈርስ ተፈርቶ ሚዲያው ዋልታ ሆኖ የተመረጠው ጋዜጠኘ ግን ለስለስ ያለ ከሌላ ጋር ነው ቃለ ምልልስ የተደረገው። ወንዳታ! ተፈሪው ጋዜጠኛ አቶ ስሜነህ ባይፍርስ። በውነቱ ድል አድርገሃል አንተም አቶ ልደቱ አያሌውም በሹልከታ ነው የተከወነው። የፈሪ ዱላ አይነት እንዲህ ጓዳ ለጓዳ ... 

አሁን ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ "አድርባዮች" ላሏቸው ጋር ተዋሀደዋል አረተኛ ሆነዋል እንደማለት። ዛሬ ደግሞ ተስፋዬ፤ አሻግሬ የሚል የዳቦ ሥም አውጥተውላቸዋል … እርፍ!

ግን "ኦል ኦፍ ዘሰደን የዴሞክራሲ ጮራዎች " ኮከብንን እንዳይሉ አስጠነቅቀው ያ አልተሳክቶም ነበር ሰኔ 16 ላይ እብደት እንደነበር ትንሽ ወፊቱ ሹክ ብላለች። የአሁንን አያድርገው እና ሙሴም፤ መላክም ብለናቸው ነበር። ታቦትም ይቀረጽ! ድርሳንም ይቀለም! ሚሊዮኖችም ...  ያን የፕሮፌስር ብርሃኑን የቀደመ ማስጠንቀቂያ ከምንም ሳይቆጥር አፋንክሎ ብሎ አጬጌቷቸው ነበር የሆኑት አሁን የተፈነገሉትን የብአዴን ጓዶቻቸው ጨምሮ። ዘውድ ተክሊል በደያመንድ … ህዝብ ሲያደርግ ግን ትንሽ እንደ ማረር ትንሽ እንደመተክን ... ወዘተረፍ በወዘተረፍ ... ብሎ ነበር ማህበረ ግንቦት 7 ከትከት ... 

ሌላም ተጠንቀቅ አለበት አለርም … ይህቺን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር አንባቸው መኮነን ተደርምሰው „ለውጥ ሐዋርያ የተባሉት መጨረሻቸው ምን ይሆን?  ሌላም የኡፍኝት ደባ አለበት። ያንጊዜ በትኩረቱ ቃለ ምልልስ የሽግግር ሰነድ ዝግጅት የቀይ ምንጣፍ በተሰናዳበት ሰሞናት ማለት ነው።   

የቀደመ ከመጣም … ሹልክ ነው እንደ ተፈጥሮው …. ሚኪ አማራም የሰጠው መረጃ ብቻ ሳይሆን የሰጠው ትንተና ልብ እና ልክ ሆኖ አረፈ …. እሺ ሾልከኽ የቀረኸው የወርቅ ካባ ስትደርብ ስታሽሞነሙን ስታነጥፍ የባጀኸው አቤቶ ብአዴን የት ይሆን አድራሻኽ? … ሥምህ ለወግ እንኳን አልተጣራም … በዚኸው ጉዳይ ላይ ወልቅህ መቅረትህን ነው የታወጀልህ ... 

አማራ ሆይ ልብ ይስጥህ! ይህን ሁሉ መሳናዶ ተማርበት … እጅህ አመድ አፋሽ ስለመሆኑ እሰበው …

ESAT Tikuret with ENM leaders October 23 2017

Published on Oct 24, 2017

የጠ/ሚር ለማወአብይ ካቢኔ ብአዴን ከጨዋታ ውጭ እንዲሆን እና ኦህዴድ ከግንቦት 7 ጋር ለመጣመር ሌሎችን እህት ድርጅቶችን በመናጆ አድርገን ወጥ ፓርቲ የሚባለው ያው እርግጫ ምርአ ከመጣ። ይህንን አስቀድሜ ኮልሜያለሁኝ። ለነገሩ ጋዜጠኛ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እኮ ቀድሞ ነግሮናል።

"ለብአዴን አብን፤ ለህውሃት አረና ለአብይ ዶር ብርሃኑ ይቅርባሉ" ብሎን ነበር … ምክክሩ እንዲህ እና እንዲያ … ግን ግን አሁን በቅርቡ ባዬሁት የጋዜጠኛ አበበ ገላው አሳልፎ የሰጠውን መረጃ አስመልክቶ እንዳዬሁት ኢንሳ ዶር አብይ አህመድን በተከተ የሦስት  ሰ ዓት አውዲዮ እናጋላጥላን ዕሳቤ ግን አቶ ኤርምያስ ለገሰ በሰጨኝ ሆኖ ነው 
በአብይወለማወነጋወታከ ካቢኔ ያደመጥኩት … … ውህደቱ በተናጠል እና በክፍፍል እንዲህ ይመርበት። አንዱ ክንፍ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሌላው ክንፍ ደግሞ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ … ይዋህዱ ይነጣጠሉ እጬጌው ሂደት ይግለጠው።  

ESAT Eletawi Part Two Mon 25 Mar 2019 1 

ይሆንና ጦር ይመዘዛል በአረስቶው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ እና አዲስ አበቤ እስኪበቃቸው ይታሻሉ … አንጋች አማራ … ክልል  …. እሰከ ህዝቡ  … ድረስ ለእነ ሹልክ ያንሾካሹክ አልጋ አንጠፊ፤ ወጥ ቤት፤ ጅራፍ ቤት፤ እሳት ጫሪ … ወዘተ ይሳናዳለታል … የ የእቃ እቃ ጨዋታ በህዝብ ደም እና እንባ። አገር እንዲህ እንደ ጥንቸል በዬዘመኑ የሙከራ ጣቢያ ሆነች … ወይ ነዶ!

በዚህ ማህል ኮሰተር ከስኮስ ለለው ህውሃት ደግሞ …. ብአዴን ከላስታ አለት ይዞ ሄዶ ተነብርክኮ ይቅርታ ይጠይቅ እና የኦዴፓ እና የግንቦት 7 ሠርግ ዳስ ሰሪ ይሆናል።  
ተልብ ሲኮን  …

ህም! በዚህ ውስጥ ያው በጥርስ የተያያዘው የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ህልፈትን አብሮ ቢታይ አይከፋም …. ማስወገድ … ማስወገድ … ማስወገድ …. ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌንም እስቲ በሻማ እንሰብው ተዚህች ዜና ጋር፤ ህም አቶ አሰፋ ጫቦ ….ስገደት እንድርግላቸው የጸጋውን። አቶ ፈቃደ ሽዋቀናስ ህመማቸው ሳይሰማ ህልፈታቸው? ተረኛው ማን ይሆን?ህም! …. ሳይንቲስ አንጂነር ቅጣው እጅጉ ሱባኤ … ይሁን እም …. እግዚኦም …  ወዮልሽ! አዲስ አበባ …! ወዮልሽ አዲሲዬ የታጨልሽን አላወቅሽ አንቺ ደግ ባዕት። በዬዘመኑ ለእሳት የተሰናዳሽ … አሰናጁም ይኸውልሽ …  

ያንገላታችሁን፤ ያሳደዳችሁን፤ የጣላችሁን፤ አቅማችን እንዲቀበር የተባባራችሁ ግንቦቶች ሁሉ እነሆ አሁን ከእውነት ጋር ተፋጠጡ … ዕውነት እንዲህ ነው መከራን ከጀርባ አውርዶ ነፃ ያደርጋል … ተመስገን!

በዚህ ጠንቀኛ ንቅናቄ ስንት የአማራ ልጅ ፍዳውን ከፈለ አብሶ ስሜን ጎንደር ተመነጠረ። ስንቱ ተገረፈ፤ ስንቱ አካሉን አጣ፤ ስንቱ ዘር ፍሬውን አጣ፤ ስንቱ መከራውን ተጋተ፤ አሁን እንኳን የራሳቸውን በር ከርቸመው እነ እጬጌ ለማ መገርሳ አማራ ላይ ጫናውን ይጭናሉ። እነሱ ፍንክች የለም። እነሱ ጥድፊያ ላይ ናቸው ተልዕኳቸውን ለማሳካት። 

 …  ውጭ አገርስ ስንቱ ከሰው ተነጥሎ እንዲኖር ተገመደለበት። ጊዜ እንዲህ ነው ሁሉንም ያሳዬናል … ማንዘርዘሪያ ገዝቶ። በሉ አቅም ያላችሁ በውነቱ ይቅርታ ጠይቁን የእውነት  … ጎድታችሁናል። መሪ አልቦሽ ምኞት እና ህልም የትውልድ ብክነት ስለመሆኑ ነበር የሰበክነው። ተመስገን። ዛሬ ትራሴን ከፍ አድርጌ እተኛለሁኝ። 

አንድ ነገር ተረሳኝ ያ የመከራ ዘመን አብረው የተጋሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ  አጅሬ ግንቦት 7 በስል ገብቶ አሻም ያለውን እንዲህ መለመላ ለማስቀረት ክንዱን መነጠል የለመደበት፤ ይገርም ነው የአባ ተርትር አናጋጋው ሬሳ ሃሳብ ተሸካሚው የግንቦት 7 ነገር እንዲህም እንዲያም ተዚህም ተዚያ ማዶም ማላጋት ...አኮ እነ አብይወለማወታከለስ ይድኑ ይሆን? ? ? ?!!!! ወይንስ ይተረተሩ ግንቦት ትውር ያለበት መናድ መክሰም ነው። ብቻ ነገ የሚነገረን ይኖረል።  ጠብቁት። 

አስቲ እነኝህ ተደግመው ይታዩ  … ሌላም የቆያዩት ይደገማሉ …


ታቅዶ ስለመከወኑ በማስተዋል ይመርመር፤

የኢዴፓ እጩነት /አዲስነት ትልሞሽ/

አይዋ ምንትሶ።


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ!

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።