ጋር።


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
ጋር።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
 እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
 ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቊጥር ፱



እንዴት ናችሁ የኔታዎቼ። የጨፈገገው ቀን ስለሆነ ዛሬ ከመደበኛ ተግባሬ ወጣ ብዬ በዚህ ዙርያ ማተኮር ፈለግሁኝ። ዕንቅልፍ እና ዓይኔ አልተገናኘም።
ዓይኔ እራሱ ሞግዱ ጭፍራዎቹን ልቀቁኝ ብሏለኝ እንደ ዳሽን ተራራ እንዳኮረፈ ነው ትናንትም እንዲሁ ነበር። የምኖርበት ተዋዳጅ ከተማም ደብሮታል። ቤተ መቅደሴ ቤቴም እንዲሁ፤ ጾም ገብቷልኝ። ቤቴ እራሷ ሱባኤ ላይ ናት እኔ ደግሞ ስግደት ላይ። … ጭነቱ ቻል በል ብሎ መጥቷል።
ምን ያህል አቅም እንዳለኝ አላውቀውም። የእኔ ድንግል ታውቃለች። አይዋ ድብርትን ገፋ ለማድረግ ዛሬ ጋር በሚል ርዕሰ ጉዳይ እንዲህ ለፌስ ቡኬ ታዳሚዎች እንደህም አልኩኝ። እርእሱ „ጋር“ ነው። ሥርጉተን በእነኝህ ሊንኮች ታገኟታላችሁ።
ከሥርጉተ ጋር ለመገናኘት በዚህ ….
Kenebete {ቀንበጥ} Blog

Sergute Selassie ሥርጉተ ሥላሴ

ቀንበጥ ሚዲያ

 

3.   https://www.youtube.com/channel/UCb4Maqp24liAGdbPE553WGA

Sergute Selassie

 

ሦስተኛው ዩቱብ ወጣ ያለ ቻናል ነው። የፍቅራዊነት LOVEISM ተፈጥሮ እና መርሆቹ ለመነሻ የሚሆኑ የቃላት ፓስተር የቢዲዮ ክሊፕስ ይሰራበታል። ከአራት ዓመት በላይ ሆነው ከ200 በላይ የቢዲዮ ክሊፖች አሉበት። ልክ የትንሳኤ ዕለት ነው የጀመርኩት። የድምጽ አልባው የፍቅር ተፈጥሮ እና መርሆዎቹ ቻናል በሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ ቅዬሳ ነው። ትንሽ ያደክማል ይሞግታልምLoveIsm Nature and Principeles. ከራሴ ጋር ፈተና ተቀምጬ ነው የምሰራው።  

 

ዓላማው ዓለም ደምናለች፤ የዳመናው መሰረታዊ ጉዳይ የፍቅርን ተፈጥሯዊ መርሆዎች እንደ አንድ የሙያ ትምህርት በመደበኛ የሰው ልጅ ስላማይማረው ነው። የፍቅር ተፈጥሮ እና መርሆዎቹ ኤክሰፐርት፤ ሳይንቲስት፤ ተመራማሪ፤ ተፈላሳፊ፤ የምርምር ተቋማት፤ ከህጻናት ማቆያ ጀምሮ አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ኮሌጅ፤ ዩንቨርስቲ፤ ራሱን የቻለም ማህበር የለውም። ባለቤት አልባ ነው። የሥልጣኔው ሁሉ እኔ እማዬው ጭነቅላት እንደሌለው ሰው ነው። የዓለም ፍላጎት ማዘዣ ጣቢያ እንደሆነ ነው እኔ እማስበው።

 

ስለ ፍቅር ተፈጥሮ እና መርሆዎቹ በመደበኛ ራዲዮ፤ ቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ መጋዚን፤ ዕለታዊ ጋዜጣ የለውም። ስለዚህም የፍቅር ተፈጥሮ እና መርሆቹ ድምጽ አልባ ሆኑ። ስለሆነም ዓለማችን በዬዘመኑ ጸረ ተፈጥሮ አስተሳሰቦችን ማሰተናገድ ግድ ሆነባት። ጸረ ተፈጥሮ እና ጸረ ሰው ድርጊቶች ደግሞ ሃዘናችን አበራከተው መቋጫም አሳጣው።

 

ሁላችንም ስንወለድ ንጹህ ህሊና ነው ይዘን የምንፈጠረው፤ የ እኔ የልብ ቅርጽ እና ይልብ ሃላፊነት የትም ዓለም ከሚኖር ፍጡር ጋር አንድ አይነት ነው። ደማችንም ቀይ ነው። አንጎላችን ነጭ ነው። ሳንባችን ተመሳሳይ ነው። ቆዳ እንደሆነ ልብስ ነው መሸፈኛ።

 

ክፉ ነገርን ከተፈጠር በኋዋላ ነው የምንማረው፤ ወይ ከቤተሰብ፤ ወይ ከማህበራዊ ኑሮ፤ ወይ ደግሞ ከመንገድ ላይ። ለምሳሌ የቤተ- መንግሥት ልዑላልን እና ልዕልታንን የሚቀበላቸው ማህበረሰብ አክብሮታዊ፤ ባህላዊ ወጋዊ ስለሆነ ብዙም ለከፋ ሥነ - ምግባር አይጋለጡም። አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፉበት ቦታ ለተሟላ ሰብዕነት ስንዱነት ምቹ ስለሆነ። ሌላቻችን ግን አደራ እምንሰጠው ወደ ቅይጡ መከራ ነው።

 

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ በዚህኛው ዘመን ደግሞ የሰው ልጅ ከሰው ግንኙነት ጋር ከሚኖረው ወደ ቁስ እና ማሽን ተኮር እዬሆነ ነው። የሰው ልጅ ለተፈጠሮ ስጦታ ያለው አክብሮት በዚህ ከቀጠለ ያስፈራኛል። ስለዚህም ዓለም ለውጥ በሥነ - ምግባር ማምጣት ከፈለገች እና ይህን ውጥንቅጥ ቀውስ መቆጣጠር ለመጀመር ከፈለገች ዓለም የፍቅርን ተፈጥሮ እና መርሆዎቹን አጀንዳዋ አድርጋ ወርክሾፕ፤ ፓናል ዴስከሽን፤ ዓለም አቀፍ የትምህርት ካሪክለም፤ የትምህርት መሳሪያ ማዘጋጀት ይኖርበታል የሚል ነው ዘመቻው።

 

ይህን ዓላማዬን ለተባባሩት መንግሥታትም፤ ለአውሮፓ ህብረትም ልኬላቸው መልስ ልከውልኝ ነበር። እንዲያውም የቀድሞው የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ጸሐፊ እኒያ ደግ በእጅ ጹሑፋቸው በተጻፈ ፖስታ መልሱን በአድራሻዬ ልከውልኛል። መቼስ ሰው አክባሪ ሲባሉ እንደሳቸው የለም። ንጹህ ሰው ነበሩ። ሌላም አቤቱታ ልኬላቸው የወሰዱት እርምጃ የሰማይ ታምር ነበር።  

 

የሆነ ሆኖ በፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች ላይ የጠበቅኩትተግባር የጠበቅኩት ምንም ስለሆነብኝ በእጄ ባለ ነገር መጀመር ፈልግሁኝ።  ስለሆነም ለአወርኔስ ብቻ ይህን የቃላት ፖስተር ቻናል ጀመርኩት። እኔ ሳልፍም ሌላ ተክቶ እንዲሞግትበት በማሰብ።

ዓለም የፍቅር ተፈጥሮ መርሆች ቀን ሊኖራት ይገባል።

ዓለም የመንገድ ላይ ትርኢት በፍቅር ተፈጥሮ መርሆች ላይ ያተኮረ ሊኖራት ይገባል።

ዓለም ለፍቅር ተፈጥሮ ሙዚዬም፤ ኤግዚብሽን ሊኖራት ይገባል።

 

አለም ለፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች መጸሐፍት በብዛት ልታሳትም ይገባታል።

 

ዓለም ለፍቅር ተፈጥሮ ቲያትር፤ ፊልም ለሚሰሩ ብርቱዎችን ልታበረታታ ይገባታል።

 

የፍቅር ተፈጥሮ ሲባል የፆታዊ ግንኙነትን ብቻ አይደለም። ተፈጥሮን ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ደስታውን በእሳተ ጎመራ ሊያገኝ ይችላል፤ ወይንም በፏፏቴዎች፤ ወይንም በእንሰሳት፤ ወይንም ለሚወደው ሰው ስጦታ በማበርከት፤ወይንም ጭል ያለበርሃ ወይንም በተራራ፤ ወይንም በበረዶ ፍቅር ለመሰጠት ይችላል። ወይንም በቀለማት፤ ወይንም ልብስን በማስጌጥ፤ ወይንም አርት ውስጥ በንቃት በመሳተፍ።

 

ስለዚህ የፍቅር ተፈጥሮ የሰው ልጅ ኑሮውን ለማስዋብ፤ ለማሳመር፤ ለማቅለል፤ የውስጥ ሐሤቱን ለመፍጠር የሚፈቅዳቸው ሁሉ ነገሮችን አክብሮ ዕውቅና ሰጥቶ መነሳትን የሚያካትት ነው። ለምሳሌ ፕሮጀክቱ የደን ምንጠራን ይቃዋማል፤ ቃጠሎን ይቀዋማል፤ ጦርነት አጥፊ ስለሆነ እሱንም ይቃወማል፤ መጫንን፤ መጨቆንን፤ መብት መረገጥን፤ የቅርስ፤ የታሪክ፤ የትውፊት ውድመትን፤ ማቃለልን ይቃዋማል።

 

ይህን ጉዳይ በተሳካ ሁለንትናዊ በሆነ ሁኔታ ለመተርጎም ግን ህጻናት ከቤታቸው ጀምሮ በፍቅር ሚኒ መድረክ ውይይት ሊያደርጉበት የሚችሉትን ነገሮች ማመቻቸት ግድ ይሆናል።

 

የፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች ማህበራት በዬደረጃው በፈቃደኞች መፈጠር ይኖርባቸዋል። ፍቅር ምንድን ነው? ለማን ተፈጠረ? ስለምን ተፈጠረ? ተፈጥሮ ምንድን ነው? ለማን ተፈጠረ? ስለምንስ ተፈጠረ? የፍቅርን ተፈጥሮ መርህ ምን ያስደስተዋል? ወዘተ ወደ 1000 ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጥያቄዎችንም አዘጋጅቼ ነበር።

 

ይህም ብቻ አይደለም ወላጆች እንዴት የልጆቻቸውን ህሊና በበጎ ማሰናዳት እንዳለባቸው፤ የወደፊት ራዕያቸውን ከውጥኑ አውቀው እንደምን መንከባከብ እንደሚገባቸው ቅደመ መሰናዶ „የተስፋ በር“ የሚል፤ በተጨማሪም የትውልዱ ብክነት አንዱ ያለተሳካ ጋብቻ ስለሆነም ባለትዳሮች እንዴት በተሳካ ትዳር የተሰካ ማህበረሰብ መመስረት እንደሚችሉ „ርግብ በርን“ መጸሐፍ ሁለት የምክር አገልግሎት መጸሐፍትንም ጽፌያለሁኝ። ታፍኖ ግን ለህዝብ እንዲደርስ ማድረግ አልተቻለም። ስቶር ያሞቃል። የ አላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መርዝ ነው ማላታይን ወይን ዲዲቲ ከመልካም ነገሮች ጋር በተጻራሪ የቆመ።

 

ለልጆች „ፍቅራዊነት“ በሚል የራዲዮ ፕሮግራም ሁሉ ጀምሬ ነበር። ያው እኔ ለመነሻ የሚሆኑ ነገሮች ጀማምሪ ቀጣዩ ትውልድ ግን በተባባሩት መንግሥታትን ላይ ጫና ፈጥሮ ይህን አስፈሪ ዓለም ወደ የተረጋጋ፤ ብሩህ ዓለም ለመለወጥ የፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች እንደ አንድ ኮመን ሳብጀክት በት/ቤት ደረጃ የሚሰጥበትን፤ ሙያ ሆኖ ተማሪዎች የሚመረቁበትን ሁኔታ እንዲኖር እንዲታገሉበት ነው የወጠንኩት። የመነሻ ሃሳቤ በዩቱቡ ላይ ይገኛል።

ለእያንዳንዱ ቻፕተር ምዕራፍ፤ ኮንፓክት እና ሳመሪ አለው። ስጀምረው ብዙም ጠንካራ አልነበረም አሁን ግን እዬጠነከረ መጥቷልኝ እኔም የመነሻ ሃሳቤን እያገባደድኩኝ ነው። ዕድሜ ከሰጠኝ ቀለል ያለች መጸሐፍ ለመጻፍ እሻለሁኝ። ታዲያ እናንተ ውድ ታዳሚዎቼ በሃሳብ ካገዛችሁኝ።  ካበረታታችሁኝ።

 

እኔማ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ደስታዬ ወደር አልነበረውም። እሳቸውንም ያወቅኳቸው በማይንድ ሴት ፕሮጀክት ስለነበር ተስፋዬ በሩህ ነበር። ለዚህም ነበር በ2017 ጀምሬ ስሞግትላቸው የባጀሁት። ግን አልሆነም። ነገር ግን ባሰብኩት ልክ መሆን ስላልተቻለ መልሼ እዛው ፓለቲካ ውስጥ ተዘፍቅኩኝ፤ እንጂ እኔ በዚህ ዙሪያ ብቻ ነው መስራት እምሻው …የነበረው። ክብረቶቼ ዓለማችን አትዮዋትም እንጂ ዘወትር ታለቅሳለች …. ሰው ትግሉ በጸርነት ከተፈጥሮ ጋር ሆኗልና።

 

ስለሆነም መንፈሱን ውዶቼ ሼር በማድረግ፤ ላይክ በማድረግ ሃሳብ በማፍለቅ ተባባሩት ሃሳቤን … 

 

የኔ የኔታዎች ውዴቼ አንድ ነገረ ልጠይቃችሁ እስኪ? እስኪ አንድ ታዋቂ ዩንቨርስቲ ወይንም ተቋም በዚህ ሥም የሚጠራ ታውቃላችሁ „መቻቻል፤ ተቀባይነት፤ ዕውቅና መስጠት፤ አዎንታዊነት፤ ተጠያቂነት፤ ምስጋና፤ ይቅርታ፤ ምኞት፤ ደግነት፤ ርህርህና፤ እርዳታ፤ መደማመጥ፤ መታገስ፤ አክብሮት፤ መስጠት፤ መቀበል፤ ማድመጥ፤ በራስ መተማመን፤ ፍቅር፤ ህይወት፤ ነፍስ፤ መኖር፤ ዕውነት፤ ኪዳን፤ ውል፤ መዝለቅ፤ ተጠያቂነት፤ ሚዛናዊነት፤ ሃላፊነት፤ አትኩሮት፤ ተመስጦ፤ መታመን፤ ታማኝነት ወዘተ … እኔ ሰምቼ አላውቅም …

 

ዓለም ሁሉም አላት ካለ ፍቅር ተፈጥሮ መርህ ተቋማት በስተቀር። ዓለም በዬዘመኑ ስንት ሚላርድ ዶላር ለጦር መሳሪያ ታመርታለች? ለፍቅር ተፈጥሮ መርህ ግን አንድ ቀን በዚህ ሁሉ ዘመን በአጀንዳ ደረጃ ውይይት ተደርጎበት አያውቅም። ጨካኞች የሚራሩት፤ በዳዮች ከበደላቸው የሚታቀቡት የፍቅርን ተፈጥሮውን በመርህ ደረጃ መማር ሲቻል ብቻ ነው። ይህ ማለት ሙሉ ለሙሉ 100 % ማሳካት ይቻላል ሳይሆን ቀውስ መቀነስ ግን ይቻላል። ዛሬ „አሸባሪ“ ነው ትናንት „ፋሺዝም“ ነበር ነገ ደግሞ  በአዲስ ሥም ሌላ ይመጣል። ልጓም የለም እና …

 

ሰው ስለሆን እንፈረዳለን እንጂ ወንጀለኞችን ወንጀል አንዲሰሩ የሚያደርጋቸው ከልጅነት ጀምሮ ሊሰራ የሚገባው ሞራላዊ ተግባር ስላልተከወነ ነው። ለመሆኑ የትኛው አገር ነው ልጆችን ስለ አገራቸው በህገ መንግሥቱ ስላላቸው መብት እና ግዴታ፤ ስለ ዓለም አቀፉ የሰብዕዊ መብት አስከባሪ ህግ ስለ 1948ቱ ኮንቤንሽናል እንዲማሩ የሚያደርገው።

 

የህግ ተማሪዎች ብቻ ናቸው የዬአገራቸውን ህግ የሚያውቁት። መሆን የነበረበት ግን እያንዳንዱ ዜጋ እንደ ዕድሜው ደረጃ ተመጥኖ የዬሀገሮችን የመነሻ ህግጋት አንቀፆችን ከሥር ጀምረው ተመረው ማደግ ይኖርባቸው ነበር። ሁላችንም። በዚህ ስሌት ስንሄድ አቤቱ ቦኮሃራም ሆነ አቤቶ ብላዲን ተጠያቂነታቸው እስከምን ይሆን? ስለነገስ> ?

 

ክብረቶቼ ዛሬ ይህን ፌስ ቡኬ ላይ ያጋራሁት ነው። ለብሎጌ ታዳሚዎች ምን ሲል ይቀርባችሁ ብዬ ነው። በዴሞግራፊ ላይ ያለኝ አስተያዬት አላለቀም። ያን መሰል ጹሑፍ ለመጻፍ የመንፈስ መሰባሰብ ስለሚጠይቅ እንደወረደ የሚሰራውን መጻፍ ነው ዛሬ የቀለለኝ።

 

በተረፈ መልካም ጊዜ በፍቅራዊነት ላይ የተሰሩት ኮንፓክቶች እና ሳመሪዎችን ከዩቱቡ በተጨማሪም በቅርቡ ከተከፈተው ቲውተር አካውንቴ ላይ ታገኙታላችሁ። ጭማቂውን ማለት ነው። 


https://twitter.com/SelassieSergute

SelassieSergute

 

 

ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።