ዛሬን የሚያኖረው ዛሬ ነው። ነፍስ ባለሥልጣን አይደለችም።


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

„ከርኩስ ነገር ንጹህን ሊያወጣ ማን ይችላል?“
መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፬

ተስፋ ይቀድማል
ተስፋ ያስቀደማል
ተስፋ ያስደምማል ነው።

ዛሬን የሚያኖረው ዛሬ ነው። ነገንም የሚያኖረው ዛሬ ነው። ነፍስ ባለሥልጣን አይደለችም።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
By Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
24.06.2019


ግን የእውነት አብዩ የጎንደር ጌጥ ነውን?
እራሴን ጠዬኩት እራሴኑ?

ዛሬን የሚያኖረው ዛሬ ነው። ነፍስ ባለሥልጣን አይደለችም።
ግን የእውነት አብይ የጎንደር ጌጥ ነውን? እራሴን ጠዬኩት እራሴኑ?
ዝም ብዬ 2017 ህዳር ላይ ሄድኩኝ።

በተስፋዬ ውስጥ የዶክተር አብይ አህመድን ስስት፤ ናፍቆት እንዴት ነህ ለማለት በሳቸው ዙሪያ ያቻልኩትን ያህል ከጻፍኳቸው ጥቂት ጹሑፎቼን ሌሊቱን ሙሉ አነበብኳቸው።

„አብይ የጎንደር ብቸኛው ጌጥ“ ስል የጻፍኩትንም ነጥዬ ደግሜ አነበብኩት። ተራራ ላይ ባንጠለጠሉት ምርኮኛ ጄኒራል አሁን የታጨውን ቦታም ቃኜት አደርጉት እንደዋዛ … ትዝብት ነው ትርፉ አሉ ፍሰኃ ለምለም ... 

ዋዘኞቹ እያዋዙ የልባቸውን እያደረሱ ነው። የጠ/ ጦር አዛዥነት እጩነት ወቼ ጉድ እለኩኝ። ጎንደርን ስላዋረዱ ብቻ ሳይሆን የምልዕቱ የመፈነቀሉን ጦስና የቋሳ እድምታውንም ፈታትሽኩት። ጄ / ብርሃኑ ጁላ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች አዛዥ ...ክፉኛ ቀፈፈኝ ...



ጎንደር „ሽፍታ“ ሲባል፤ በአዲስ አባባው ፖሊስ ኮሚሽነር ደግሞ ጎንደር እና ወሎ፤ ሌባ፤ ዘራፊ፤ ወንበዴ፤ ቁመርተኛ፤ የደረቅ ወንጀል መፈልፈያ ሲባሉ ዝምታቸው የጠ/ሚሩ እና አሁን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሊሆኑ ስለታሰቡት ምርኮኛ መኮነንን በትዝብት አዬሁት።

የጎንደር ጌጥነት በመስፈርት ሲለካካ ኑል ሆነብኝ። ይልቁንም ወደ ኔጌቲብም ተምዘገዘገብኝ። የዛሬው አብይ እኔ ያልመኩት አብይ አልሆንልኝ ብሎም ተቸግሬ ታምቅኩኝ። ዐነባሁኝ ...

ጠረኑም እምክ እምክ አለኝ። የኦሮሞ ፖቲካ ፍልስፍና ውስንነት እንዴት እንደ ለደመደበት ወሮ ዘቅዝቆ አቅምን እንደ ሰቀለውም አዘንኩኝ። 

ብዙ ነገር ነበራቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ብዙ በጣም ብዙ ምን ያደርጋል „ከአጋም የተጠጋች ቁልቋል ዘላለም ሲያልቀስ" ይኖራል ሆኖ እንዲህ የትንታ የብንታ ቤተኛ ሆነ። አንድ ዓመት ማሰቆጠር ሳይችል ቀርቶ ያለ አግባብ ባከን። ሰኔ 16 በታቀደ ሰኔ ዓመት ድገምም በታቀደ ህውከት። ሰው ገድለህ ለማትረፍ። ፉርሽ።

ለብቸኛ ጓደኛቸው ለዶር አንባቸው መኮነን እንኳን መሆን ተሰኗቸው ከመስከረም ጀምሮ አንሳፈው ሲደቋቸው ነበር የከረሙት ያም ይሁን ተብሎ አሁን ደግሞ መደመር በሰኔል ተውኔት በቹቻ መድረክ እንዲህ ውርድ በራሴ ተወራረደ።

በዚህ ውስጥ ገናናውን፤ ብሄራዊ ሉላዊ ጉዳዮችን አንስቶ ሁለመናውን መልክ ለማስያዝ የተነሳውን እነሱንም ለዚህ ቦታ የበቃው ያ ሞገደኛ ምክንያታዊውን የጎንደር አብዮት ጭንቃላት ውስጥ የወልቃይት እና የጠገዴ ጉዳይ እንዴት መጠራቀቅ ውስጥ ሆነ አሮጌ ዲሪቶ ተከናንቦ በአብይወለማ መንግሥት እንደ ተጀቡነም አሰተዋልኩት።

ባለቤት ያለው የኤጄቶ የድል አጥቢያ አርበኛው ጉዳይ ደግሞ እንደ ቀዳሚ አጀንዳ በምርጫ ኮሚሽን በቅድመያ እንደተያዘ የምርጫ ቦርድ አማካሪ ያሉትን ተደመምኩበት። "ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁት።"

„የአማራ ተጋድሎ“ ለማለት ድፍረት ጠፍቶ የፈሪውን ብዛትም በቦንዳ ለካሁት ብአዴንን ጨምሮ። ከዚህ ያፈነገጠው አንበሳ ደግሞ ዛሬ ተፈላጊ ወንጀለኛ ነው ብ/ ጅ/ አሳመነው ጽጌ። የአባቶቹን ቅርስ ወረሶ ሎሌ፤ ባሪያ አልሆንም ያለ።

እኔ ሥርጉተ ሥላሴም የኦነግ ተስፋ ጠበቂ ፍርፋሪ ለቃሚ ከምሆን አንድ ሞት አይደለም 90 ሞት ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ። አሻፈረን ያሉት ጀግናዎቼ ናቸው። ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በሃሳብ ልቅና ሙግት ቢሆን ግን ምርጫዬ ነበር። ግን ልዕልት አደማ መታበዩን አበዛችው፤ ልክም ደንበርም አጣች። በጣም ተጋፋችን ... "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላሉ ጎንደሮች። እትጌ አዳማ ልኳን ሳተች። 

የአብይወለማን ሌጋሲ ተሸክሞ የባጀ ባዕት ጦር አይደለም ዝንቡን እሽ ሊባል አይገባም። "በማን ላይ ቁመሽ" ሆነ ነገሩ ሁሉ ... ፖለቲካ ድርጅቶች ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ/ ተደማሪ የሚባሉትም መናህሪያቸው ያ ቀዬ ብቻ ነው። ለ ኣለመ አቀፉ ማህበረስ አይን ህሊና ማረፊያ። አሳታፊ እንዲባል ኢህዴግ። የ ኢህዴግን መከራ ተሸክሞ የኖረ ዛሬም ያለ ያ ባዕት ነው።

አሁን ልጆቹን እንዳያስተናግድ ነው ጦር የተዘመተበት። የባላደራስ ባልደረቦች ልጆቹ ናቸው። ጉዳዩ አናት ነው። ያን አካባቢ ነካክቶ ሰላም ባይታሰብ ይሻላል። ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል። ፍቅርም ሲያልቅ ትእግስት ይሰደዳል። አንድ አመት ከሁለት ወር ተሸከመ የኦነገን ንግሥና ...ያ መከራ የባጀበት ባዕት በመስቃ እዬተቆላ ... ቋያ። 

በ27 ዓመት ውስጥ የድመትን የእርግዝና ወቅት ብቻ የያዘው ለማሟያ ለሟሟቂያ ጊዜ ብቻ ቦታውን ለአቶ ንጉሱ ጥላሁን ለማስጠት ቆስቆሶ ለዚህ ያደረሰው ራሱ መንግሥት ነው።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ የዶር አንባቸው መኮነን ሹመት እና የጎንደር እናቶችን ፈተናም ከነዳሁት ከልብ ሆኜ። የጎንደር ፍሬ ስንት ጋሻ መሬት ለሰብል እንደበቃ ወይንም ከስሞ ቃርሚያ መረጋገጫ ብቻ ሆኖ የመስቃ መናኽሪያ ሆኖ እንደቀረ እኔና እናቴንም በምን እና በምን ሁኔታ እንደተለያዬን ዕንባዬን እያወረድኩ አወጋሁት።

ፍደኛውን መክሊቴንም አባብልኩት ሆድ እንዳይበሰው፤ ደስታ ከረሚሉ አቀረብኩለት ደስታ ከረሚሎው የቀለሚንጦስ ነው።

በዚህ ማህል የዶር አንባቸው አህቶች የእህት ልጆች ወጭ አገር የሚኖሩት ይህን መራራ ነገር እንዴት ሊያስተናግዱት እንደሚችሉም አሰታመምኩት። እኔ ብሆን ብዬ አሰብኩት። አብሶ ሩቁን ኒዊዘላንድን ሰማይና መሬት የተገናኙበት የአገር መጨረሻ ላይ ተሁኑን አሰብኩት። መራራ!

አለፍ ብዬም የጭልጋን እያንዳንዱን ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ስለማውቀው ወደ ላዛ ወደ ጅባንሰግ፤ በወ ገለድባ፤ ወደ ሰራባ፤ ወደ እሜቴ አይከልም ጎራ አልኩኝ፤ ለጥ ያለውን ተንከልምንም በዓይነ ህሊናዬ፤ ለጥ ያለውን ደንብያንም በእዝነ ልቦናዬ አሰተውዬ የዋይታ መንደር ሆኖ 100ሺህ ነፍስ የቋሳ፤ የበቀል መደመሪያ መሆኑ ውስጤን በእልህ ፈጀኝ።

የማውቀው ያ ሰው ብልቶ የጠገበ የማይመስለው የላዛ ገበሬ ሳይቀር እንዴት ወገኖችን አፈናቅሎ ሜዳ ላይ እንዳፈሰሳቸውም አወያዬሁት፤ በዘመነ አጤው በሲወዲን ተራድዖ ድርጅት የተሰሩት ዘመናይ ት/ቤቶች የተቃጠሉት፤ ተቃጥለው፤ የወደሙት ወድመው አሁንም ቤተኞቻቸው ተብትነው ማህበረ ወና ሆነው ወደ 44 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ወለል ላይ ሜዳ ላይ ፈሰው ብዕርና ብራና በናፍቆት ሲንጣቸው ...ዕንባ በዘላለማዊነት።

ዘመናቸው አንደኛው ዘመን አልፎ ሁለተኛው፤ ሁለተኛው በሶስተኛ ተተካክተው እንዲት እንደተቃጠልም ንግግር ቢጤ አደረግን ሁሎችንም ተረ በተራ ቤት ለእንግዳ እያልኩ በተዘናከተ ትህትን አወያየኋቸው።

አለፋ ጣቁሳ ጠመኔ አጥቶ የጠሜነ ያለህ ስለማለቱም በምልሰት እንዴት ሆነህ ይሆን አልኩት። የዳስ ት/ቤቶችም ዕጣ ፈንታ ዝቅ ብዬ ሰላምታ አቀረብኩኝ

በዘመነ ደርግ ህውኃት በጊዜያዊነት በሚቆጣጠራቸው ቦታዎች ቅናቱ፤ በቀሉ አይጣል ነው የመጀመሪያ ተግባሩ ት/ቤቶችም ማቀጠል ስለነበር እነዛ የተቃጠሉ ት/ቤቶች ቃጠሏቸውን ንብረት አድርገው እንዴት ደግመው ሳይሰሩ ፈልሰው እንደቀሩም ድንኳን ውስጥ ከእነሱ ጋር በምልሰት በሃዘን ተቀመጥኵኝ። ልዝ ቢጤ አሰናድቼ ስለነበር በዛው እዬተከዝን - አብሮነት።

የጎንደር እናት መቼ ይሆን ዪሚያልፍልሽ አልኩኝ? የወሎስ? የጎጃምስ? የሽዋስ? መቼም ለመቼ መልስ የለውም። መቼቱ ለጦርነት፤ ለመገነዝ „ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ“ መሆኑም ማህሌት አስቆምኩት ወደ ሱባኤ ልልከውም ተሰናዳሁኝ … ሱባኤ ሱባኤ የኖኽ መርከብን ፍለጋ …

ዛሬ ሰላምታው ዘገዬ ግርማዎቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ?
ትእግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል\ፍቅርም ሲያልቅ ትእግሥት ይሰደዳል።
ኑሩልኝ የኔዎቹ መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።