ይድረስ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሞት ከአማራህ ስለምን ወደ እቴጌ ትግራይ ጎራ አትልም?

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ

   በሰላም መጡልኝ።

 

ዕለተ ማክሰኞ ዕለተ ይግቡ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በሰብለ ህይወት አዝመራ

በቢሆነኝ ብራ

ለራህብ የሚራራ።



"ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው ይላል።"

(መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ 1 ቁጥር ቀጥር)

 

ይድረስ ለዴያቆን ዳንኤል ክብረት

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ።

 

ሞት የናፈቀው የቤተክህነት ሊቅ ሞት ካማረው

ለምን ወደ እቴጌ ትግራይ ጎራ አይልም?

ወይንም ለሱዳን ወደ ተሰጠው የጎንደር መሬት?

 

 




·       ዕፍታ።

 

አማራ ብሄርተኝነት ስብራት ላይ ማን ዘመተበት ቢባል ዴያቆን ዳንኤል ክብረት ነው። አሁን ተቆርቋሪ፤ እረኛ፤ ሰብሳቢ አልቦሾች በመደዳ ተረሽነው ሊሂቃን ምንጥር አሉለት አረፈ። አቅሉ ተረጋጋ። መዋያ ማደሪያው እዛው ነበር። እንደ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እሰቡ የኋሊት ዙሩ እያለ ይሰብክ ነበር።

ተዋህዶም ውርዴቷን በዓይነት ለእሱ ከረባት እና ገበርዲን ገበረች፤ ተገበረች። አሁንም ይህ ይቀጥል ዘንድ ደግሞ አለሁኝ ይለናል። ካድሬነት ወይንም ዲቁና? አንዱን መርጦ መሄድ ይቻላል። መብት ነው። በዥንጉርጉር ማንነት ግን አገር መታመስ የለበትም።

 በከበረው በዲቁና ሥም ማህበረ ምዕመናን ለእርድ ሥርዓት ሊቀርቡ አይገባም። አብይዝም የመቃብር ሥፍራ፤ ገዳ የሞት ኢንፓዬር ነው። ለፕሮቴስታትን፤ ለዋቄ ፈንታ ኢንፓዬር ግርዶሽነት የቁም ሙትነት ነው።

ለዚህ አሳለፊ እሆናለሁ ለአማራ የዘር ጭፍጨፋ አጋፋሪነት እስለፋለሁ ይቻላል ለጭካኔ ፈቃድ ስለማያስፈልገው። ተባጅቶበታል። በታውህዶ ስም ግን ቃር ነው። ቃ ያለ ገመና። ያ ሁሉ ሰማያዊ ጸጋ ለግል ምቾት እና ዝና ክምችት አርኬብ ሲሳናዳ ያሳፍራል።

 https://www.youtube.com/watch?v=5eE6PrrKZ70

„ለሃገሬ እንድሞት ይፈቀድልኝ“

Feb 25, 2021

10SHARESAVE

ማን ከለከለህ ጦርነቱ እኮ አላለቀም ለምን አትሄድም?

 https://www.youtube.com/watch?v=8kgWb-TLp9U

የምድራችን ዕውነት ይህ ነው" ከጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ።

Aug 5, 2020

30SHARESAVE

·     ውላቂንት እንደምን ይናፍቃል?

ለየኔታዋ ተዋህዶ እግር ብረት ነህ አንተ። ለየኔታዋ ታወህዶ አንተ የመቃብር ሥፍራ ነህ። ለተዋህዶ አንተ የጉሮሮ አጥንት ነህ። አለቅትም።

ዝም እምንለው እንደፈለገው ሆነህም ዱላውን፤ ንቀቱን፤ ውርዴቱን፤ በማህበረ ኦነግ ስናዳምጥ „የቤትህ ቅናት በላኝ“ ይዞን እንጂ አንተ የቅንጣት ታህል እዛ ቤተ - መንግሥት ተቀመጥህ ለየኔታዋ ተውህዶ ከቀስት ትድን ዘንድ የፈዬድከው አንዳችም ነገር የለም ከውርዴት በስተቀር። ቤቷን፤ ቤተ - መቅደሷን ከማስደፈር፤ ንዋዬ ቅድሳቷ ከማስነደድ በሰተቀር።

መቼም የሙርቅርቁ የገዳ ስሪት ያላወለቀው ሰብዕና የለም። ሞት ናፈቀኝ ይለናል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ደግሞ። አይሰማ የለም። ሞት ከናፈቀው ለምን በህወሃት እና በኦህዴድ የጥጋብ አታሞ ጦርነት ላይ ሳጅን አዋጊ ሆኖ አልተገኜም? አሁንም እኮ መሄድ ይቻላል? ከቶ ከአሜሪካ ሳይቀር የሄዱ የወልቃይት እና የጠገዴ ሰዎች አልሳማ ይሆን? ከማህል አገርስ? ካልሰማ እኔው ልንገረው።

ሌላው ያን ያህል ቤተ - እግዚአብሔር በሙሉ ኦሮምያ ሲነድ፤ የዶግ አመድ ሲሆን፤ በመተከልም ሲደገም፤ ምዕምናን ሲታረዱ፤ ሲሰቀሉ፤ ሲወገሩ፤ አካላቸው ለዱር እንሰሳ ሲሰጥ የት ነበር ሰባኪው? ጁቪተር ላይ? ሞት ካማረው? የሻሸመኔ፤ የአርሲ ነገሌ፤ የዝዋይ፤ የሐረር ሰማዕታት ቤተሰቦችን ሄዶ እንደ ጀግነቹ አይቷልን?

ፉከራው ቀረርቶ ቤተ - መንግሥት ሥጋጃ እንደማንጠፍ መሰለውን? ለነገሩ የማይጋፉት የአቡነ ጵጥሮስ ልጅ በሁሉም ብቃት ሙሉዑ የሆነ ደልዳላ የጨመተ ክስተት ምስባህክም ባልተሳበበት ወቅት ታማሩ የላይኛው አያልቅም እና ስለተከሰተ ነው ይህ ቃል የተደፈረው? ቤተ መንግሥቱም ንጠቱ ያ ነው። አትችሉትም ልዕቁን ጀግናውን።

ኢትዮጵያ ምርኮኛነትን የሚጠይፉ ልጆች እንዳላት ዘመነ አስተርዮ  በዓይናችን በብሌናች አሳይቶናል። አንተ ከያዝከው ከያዘከው ወንጌል ይልቅ እስክርቢቶ ያያዘው የዕውቀት የኔታ ፊት ለፊት ወጥቶ ቤተ - መንግሥቱን እዬተራመሰው አዲስ አጀንዳም እያሸከማቸሁ ነው።

·       አነይዝም አይሆኑ ሆነው ሞተዋል።

አብይዝም፤ ህዝቃዬሊዝም፤ አራርሳይዝም፤ ጃዋርዚም፤ አሰፋወጃለታይዚም፤ ለማይዝም፤ ጎንፋይዝም፤ ጉዲናይዚም፤ ሌንጮይዝም፤ ዳውዲዝም፤  በቀለይዝም፤ እንኩትኩቱን አውጥቶላቸዋል የጥቁር አንበሳ ልጅ።

ለመሆኑ „ኦሮሞ ማናው ብሏዋል?“ መልስ ካላቸው? „በህይወቴ የማውቀው የከበረ ዕውነት ቢኖር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ነው“ ብሏል አንበሳው። ይህም ብቻ አይደለም ተዋህዶ ስትደፈር ምዕምኑ „ዝም ሊል አይገባም“ ብሏል። „በምርጫ ካርድ ሊቀጣ“ ይገባል ብሏል። ኢትዮጵያ እሸት፤ ያልባለቀ፤ ድንግል፤ ጥቃት አውጪ ልጅ አግኝታለች። የ እኔ ድንግል ትጠብቀው እንጂ አለን እንድንል ችለናል። ተስፋም አግኝተናል።

የጎመዘዘው ዕውነት ሲደመጥ ነው ያዙኝ ልቀቁኝ ከኦዳ ቤተ መንግሥት እስከ አንጣፊ አሽከሮቹ ትርምስ የታዬው። የተደመጠው። „ሲለቁሽ ሜዳ ሙሉ ሲይዙሽ ጭብጥ“ የሚለው ዕውን ሆኖ የኦዳን ቤተ - መንግሥት በማግሥቱ ተመልክቻለሁኝ። ዳጥ በዳጥ ነው የሆኑት። ጥቃት አውጪ ሲመጣ።  ማርከሻ የመርህ፤ የዕውነት፤ የሥርዓት፤ የህግ ፈላስፋ ሲመጣ።

የት ይግቡ? ምን ይዋጣቸው እነ ሰበር? ማጥ እና ዳጥ መሆኑን ቤተ - መንግሥቱን የዕለቱ ዕለት ነበር እኔ የተረዳሁት። ቅድስት እናታችን ተዋህዶ ስትከስል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የከረባት እና የገበርዲን ጨዋታ ላይ ነው የነበረው። አጃቢነቱ ለዕብለቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ነበር።

·       ወንድማችን፤

እንደ አከበርነህ ብትኖር ምን አለ?

እንደቻልንህስ ብትቀመጥ ምን አለ?

ተመችትህን ይመስልኃልን?

ምስልህ ሲመጣ እንደምን እንደሚቀፈን እኔ ልንገርህ?  

የሞገሳው ተጠማቂነት ይልቅ የሰማዩ የሰጠህ ክብር ልዕልና እና ጥበብ ይበቃህ ነበር። አንተ እራስህ ተቋም ነበርክ እኮ። ይህ የግርዶሽ ቀጨር መጨሬ አንድ ቀን በበላይህ ይነዳል። ጠብቀው። ፈጣሪ አልተከፋብኝም ብለህ አትሰብ። የፈጣሪን ሥራ ከአንተ በላይ የሚያውቀው የለምና።

እንዳከበረነው ቢቀመጥ ምን አለ? እኔ እራሴ እኮ እሱን እንደ ሪፈረንስ ርግብ በር መጸሐፌ ላይ ጽፌዋለሁኝ። በወቅቱ የሞገቱኝ ነፍሶች ነበሩ። እኔ ግን በሚከሰሰብት እንጂ ሊወነጀል በማይገባው መልካም ሥራው ንክች ማድረግ አይቻልም ብዬ ፈጽሜዋለሁኝ። ያን ጊዜ ለህወሃት ማደር ዛሬ ለኦህዴድ ይከረፋል። በውነት ይጎፈንናል።

አሁን ደግሞ የቀረው የቅድስት ኦርቶዶክስ እርሾ ተሟጦ ይገብር ዘንድ የጉሮሮ አጥንት ሆኖ ከች ብሏል። ፈጣሪ አምላክ ሥራውን የሚሠራበት ቀን አለውና ፍርድ እና ዳኝነት ይሰጥበት ዘንድ ለእርሱ መተው ይሻላል ብዬ ዝም ብል ዘመናይነቱ በዛ።

ቤተ - መንግሥት ውስጥ ተሁኖ አይደለም ሞት ሊናፈቅህ የሚገባ። ሞት ወደ አለበት አውድ ጎራ ብሎ ነው። ድፍረቱ ወኔው ካለህ ድበረ ዳሞ ሲደበደብ በዕብሪት፤ አክሱም ምዕመናኑ እንደዛ መጠጊያ አልባ ሲሆኑ፤ ሲጨፈጨፉ፤ እንደ አንተ አይነትስ ሰማዕትነት የፈቀደ እዛ ሄዶ መማገድ ነው ፉከራው ቀረርቶ አይደለም የጀግና ውሎ። እዛው ከሳቱ ሄዶ እንደ ቅዱስ ዳንኤል መንደድን መፍቀድ ነው ሰማዕትነት። ቅብዕ ሰብዕና በላይኛው እንዴት እንደሚዳኝ እሱ ይፍረድበት። አሜን!

 

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  

 


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

09.03.2021

 

የዕብለት ወታደሮች ቋቅ አሉኝ።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።