የዶር ሲሳይ መንግሥቴ መርህን የማሳበድ ዕብደት።፡
እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ
በሰላም መጡልኝ።
ዕለተ ማክሰኞ ዕለተ ይግቡ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በሰብለ ህይወት አዝመራ
በቢሆነኝ ብራ
ለራህብ የሚራራ።
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው ይላል።"
(መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ 1 ቁጥር ቀጥር)
• ዕፍታ።
ዕለተ ማክሰኞ ባለቤት የሌላቸውን ማህበረሰቦች፤ አመክንዮዎች የምንዳስስበት ዕለት ነው። ዛሬ ኢትዮጵያዊው ህግም፤ ሥርዓትም፤ መርህም፤ ዕውነትም፤ ሰማያዊ ህግም ጥሰቱ አና ያለባት ቅድስት አገር ኢትዮጵያ ተክዳ ያለውን የልብጥ አታሞ የኩሸት መጪነት በጥቂቱ ማዬት ይገባል ብዬ አሰብኩኝ። ቅጥፈቱ ግልምት አለኝና። ሰብዕናው ሙሉ ቅጥፈት ሲሆን ከማዬት በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር ይኖር ይሆን? ከረፋኝ!
• ዕርዕስ።
ታላቅ የህግ ባለሙያ በሥርዓት አልበኝነት በህግ ጥሰት፤
በዕውነት ጥቅጠቃ፤ በመርህ ተራጋጭነት በልቅነት ጎዳና ላያነጋ።
ዕርሴ ይሄ ነው። በዘመነ ህዋህት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የህግ ተቋማት ለምን አይከረቸሙም፤ ዩንቨርስቲዎችስ ለምን አይዘጉም ብዬ ጽፌ ነበር። ደጉ ዘሃበሻም አትሞልኝ ነበር።
ለምን? ብላቸውሁ ብትጠይቁኝ ህግ በኢትዮጵያ መረጋጋጫ ስለመሆኑ ስላስተዋልኩ ነበር ያንን ኃይል ጦማር የጻፍኩት። በተቃጠለ ካርቦን፤ አገልግሎቱን በጨረሰ ባትሪ አገር እንሆ አሁን እዬታመሰች ነው። ፍርጃ ለመታረጃ!
ዶር ሲሳይ መንግሥቴ የዘመነ ህወሃት የአደራ ልጅ ናቸው። ይህም ሆኖ ላደምጣቸው ከምፈቅዳቸው ወገኖቼ አንዱ ሆነው ቆይተዋል። ሙሉውን ቃለ ምልልሳቸውን እዬተከታተልኩ አደምጣለሁ ባልልም ስችል ስችል ግን አዳማጣለሁኝ።
እኔ ማንበብ ነው እምወደው። ይህም ብቻ ሳይሆን በጹሁፌ፤ በራሴ ምልከታ እና በህይወት መርሆቼ ላይ የሌላ ነፍስ ተጽዕኖን ለመከላከል እንደራሴ ለመኖርም ስለምፈቅድ ብዙም አላዳምጥም።
ምክንያቱም የማደምጠው ነገር ተጽዕኖ ያሳድርብኝ እና የእኔን ጸጋ እጫነዋለሁኝ፤ የሌላ ሰውን መክሊት እንድከወን እገደዳለሁኝ። አሰልችም ይሆናል ለታማደሚዎቼ። እራሴ እኔ የራሴ አለኝ። ተውስት የሚአስኬድ ነገር የለም።
መረጃ አለን ሲሉ ካልሆነ በመደበኛ ውይይትን አልከታተልም፤ ትንተናንም አላዳምጥም። በመደበኛ እምከታተለው ዜና ብቻ ነው። ለዛውም ዜናው ዕንባን ካወያዬ። የቅጅ ቅጅ ካልሆነ ከዛው ከተጎጂው የሚመጣ ድምጽ ከሆነ ብቻ።
• ቧልተኛው የህግ ሊሂቅ የቅጥፈት ዳንስ ምት?
የሆነ ሆኖ ዶር ሲሳይ መንግሥቴ የተማሩትን፤ ክብር ያገኙበትን፤ የድካማቸውን ውጤት በቤንዚን አርከፍክፈው ያቃጠሉት እኒህ የህግ ሰው አዲስ ቧልት ይዘው ብቅ ብለዋል። ይህ ቧልታቸው እልፈኝ ሊበላ አይገባም እና በልኩ ሊሞገት ይገባል። ተጨመላለቁብን። ኢትዮጵያም የሰው ድርቀት ማዕት ወረደባት። ጥቃት የሚወጣም ጠፋ።
የመገለ ቀልድ ሲበዛ ይከረፋል። የገዳ ልዕልቷ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ ያሰወገዱትን አስወግደው፤ የሰረዙትን ሰርዝው፤ ዲስክርምኔሽን የፈጸሙበትን ፈጽመው፤ አለቃቸውም የስሜን ፖለቲካ አፈር ድሜ አስግጠውላቸውም ይህም ውጤት ሊያመጣ አልችል ሲል፤ ማጣፊያው ሲያጥራቸው የፌስቡክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ለቀማ ላይ ናቸው። ልብጥ ሂደት፤ ውልቅልቅ ዝግመት። ዝገት በውይበት!
እሳቸውም ለነገሩ ሉላዊ የህግ ሰውነት ያላቸው አንቱ ነበሩ። አንቱታው ካለልኩ የተለጠጠ ነበር መሰልኝ ከበዳቸው እና ሰባራ ገል ሆኑ እንጂ። ከከንቱነት ጋርም በተክሊል ጋብቻ ፈጸሙ። እኛን ትተው አዲሱን የክህደት ጋብቻቸውን ፈጸሙ። ያልታደሉ።
ኮመዲያኑ ዶር ሲሳይ መንግሥቴ „ብልጽግና አይደለሁም ብልጽግና ወክዬ እወዳደራለሁ“ ይላሉ።
ማህከነ!
እግዚኦ!
ተሳህለነ!
ይቀር በለን!
አሜን ወ አሜን! ለይኩን ወ ለይኩን!
በሰውዬው አገላለጽ ከአራት በላይ የፈጣሪ ጸጋዎች በድፍረት እና በማን አለብኝነት ድጠዋል።
(1) መርህ!
(2) ዕውነት!
(3) ሥርዓት!
(4) ህግ!
• ቁጥር 4 የሰማያዊ ህግ ጥሰት።
ዶር ሲሳይ መንግሥቴ ምድራዊውን ብቻ ሳይሆን ሰማያዊውንም ቃል እንዳሻቸው ረጋግጠውታል። ጨፈላልቀውታል። ምናባህ አገባህ ብለውም ደብድበውታል። ህግ መማራቸውም ለገኃዱ ዓለም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሆኗል። ለመንፈሳዊ መኖር አመክንዮም።
ምን አልባት ከምርጫ በኋላ አቃቢ ህግነት፤ የፌድራል የህግ መቀመጫ ወንበር ፍርፋሪ ቃል ተገብቶላቸው ይሆናል። ነገር ግን ከዛ በፊት ፈጣሪ ሊሠራው ያሰበውን አያውቁትም። በህይወት ላይኖሩም ይችላሉ። ነፍስ የሰው የዳንቴል ውጤት አይደለችም እና።
ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ ፰
„መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፤ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ንስር ይመጣል። እነርሱም። አምላክ ሆይ፥ እኛ...። የሕጌን ብዛት ጽፌለታለሁ፤ እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጥረውታል። መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፤ እግዚአብሔር ግን አይቀበላቸውም...“
· መጽሐፈ ነህምያ ምዕራፍ ፲
„አኪያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥ መሉክ፥ ካሪም፥ በዓና። የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ሕግ... ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የጌታችንንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ፍርዱንም ሥርዓቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እርግማንና...“
· „መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፩
አቤቱ፥ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ። እዘምራለሁ፥ ንጹሕ መንገዱንም አስተውላለሁ፤ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ። በዓይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርሁም፤ ሕግ ተላላፊዎችን ጠላሁ። ጠማማ ልብም አልተጠጋኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅሁም። ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን...“
· ትንቢተ ሚልክያ ምዕራፍ ፪
„ደነገጠ። የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበረች፥ በከንፈሩም ውስጥ በደል አልተገኘበትም፤ ከእኔም ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙ ሰዎችንም ከኃጢአት መለሰ። ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል። እናንተ ግን ከመንገዱ...“
· ትንቢተ ሚልክያ ምዕራፍ ፬
„እግዚአብሔር። ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ። እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን...“
· ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ ፬
„በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ልጆችም... ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል። ስለ እናንተ አመነታለሁና አሁን በእናንተ ዘንድ ሆኜ ድምፄን ልለውጥ በወደድሁ። እናንተ ከሕግ በታች ልትኖሩ የምትወዱ፥ ሕጉን አትሰሙምን...“
• ምርኩዜ ይህ ቃለ ምልልስ ነው።
https://www.youtube.com/watch?v=VerbN7cIV6I
Ethiopia #Ethiopianews #AbbayMedia
መስመር ላይ - ለብልጽግና እወዳደራለሁ፣ የብልጽግና አባል አይደለሁም|ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ - የህግና ፌደራሊዝም መምህር |
Ethiopia |Abbay Media
• ቁጥር 1 ቁጥር ቁጥር 3
የመርህ እና የሥርዓት ጥሰት
በጋህዳዊ መኖር ዕድምታው ሲፈተሽ።
„ብልጽግና“ የሚባል ፓርቲ የለም። አልተፈጠረም ሳይሆን አልተጸነሰም። ያለው የህውሃት ውራጅ እና ጉራጅ የኢህዴግ እንጥፍጣፊ አሰርውሃ ነው። የህውሃት ጭላጭ ነው። በአንድ ጫኝ መኪና መጥቶ ወደ ሌላ የጭነት መኪና የተገለበጠ ውራጅ የትውስት ቤተኛ ነው አባሌ የሚሉት የኢማጅኔሽን ኤክሰፐርቱ … ዶር አብይ አህመድ አሊ።
· ለዚህ ተጨማሪ ጹሑፍ መጻፍ አልስፈለገኝም።
ከዓመት በላይ የሞገትኩባቸውን ጹሑፎች መርህዊ ስለነበሩ በፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ ላልበቀሉት ወይንም ለሳቱ ወይንም ለወለቁት ለዶር ሲሳይ መንግሥቴ ህሊና ድርቅ ስለመታው፤ ወይንም በአንበጣ መንጋ ስለተወረረ ለጥፌዋለሁኝ።
እኔ የዛሬ ዓመት የኢማጅኔሽን ተረበኛው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የእኔ መርህ 50/60 ዓመት ይገዛል ሲሉ ያረጠ ብዬ የሞገትኩት ዕውነትነቱ ግን ሳይውል ሳያድር ታዬ አደባባይ። ሰው ስሌለው ልመና ላይ ነው።
ለነገሩ ተስጥዖዋቸው ልመና መሆኑን ጠቅላዩ ነግረውናል። ሁሉ ነገር ለምኖ በተገጣጠመ የሰባረ ገል ኦርኬስተር ታላቋ አገር ኢትዮጵያ ክልትምትም ማለቷ ግን ያሳዝነኛል። በጣም። ገንዘብ ተለምኖ፤ ድጋፍ ተለምኖ፤ ተወዳዳሪ ተለምኖ፤ ድምጽ ተለምኖ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተለምኖ፤ ሚስት ተለምኖ? አገር አይችለው የለ የኮረኮንች ኩርንችት። ከርዳዳ!
(1)
https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post_29.html
2019 ዲሴምበር 29, እሑድ
የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ {ዘለግ ያለ ሙግት ከምርጫ ቦርድ ጋር}
(2)
https://sergute.blogspot.com/2020/01/5060.html
50በ60 ያረጠ ፖለቲካ።
(3)
https://sergute.blogspot.com/2020/01/blog-post_63.html
2020 ጃንዩወሪ 4, ቅዳሜ
የጨረቃ ቤት {ብልጽግና} የመርኽ ጥሰት እና ልብዱ ስብሰባ።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት የአደረጃጀት መርህም ሥርዓትም አለው። አንድ አባል የሌለው የፖለቲካ ድርጅት ዓለም አስተናግዳ አታውቅም። በውራጅ ቀዳዳ፤ በተብተከተከ አባላት እና አካላትም' በተጨማታተረ አካላትም ፓርቲ አዲስ ሆኜ ተፈጥሬያለሁ ሊል አይችልም። ፈጽሞ።
ያለው በጠቅላይ ሚኒስተሩ ህሊና ያለ የኢማጅኔሽን ዳንቴል ቅራቅንቦ ነው።
የዶር. ሲሳይ መንግሥቴ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ልክ "እናቴ ስኳር ግዛ ብላ ስትልከኝ መኪናዬን አስነስቼ፤ ቡቡ እያልኩኝ ድምጽ እያሰማሁኝ፤ ሱቅ ስደርስ ፓርክ ላይ አቁሜ፤ ሱቅ ሄጄ ሱካሬን ገዝቼ፤ ከፓርክ ያቆምኩትን መኪናዬን አስነስቼ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ።"
"ስተኛም ሰኔሉን አንጥፌ የደብርብርሃን ብርድ ልብስን ሳለብስ እያጠፍኩን አንሶላ አንድ አንሶላ ሁለት እያልኩ አንጥፌ እተኛለሁ። እናቴ መኬና እንዳለኝ፤ እንሶላ እንዳላኝ ኣተውቅም። እኔ ግን ነበረኝ“
በእቃ እቃ ጨዋታ ነው አሁንም ፓርቲ አለኝ የሚሉት። ብሄራዊ ጉባኤ፤ ማዕክላዊ ኮሜቴ፤ ሰነድ፤ ቁጥጥር ኮሚሽን፤ ኦዲት ኮሚሽን፤ ፖለቲ ቢሮ የሌለው የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሱቅ በደረቴ ነው „ብልጽግና“ እዬተባለ የሚላገጠው።
በእሱ ውስጥም የለሁም በሌለሁበት እና በሌለ መንፈስም አለሁ ብዬ እወዳደራለሁኝ ይሉናል ቧልተኛው አዲሱ የ ዕብለት ሪከርድ ሰባሪ፤ የጥሰት የአሸናፊዎች አሸናፊ ዶር ሲሳይ መንግሥቴ። የጃርት ፖለቲካ። ሙጃ እሳቤ ለዛውም የጠነዘለ - የታመከ ሙጃ እሳቤ። ለከብት መኖ እንኳን ሊውል የማይችል ዕምል።
አካል የሌለው፤ ሥርዓት የሌው፤ ሰነድ የሌለው የቅዠት አታሞ ነው "ብልጽግና"
ገዳ ነው ያለው። ይህን በመቀላላቀላቸው የህግ ሊቃውንቱ¡ ባለሙያው ውረዴነት ይሸለማሉ። ሰብዕናቸውን አለ ለማለት አልችልም እኔ ከዚህች ዕለት ጀምሮ። በመንፈሴ ቀብራቸው ተፈጽሟል። ከለሉት ጎን በውርዴት ተንቆጥቁጠው ተቀብረዋል። አዬ ይህ ዘመን እንደምን መነጠረን? ያሳዝናል።
• ቁጥር 2 ዕውነት።
በዚህ ዘመን እንደ ዕውነት እና ደግነት ስደት ላይ ያለ አምክንዮ የለም። የማባጨለም ልክ አለው። የቀልድም ልክ አለው። „የብልጽግና ፓርቲ“ አይደለሁም፤ ብልጽግናን ወክዬ እወዳደራለሁ“ ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በላይ የዕውነት ሞት የለም። ከዚህ በላይ ዕውነት በአደባባይ የተረሸነበት ዘመን አላዬሁም።
ሰብዕን እንዲህ የተልባ ስፍር ሲሆን እንደምን ያ ገበርዲን እና እና ከረበት ጨርቁን ጥሎ እንዳላበደ አላውቅም። ልበሳቸው አላውቅህም ብሎ ዲሞ መውጣት ነበረበት ገባርዲኑም፤ ከረባቱም። ወይ አማኑኤል ወይ ድግሞ ጎንድ ተክለ ሃይማኖት መሄድ ነበረበት።
ያቺ እቴጌ ሚስትዬም እንደምን ታቅፋ እንደመትተኛ? ዝልብነት ባል እንዴት ሊሆን ይችላል? ስለምንስ ሚስት መሪ አትሆንም ለሰባራ ገሉ እንቶ ፈንቶ ምኞት? አባትነቱም እንደምን እንደሚከውን ግራ ይገባል። በዚህ ውስጥ ትውልድ ሊገናባ? ወይ ቀልድ? ጭው ባለ ገደል የገባ ሰብዕና ብቻ ሳይሆን ለዘር ሽራፊ ያልተረፈለት ስብርባሪ። መራራ ስንብት ...
በዘመኔ ስኖር አንዲህ ዓይነት የተቃጠለ ሰብዕና አይቼ አላውቅም። እኔ ብዙ ሰው ነው እማውቀው። በተለያዩ የህይወት አጋጣሚወች። እንደዚህ ያለ የተቀደደ ሰብዕና ግን አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ለመሆኑ የፓርቲ አባል ሳይሆን ለፓርቲ ውክልና ውድርድር በማን ውክልና? ማን በሰጠው የውክልና አቅም? እፍረትም ለካ ወግ አለው? እርቃኑን የቆመ ሰብዕና ነው የሚታዬኝ። የሌላ። ባዶ አብዶ!
የጠጅ ተርቲም ወይንስ የጠላ ተርቲም፤ ወይንም የቡና ተርቲም መሰላቸው ይሆን የፖለቲካ ድርጅት አመሰራረት፤ አወቃቀር እና አደረጃጀት እና ውክልና? እንደምን ያለ ዝልቦነት ነው? እንደምንስ ያለ አዚፋነት ነው? እንደምንስ ያለ ዝልግልግ ላንቁሶነት ነው? እንደምንስ ያለ እንኩቶነት ነው?
የማፈሪያነትም እኮ ልክም ደንበርም፤ ወሰንም አለው። የወራዳነትም መጠን አለው። አንዲህ ያለ ውልቅልቅ ያለ፤ ጭምልቅልቅ ያለ፤ ጮፍራራ ...
.... እንደዚህ ያለ ዝብርቅርቅ ያለ ገመና ነፍሴ መሬት ረግጣ ነፍስ ካወቅኩበት ዕለት ጀምሮ አላዬሁም። አለስማሁም። ከእሳቸው እና ከአለቆቻቸው ማህበረ የሞጋሳ ደራጎን በስተቀር። ማህበረ ማፈሪያ! ይደበቁቁቁቁቁቁቁቁቁቁቀ!
እኔ በእንቆቆው የገዳ ምርጫ ዳንኪራ ምንም ላልል አስቤ ነበር። ዝም ሲባሉ ግን ክርፋታቸውን አንጠልጥለው ዓውዱን በመርህ ጥሰት፤ በዕውነት ጥሰት፤ በህግ ጥሰት፤ በዕውነት ጥሰት ያግማሙታል። ይህን እያዬሁ ዝምታ ደግሞ ኩነኔም ነው።
የዶር ሲሳይ መንግሥቴን ገፃቸውን ማዬት እራሱ እንደ ኃጢያት ነው የቆጠርኩት። ያቅለሸልሻል። ቋቅቅቅቅቅቅቀ!!!!!!!
ምርኮኝነት እንደምን ይቀፋል? ብዙወቹ በማንነት ቀውስ የሚገኙ ናቸው እንደዚህ ቅርቃር ላይ የተቀረቀሩት። ቢበቃወትስ ምን አለ? ለወጣቶች ዕድሉን ቢሰጡስ? እንዲህ ረግረግ ውስጥ ረግረግ ለመሆን ባይፈቅዱ። ጨቀጨቅ ውስጥ ጨቀጨቅ ሊሆኑ ባይፈቅዱ ምን አለ፧ {}
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergut©Selassie
09/03/2021
የወራዳ ውረዴት ከረፋኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ