" Evita-Kult in Argentinien"

 

ንኳን ወደ ከበቡሽ

ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

 

„ምስጉን ነው በክፉወች ምክር ያልሄደ

በኃጢያቶኞችም መንገድ ያልቆመ

(መዝሙር ምዕራፍ 1 ቁጥር አንድ።)

 

ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ

በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

በቢሆነኝ ብራ

ለራህብ የሚራራ።

 







 

· ዳማዊ እምቤቷ አርጀንቲናዊቷ የተግባር ልዕልተኢቫ /ኢቢታ/ ህይዋን/ማርያ ፔሩን ማን ናት?

 

· በዝቀተኛ የኖሮ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያ ወጣቶችስምን ይማራሉ?

 

ዳማዊት እምቤት ኢቫ ፔሩን አርጀንቲናዊ የጥበብ ሰው፤ የፖለቲካ ሰው፤ የቲያትር እና የፊልም አክተር፤ የሙዚቃ ተጫዎች የነበረች ድንቅ እጹብ ድንቅ የመብት ተሟጋች የነበረች ሴት ናት። በዘመን ማሀከል አንድ ጊዜ ብቻ የምትፈጠር።

አርጀንቲናዊቷ ቀዳማዊት እመቤት ኢቫ / ኢቢታ ፔሮን/ ከመካከለኛ ቤተሰብ ከጋብቻ ውጪ የተወለደች ልጅ ነበረች። እሷ በኖረችበት ዘመን ይህ እንደ ነውር ይታይም ነበር። ኢቫ ፔሩን ገና በጥዋቱ ነበር መንገድ ላይ የወጣችው። ከዛም በጾታዋ መተዳደር ጀምራም ነበር።

ዕድል አጋጣሚ ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ቁልፉ ተገኜ እና ወደ የቲያትር ትወናው ዓለም ተቀላቀለች። የቲያትር ትወና ከአርቱ ሁሉ የተለዬ ነው ለእኔ። ከህዝብ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ የጥበብ አውደ ምህረት ነውና። ከታዳሚው ጋር ቋንቋው ገጽ ለገጽም ነው። እርምቱም ሐሤቱም እንዲሁ። የጓዳ ግንኙነት የለውም።

 

ዳማዊ እመቤት ኢቫ ፔሮን ከዛም ወደ ራዲዮ ጋዜጠኝነት ተሸጋገረች። ድንቋ አዛኝ እና ሰው ወዳጇ እመቤት ኢቫ በጣም የሳባት የትግል መስክ የሴት ሠራተኞች ብቃት፤ ክህሎት በህግ ያላቸው የዕውቅና መኮሰስ ወይንም መክሳት ነበር።

 

ሴቶች በእጅጉ ያሳዝኗት ነበር። ስለዚህም በሴት ሰራተኞች ትግል ውስጥ ተግታ መሳተፍ ጀመረች። በዚህ ሂደት ውስጥ ነበር የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ዮን ፔሮን የተዋወቀቻቸው።

ይህቺ ድንቅ ፍጹም የሰማይ ጸጋ ዕድሏን አለፈሰሰችውም።

 

ብቻውን ተቀበል ለመክሊቷ አዲስ ጎዳናን ቀዬሰችበት።

ቀዳማዊት እመቤት ኢቫ ጥሩ ማህንዲስ፤ ጥሩ አደራጅ፤ ብቁ ተዋናይ፤ የወጣላት ተናጋሪ፤ ተግባቢ፤ ልብ አንጠልጣይ የራዲዮ ዝግጅት እና ተዋናይ ሳቢ ባልደረባ እንደ ነበረች ታሪኳ ይመሰክራል። ለዛም ነው እጅግ ባጠረ ጊዜ እዚህ የመጨረሻው እርከን ደረጃ የደረሰችው። ዕድገቷ ፈጣን። ውጤቷም ታምራዊ ገድል ነበር።

 

ርቲስቷዋ ቀዳማዊ እምቤት ቤተ መንግሥት እንደ ገባች በቀጥታ የሥራዋ መጀመሪያ ያደረገችው የሴቶችን ተራጋጭ ህግ ተወግዶ የሴቶች እኩልነት ህጋዊ መሰረት እንዲያገኝ ማድረግ ነበር። ይህን በድል አጠናቀቀች።

 

ዚህም አላቋመችም በአገሯ በአርጀንቲና አዲስ የሴቶች እኩልነትን የሚያረጋግጥ ማህበራዊ ንቅናቄ በተከታታይ እና በትጋት በራሷ መሪነት አደራጅታ ጀመረች።

 

ማህበራዊ ንቅናቄ ከህግም በላይ ሃይማኖታዊ እንዲሆን አደረገች። ለዚህ ነው መንፈሳዊ መሪ እስከመባል የደረሰችው። ቅባዕው የነበራት ሴት ነበረች። ቅባዕውን ደግሞ አስከበረችው። በጣም ውስን ሰዎች ናቸው ዕድላቸውን በወጉ ተጠቅመው አገራዊ ፋይዳ የሚፈጽሙበት።

 

ዳማዊት እመቤት ኢቫ ፔሮን ሴቶች እኩል ናቸው ከወንዶች የሚል ህይዋው መንፈስ በመላ አርጀንቲና ህዝብ አሰረጸች። የአርጅንቲና ህዝብ ከልቡ አደመጣት። መርኋን ጠጣው። ከደሙ ጋር አዋኃደው። በውስጡም አተመው። ተወዳጅነቷ ወሰንም ደንበርም አልተሰራለትም ነበር።

በዘመኗ በእያንዳንዱ ቀን በዝቀተኛ የኑሮ ደረጃ ላሉ ለህፃናት፤ ለልጆች፤ ለሴቶች፤ ለወጣቶች፤ ለሠራተኛ ሴቶች ጠበቃ፤ ተሟጋች በመሆነ ከጥበብ ሥራዋ ጋራ ፊት ለፊት ወጥታ ተጋፈጠች።

 

ርቲስት ኢቫ "ድህነትን አትሰቡት" ሳይሆን ሴቶች ድህነትን መቋቋም እንዴት እንደሚችሉ፤ በተለይም የአስተሳሰብ ድህነትን ጥሰው እንዴት ሊወጡ እንደሚችሉ በህይወቷ ጨምር ሐዋርያ ሆና አስተማራች፤ ሰበከች፤ ሆነችበትም። ጀግና!

 

ዚህም የፖለቲካ ልዕልናዋ እዬጎላ፤ እዬጎለበተ፤ እዬጎመራ ሲመጣ ከባለቤቷ ጋር በመሆን ለአገሪቷ ምክትል ፕሬዚዳንትነት እጩ ሆነች።

 

ርጀንቲና ከጽንፍ አስከ ጽንፍ እልል አለ። ታዲያ ምን ይሆናል ካንሰር የሚባል በሸታ ለዘርም ሳትበቃ ታይታ ሳትጠገብ፤ የፖለቲካ መሪነት በሙሉ አቅም ድርጊት ላይ ለማወል የነበራት ራይ ሳያሰብል ሞት ቀጠፋት።

 

 

ዛን ዕለት ለህዝቡ መርዶውን ለመንገር እጅግ ከባድ ነበር ይላል የህይወት ታሪኳ። በዛን ዕለት በመላ አርጀንቲና በአበባ መሸጫዎች ሁሉ ለዘር አበባ አይገኝም ነበር ይላል ዝክረ ታሪከ የቀዳማዊት እመቤት ኢቫ ፔሮን። ትንግርት ነበረች ይላል ታሪኳ። ጥበብም ነበረች ትባላለች።

 

ዳማዊት እመቤት ኢቫ አልሞተችም። የተግባር ልዕልቷ፤ የሁለገብ ሥጦታ እመቤቷ ኢቫ ተግባሯ በመላ አርጀንቲና፤ በመላ አውሮፓ፤ በመላ ዓለም የተናኜ ነው። ፈረንሳዮች፤ እንግሊዞች አውታራቸው ናት።

 

ርመኖች በበርሊን የቲያትር ቤት በሥሟ ሰይመዋል። እኔም ለጥፌዋለሁኝ። ጀርመኖች ዕውቅና ለመስጠት ስስታም አይደሉም። በጣም እጅግ በጣም ስልጡን እና ለጋስም ናቸው።

 

ንግሊዞችም ተመሳሳይ የማስተዋሻ አሻራ አስቀምጠውላታል። በአገሯ በእርጀንቲና የተለያዩ ፋውንዴሽን በመጠነ ሰፊ ሁኔታ ተቋቁሟዋል። ከሁሉ የሚለቀው ግን የማህበረሰቡ የህሊና ለውጥ እጅግ ድንቅ ነው። ቋሚ ሥራ ነው የከወነችው። እያንዳንዱ አርጀንቲናዊ ዜጋ ለሴቶች እኩልነት እራሱ ተቋም ነው።

 

ርጀንቲና ውስጥ አንድ ተባዕት ልቆ ከወጣ ሴት ጓደኛው፤ ሴት አማካሪው፤ እናቱ፤ እህቱ፤ ሚስቱ የሰጡት የብቃት ሥጦታ ነው ተብሎ በጽኑ ይታመናል። በመንፈስ ሥር ነቀል ለውጥ የአርጀንቲናን ያህል የለም ይላሉ ተወላጆች።

 

ዚህ አውሮፓ ሲመጡ በአንዳንድ ነገር እንደሚገረሙ አጫወተውኛል። ለምሳሌ አርመን በሴት አያያዝ ላይ በህግ የተደገፈ ጠንካራ ተግባር ይከውናል። የአርጅንቲናው የሚለዬው ህግ ብቻ አይደለም የህዝቡን ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ለውጥ ያመጣው።

 

ህበራዊ ለውጡ በቀዳማዊት ኢቫ ፔሮን ቀለማም የህይወት ተመከሮ ያሰበለ ንቅናቄ በህዝብ ሙሉ ፈቃድ በውስጡ የታተመ መሆኑ ነው። ይህ ድንቅ ተግባር በዬትኛውም ዓለም ያልታዬ ብርኃናማ የኢቨይዝም ላብይዝም ናቹራሊዝም ሂውማኒዝም የተግባር ፋና ነው።

 

ዳማዊት እመቤት ማሪያ ኢቫ በአመዛኙ በተጋችበት መስክ ከቲወሪ ያለፈ ሁለገብ ሰበነካዊ፤ ተፈጥሯዊ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ፈጽማለች። ፍቅር ነው የነበረችው። ህግም ነው የሆነችው። ፖለቲካዊ ሪቮልሽን አካሂዳለች። አሳካታለችም።

 

ንደ እኛዎቹ ላይ ወጥተው ታች እንደሚሉት አይደለችም ቀዳማዊቷ እምቤት ኢቪታ ፔሮን። የእኛዎቹ የህዝብ ፍቅር ባገኙ ቁጥር እንደ / ብርቱካን ሚዲቅሳ ማበሻ ጨርቅ አይሆንም የህዝብ ፍቅር እና አክብሮት። መታበዩ ነው እኔን የገለማኝ። እኛው ላይ አንጠልጥለን። እኛው እነረጋገጣለን።

 

በቧ ኢቫ ግን የህዝብን መዋለ ፍቅር ለቀለማም ህብራዊ ድርጊት ነው ያዋላችው። በሳባዕዊ መበት፤ በቲያአትር፤ በፊልም፤ በሙዚቃ፤ በሠራተኛ ማህበራት፤ በአስተዳር ልዩ ህብራዊ አርት ነው የፈጠረችው። ዓለምን ያስደመመች የተደሞ ሚስጢር።

 

ንገድ ላይ ልጆችን፤ የከፋቸውን ለማግኜት በጣም እጅግ በጣም ቅርብ ነበረች። የድሆች እናት ነበረች። ድህነቱን ስለኖረችበት ለውጡን በድርጊት ለማስጌጥ አልተቸገረችም። እርግጥ ነው ድህነቱን ኖረውበት ግን "ድህነትን አትሰቡት" የሚሉ እኛ ቅምጥሎችም ይገጥማሉ።

 

ዳማዊት እመቤት ማርያ ኢቫ ፔሮን ግን ልዩ የድርጊት ዓይነት ዓይንም ነበረች። የህሊናም ብሌን። የጆሮ ልባም ህሊናም።

 

እጹብ ድንቋን ፈርጣም ዕንቁዋን ኢቫ ፔሮን አንስቼ የእኛን የኢትዮጵያን የሴቶች የፖለቲካ አቅም፤ አብሶ ሰባራ ገሉን የአብይዝምን ካቢኔ እና እንኩቶ መዋቅሩን ለሴቶች ዕንባ፤ ለወጣቶች ሰቆቃ፤ ለህጻናት ስቃይ፤ ለሰው ልጅ መታረድ፤ ለቀንበጥ መታገት፤ ለወጣት ሴት ፖለቲከኞች መታሰር፤ መረገጥ፤ መሳደድ ያለውን ገመና፤ ለሴቶች ክህሎት ያለውን ጥበቃ ሳስብ መቃብር ቤት ይሆንብኛል። ከዚህ በላይ ባልሄድ ይሸለኛል።

 

https://en.wikipedia.org/wiki/Eva_Per%C3%B3n

María Eva Duarte de Perón (née María Eva Duarte;

7 May 1919 – 26 July 1952

 

ርጀንቲናዊቷ ቀዳማዊት እመቤት ማርያ ኢቫ ኢቫ /ኢቢታ / ህይዋን/ ፔሩ አርጀንቲናን በህግ ለውጥ ሳይሆን በህሊና ሥርዓታዊ ማህበራዊ ለውጥ ነው መሰረት ያስያዘችው፤ በማይነቃነቅ የማህበረሰብ ግንበታ ያነጸች ዕጹብ ድንቅ ናት። ፍጹም ዕጹብ ድንቅ።

 

ቀዳማዊት እመቤትነቷን በተግባር ያረጋገጠች የግሎባሏ ልዕልት ኢቫ ፔሩን የተሳከለት ድንቅ አርቲስት፤ ተናፋቂ የፖለቲካ ሰው፤ እጽብ እንቁ የድሆች እናት፤ ታማራዊት የሰብዕዊ መብት ተሟጋች እና የራዲዮ ጋዜጠኛነቷን በተግባር አስመስክራ አንርጀንቲናን በሴቶች የዕውቅና የከፍታ እርከን ማማ ላይ በዘላቂነት ያሰቀመጠች የጌጦች ጌጥ፤ የፈርጦች ፈርጥ ድንቅ ሰው ናት።

ኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች በዬትኛውም መስክ፤ በዬትኛውም የኑሮ ደረጃ ይሁን ባገኙት ዕድል መጠቀም እንዳላባቸው የአርቲስት ኢቫ ፔሮን የተግባር ሰውነት ያሳያል።

 

ተለይ በኑሮ ከዝቀተኛ ቤተሰብ የተፈጠሩ፤ መንገድ ላይ በድህነት ምክንያት የወጡ፤ በችግር ምክንያት ፆታቸው መተዳደሪያቸው የሆኑ እህቶቼ፤ ልጆቼ ምንም ተስፋ ሳይቆርጡ ከተጉ እግዚአብሄር ከተገፉት ጋር ነውና እና ለቀኑ ቀን የሰጠው ዕለት የመኖራቸው ቁልፍ የዓለም ማሾ ሊሆን ይችላሉ።

 

ለዚህ ሳይዘናጉ እያንዳንዱን ነቁጥ የዕድል በር ይጠቀሙበት ዘንድ አጽህኖት ላሳስብ ነው ዛሬ ይህን ጉዳይ በዝርዝር ማንሳት የፈለግኩት።

 

ዳማዊት እመቤት ማርያ ኢቫ ብዙ ናት። ኢቫ ሚሊዮን ናት። ከአፍሪካዊት አገር ኢትዮጵያ መጥቼ ፍጹም አክባሪዋ ነኝ። ሁልጊዜ አዘክራታለሁኝ። ሥራዎቿን አነባለሁኝ።

አደምጣለሁኝ። ምስሏ ቤቴ ውስጥ ሁሉ አለ። ስለምን? ተግባሯ ቋሚ የማህበሰብ ለውጥ ብርኃን ስለሆነ።

 

ደም ብዬ እንዳነሳሁት በሴቶች ዙሪያ ከምመሰጥባቸው አገሮች አንዱ አርመን ነው። አርመን በሴቶች ዙሪያ ጠንከር ያለ ሥርዓት የዘረጋ አገር ነው። ትጋቱም መዋቅራዊ ነው።

የድንቋ የኢቪታ ግን የሥርዓት ለውጥ ብቻ ሳይሆን በሴቶች አመለካከት ላይ ደንቃራ በነበሩ የአስተሳሰብ ለውጦች ላይ ህዝባዊ ማህበራዊ የንቃተ ህሊና አብዮት ነበር ያካሄደቸው። ያሳካቸውም።

 

አርጀንቲና የሴቶች ጉዳይ ሳስብ፤ አውሮፓንም ሳስ ከዚህ ያለውን የግንቦት 7 አረሟሟዊ አመራር በንጽጽር ሳስተወለው ገና ሰው ሆነው አለመፈጠራቸው ይደንቀኛል።

 

ርጀንቲና የት ላይ ደርሷል እነሱ አንድ በራሷ የግል ጥረት በነፃ ህዝባዊ አገልግሎት የምትሰጥን ባተሌን ዕጣ ነፍስ ሴት አግር እግር እዬተከታተሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲያጠለሹ ውለው ያድራሉ። እጭነት። አገር ገብተውም አያርፉም። ያምሳሉ። ያተራምሳሉ።

 

እዛ በራሳቸው ጊዜ የበቀሉ አንስት ሰብሎችን ለካቴና ያሰጣሉ። አንዲት ዘር አብቅለው አስብለው ማውጣት አልተቻላቸውም። የበቀለ ከመንቀል በስተቀር። ድውያን።

 

https://www.youtube.com/watch?v=KD_1Z8iUDho

#OfficialMusicVideo #Madonna #DontCryForMeArgentina

Madonna - Don't Cry For Me Argentina [Official Music Video]

Spiritual Leader Of The Nation: Eva ‘Evita’ Perón Of Argentina

https://theculturetrip.com/.../spiritual-leader-of-the.../

ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ ይከወን።

ውዶቼ 2021/2013 ዓለም ዓቀፉ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ያሰናዳሁት የዕለቱ መሰናዶ በዚህው ተጠናቋል።

መሸቢያ ጊዜ።

 

ኑሩልኝ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

08.03.2021

ብቁ ሴቶች ሞግዚት አያስፈልጋቸውም።

ባለ ተስጥዖ ሴቶች ሐረግ አይደሉም።

ባለ መክሊት ሴቶች የአስተሳሰብ ጥገኛ ለመሆን አይፈቅዱም!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።