#እንኳን ደስ አለህ ቦረና! ኢትዮጵያም ታድለሻል። አይዞሽ!
እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
እንኳን ደስ አለህ ቦረና! ኢትዮጵያም አለልሽ!
ዕለተ ሃሙስ ማዕዶተ አሰጋሪ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል"
(ምሳሌ ፲፯ ቁጥር ፱)
#እንኳን
ደስ አለህ ቦረና! ኢትዮጵያም ታድለሻል። አይዞሽ!
#ዛሬ
ማዕዶተ አሰጋሪ የፀጋዬ ቀን ነው።
ኢትዮጵያ ያለችበትን ምስቅልቅል አስቤ፤ ልዩ የውስጤ ሊለው የሚችል ልጅ ማግኜቱን ሳስብ እፅናናለሁ። ብላቴው አልሞተም። እራሱን ተክቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድንግሉ መንፈሳቸው የጠቅላዩን ቢሮ ሲናጥ አስተውላለሁ። ምልከታዬንም አቀርባለሁኝ።
#ዬጠቅላይ
ሚኒስተሩ ቤተ መንግስት ንጠት የላይኛው በሰጠን የእኛነት ድንግል ልዑል ምክንያት ነው። ደንግጠዋል።
ታስታውሱ ከሆነ አብይዝም፤ ለማይዝም ጉዲናይዝም ሌንጮይዝም በቀለይዝም ጃዋርይዝም ታዬይዚም አራርሳይዚም ህዝቃኤልዚም ጉዳቸው ፈላ ብዬ ከደን አድርጌ ፅፌያለሁ። የሆነው ይህ ነው።
1) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተወዳዳሪ ሆኖ የመጣው። ያ የፈጣሪ ቅባዕ ያለው ፀጋ በተዋህዶ አማንያን ላይ ሊኖራቸው የሚገባ ግልፅ አቋም ስለታወጀ ነበር። የኔታዋ ያልሠራችው ነበር የተከወነው። ያ የፅዋ ቅዱስ ውይይት ላይ አስታውሳለሁ አቶ ጎዳና ያዕቆብ ቢያስፈልግ "እኔ እራሴ ሄጄ ድምፅ እሰጣለሁ"
ብለው ሁሉ ነበር። Feb 11;2021
2) አንድ በተለያዬ ሙያ ዕውቀት ያለው የጠቅላዩ አማካሪ ወጣት ተወዳዳሪ ሆኖ የወጣው ምክንያትም አቶ ጎዳና ያዕቆብ ባላቸው ዕውቀት ልክ እኛም አለን ነው። ወጣቱን እማከብረው እማዳምጠው ልጅም ነው የጠቅላዩ አማካሪ። የኢትዮጵያ ልጅ "በህይወቴ እማውቀው ትልቅ ዕውነት ቢኖር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ነው"
ይህ ሥጦታ ሁለገብ ዕውቀት ከጭምትነት ጋር ያላቸው ናቸው። ያ ድንጋጤ ነው የጠቅላዩ አማካሪ ለእጩነት የተሰዬሙት።
3) በዓድዋ ድል መታሰቢያ እኒህ የላይኛው ስጦታ አቶ ጎዳና ያዕቆብ ባሠፈሩት አጭር ፁሁፍ የእቴጌይቱ ሃውልት ይሠራል ብለው አደባባይ ሲወጡ ኦሮምያ ለእቴጌይቱ ሃውልት በጀት መመደቡን አዳመጥን።
4) "ከኦሮሙማ፤ ከመደመር፤ ከፍኖተ ብልፅግና፤ ከኮንፊዩዝድ ኮንቢንስ፤ ከቁማር፤ ከላሟ፤ ከሰበርናቸው፤ ከሰው እንበላለን፤ ከወራጅ የለም፤ ከፌስታል ፖለቲካ፤ ከወዘተረፈ የድንገቴ ሱናሜ የቀውስ ባጀት፤ ተወጥቶ" "ሰቦውያን ነን" ትርክት አዳመጥን። ሰቦ የሚለውን እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሉን ያዳመጥኩት አቶ ጎዳና ያዕቆብ ከጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ጋር ባደረጉት ውይይት ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ ያዳመጥኩት በቅርቡ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ተገኜ አቶ ብሩክ ተሾመን እና አቶ ጎዳና ያዕቆብ ጋር ባደረጉት ውይይት የኦሮሞ ጥላቻ አለባችሁ ይሉናል ሲል
"እኔ የቦረና ኦሮሞ ነኝ ሰቦ" ሲሉ አድምጫለሁ።
ግንዱ ዋርካው በጭምትነት በድንግልና በፋፋ የዕውቀት አቅም የላይኛው ሲሰጥ ድንጋጤ ሆነና ኦነጋዊው ኦህዴድ ዕሴታችን ፍኖታችን ሰቦዊነት ነው ተባልን። ይህን ተርጉመው ያስነበቡንም ቅኑ አቶ ጎዳና ያዕቆብ ናቸው። እሳቸው ሰቦ ነግሦ እንዲወጣ ያስደረጉት ምክንያታዊ አቅም እሳቸው መሆናቸው የገባቸው አይመስለኝም። እኔ ግን ገብቶኛል። እነሱ ሲያቆላምጡ የኖሩት፤ አቶ ጃዋርም በባዶ እግሩ የሄደለት ከሚዲያ ውጭ ጠቅላዩ የእጅ ሰዓታቸውን ለጨረታ ያቀረቡለት አንቦ ነበር። የአንቦ አቅም ፀጋን አውቀዋለሁ። የፀጋዬ ቤት ቤተኛ ነኝና።
አንድም ቀን ስለ ቦረና ሰቦ ሰምተን አናውቅም ድፍን ሦስት ዓመት ሙሉ። የጠቅላዩ መንፈስ ህውከት ላይ ነው። የጠፋው የቁቤ ትውልድ መዳኛው ቅርብ ነው። Oct
22/2020 ከጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ጋር፤ Mar
21/2021 ከዬኔታ ዲያቆን አባይነህ ካሴ ጋር የጋዜጠኛ ብሩክን የፖለቲካ ብቃታዊ አቅም ያዬሁበት ዕለት ነበር።
5) ኦሮምዬ ስለአማራ መጨፍጨፍ ድንኳን መጣሉን ሰማን። አቶ ታዬ የሃዘን መግለጫ አወጡ። አጤ ዝናቡም እስተ ቢሯቸው አወጡ መግለጫ። ይህን ሰው ለምን ሆነ ብሎ ያስተዋለው አይመስለኝም። ለዚህ ነው እንደ ጥሩ ነገር ያዬው፥ እንደ ስላቅ የተመለከተውም አለ። ዕውነት ከተደፈረ፤ መርህ ከተደፈረ ይህ እንዲሆን ያስደረገው የአቶ ጎዳና ያዕቆም የህሊና ንፅህና አቅም ነው ብዬ ነው እማስበው። ይህ አቅም ከተለመደው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንድርቺ እንድርቺ የወጣ ነው። ምስባክ ነው። ክስተትም።
6/7/88……… ይቀጥላል ጠብቁት።
የ ኦህዴድ መግለጫ ሆነ የጠቅላዩ ልሳን የተፈፀመው ተገደው ነው። የማይቋቋሙት መካች ዕውነት ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ስለሰጣት።
ይህን አቅም መኮረጅም መክደንም መፎካከርም አይቻልም። የሰው የእጅ ሥራ ዳንቴል አይደለም እና።
የላይኛው ሥጦታ በጥንቃቄ ቢያዝ፤ ዕውቅና ቢሰጠው፤ በተገባው ልክ አክብሮት ቢሰጠው፤ ሊደመጥ ቢፈቀድ፤ ለሁላችንም ከቀስት እንድንበት ዘንድ የተሰጠን እናታዊ ተስፋ ነው። ስለተጎዱ ስለሚሰቃዩ ተስፋ ስላጡት ሁሉ እኔ ባዳመጥኩት ውይይት ሁሉ ያዬሁት ጭምታዊ እናትነትን ነው። ክድን አድርጌ ኢትዮጵያ ለተመድ ዋና ፀሐፊነት የመወዳደር አቅም አገኜች ብዬ ሁሉ ፅፌያለሁኝ።
የትግራይ እና የፌድራሉን ጦርነት ሲሉ በሥሙ ከመጥራት ጀምሮ "ትግራይን ለማበልፀግ"
የሰሜን ፖለቲካ ለመስበር፤ ተዋህዶን ለማድከም" አሉ። እሳቸው ማስታመም አያውቁም። ጦርነቱን በሚመለከት ወጥ አቋም የነበረን ጋዜጠኛ ኃብታሙ አያሌው ጋዜጠኛ ማዕዛ መሃመድ አቶ ጎዳና ያዕቆብ እኔ ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ፀጋዬ አትራፊ እንዳልሆነ ወጥ አቋም ነበረን። ያልነው ነውም የሆነው።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ትምህርተ ጎዳና ጨካኞችን ሁሉ እዬገራ ስለመሆኑ እያስተዋልኩኝ ነው። "አብይ የሥልጣን እንጂ ኢትዮጵያ ፈርስት ነው" ላሉትም
"ከማህበረ ኦነግ የተለዬ አይደለም"
ብለው ሞግተዋል። "ተረኝነት" ለሚሉትም
"ከተረኝነት በላይ" ነው ብለው ሞግተዋል ጠቅላይ ሚኒስተሩን
"እርስዎ"
ይበሉ የሚል አስተያዬት ገጥሟቸው ይመስለኛል በእኔ ሥም ለሚፈፀም ጭካኔ ዕውቅና አልሰጥም ሲሉ እንቅጩን ተናግረዋል።
ለቀኑ ቀን ሲሰጠው የቀኑ ችግር ቁልፍ ቀኑ ይሰጠዋል ያልኩት እዬተፈፀመ ነው። እኔ ሳስበው የጀግና አበበ ገላው የሬገን ህንፃ ነጎድጓዳማ ድምፅ ኢሳትን ትንሳኤውን እንዳወጀው ሁሉ የመጀመሪያዋ ቀን የጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ቃለ ምልልስ ከአቶ ጎዳና ጋር የተዘጋበት በር አስከፍቷል ኢትዮ 360 የተመሠረተበት ሚስጢር የተገለጠበት ዕለትም ማለት እችላለሁኝ። የOct 22/2020
እሳቸውን ስታዳምጡ ኮርስ ላይ የተቀመጣችሁ ያህል ይሆናል።
"የቃል ኪዳን ሰነድና ምርጫ"
Feb 19/2021 ሁልጊዜ አዲስ እሸት ነው። ጥያቄውንም የመወያያ መድረኩን አስከብረውታል። አወያዮቻቸውን እምለምነው በረባ ባረባው አያቋርጧቸው።
ማወያዬት ሙያ ነው። ኤቲክስም ነው። ለኦዲዬንሱም ክብር መጨነቅ ይገባል። ባለፈው በፅዋ እማስታውሰው "አገር ማፍረስ እና መመሥረት" ላይ ነበር የተቋረጡት። ሁለት ቀን እራሴን አሞኛል። ዓለም ያላወቀው አመክንዮ ነበር የተነሳው። ግን ተጨነገፈ። አቶ ጎዳናም አልተመለሱበትም። ሃሳባቸው ተበተነ። ለዛውም የኔታ ዲያቆን አባይነህ ታጋሽ እኮ ናቸው።
መክሊትህን ምርቃትህን የሰማይ ሥጦታህን በጥንቃቄ ካልያዝከው ይነጠቃል። አቶ ጎዳና ያዕቆብ ለእኔ የኢትዮጵያ መክሊት። የኢትዮጵያዊነት ምስባክ። የኢትዮጵያ ክስተት ናቸው። የደነገለ ያልባለቀ ጭምት ፀጋ። ከሁሉ የልቅናው ልክ ከዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር አብረው አልሠሩም። ይህ ሽልማት ነው ለትውልዱ።
ጎዳናን እንማረው። እናዳምጠው። እናዋህደው። አይዞህ እንበለው። በዘመን መካከል የሚሰጥ ምርቃን ነውና። ተስፋ በእግሩ መጥቷል ላኪው የላይኛው ነው ቀለባችን ነውና እንቀበለው በተጠረገ ልቦና። መካች ጥቃት አውጪ አፅናኝ ፈቃዱ የላይኛው ነው።
ህብራዊነት መዳኛ ጎዳናችን ነው። ጎዳናዬ ትምህርተ ጎዳና ነው። ፖለቲካችን ንፅህና ያስፈልገዋል። ለዛ ያልባለቀ መንፈስ ተሰጥቶናል። ለእኛ ብቻ አይደለም ለአህጉራችን ለዓለማችንም። ታቦቴ ብሩኬ ብሩክ ቅዱስ ሁንልኝ። አሜን። ቅዱስ ሃዲድ ስለዘረጋህ። ፈጣሪም ይወድኃል። ሚስጢር ተገልጦልኃል እና።
• ከትምህርተ ጎዳና የወሰደኳቸው አገላለጾች በጣም በጥቂቱ።
• „ሽመልስን ብንቀበለው // ብናምነው ይሻላል“
• „ዛሬ ያለውን ኦሮሞነት እኔ አላውቀውም“
• „በህይወቴ የማውቀው አንድ የከበረ ዕውነት ቢኖር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው“
• „ዛፍ እንኳን ሲመለመል አባቶች ከልጆች ጋር ይሄዳሉ“
• „ጥጃ እንኳን ሳትጠግብ ወተቱ አይታለብም“
• „ሰው ወደ ላይ ያድጋል እንጂ ወደ ቁልቁል“
• „መሬትን ተጠንቅቀህ እንድትረግጣት ነው የሚነገርህ“
• ፕሬዚዳንት ቡሽን „ደደብ ባልለውም የአዕምሮ ውስንነት“
• „ነፃነት የህይወት አጥር ናት! እና ነፃነት ስጠኝ የሚልህ መንግሥት ነፃነትህን ከሰጠኸው በኋላ ህይወትህን መውሰዱ አይቀርም“
• „የአብይ ምዕመናን፤ የአብይ መዘምራን“
• „ሰው ለተፈጥሮ የሚገባው ሆኖ እንዲኖር ምን እናድርግ?“
• „አንተ ተበድለህ መንግሥት ሲፈጽመው ፍትህ ይሆናል አንተ ስትፈጽመው ደግሞ በቀል ይሆናል።“
• „ኦሮሞ ማነው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው“
• „ጦርነቱ ትግራይን በበልጽግና ለማበልጸግ ነው“
• „የምናከብረው ሰው አሳጡን“
• „የምናዬው ነገር ከተረኝነትም በላይ ነው። እኛ እንኑር እናንተ አኗኗሩን ነው“
• „በጣም እማፍረው አስተካክለው ማበላሸት ሲያቅታቸው ነው“
• „ኢትዮጵያ ሁሌም ረቂቅ ሚስጢር ናት፤ የታምራት አገር ናት“
• „የፖለቲካ ፓርቲ ህዝብ የለውም ማህበራዊ መሰረት ሊኖረው ይችላል። የፖለቲካ ፓርቲ አባላትም እንጂ ህዝብ የለውም“
• „የተፈጥሮ ህግ መሰረታዊ አመክንዮዎች ሦስት ናቸው“
• „በመንግሥት እና በህዝብ መካከል የሚገባ ማህበራዊ ውል የለም“
• „ሰዎች ሁለት ነገር አላቸው። እንደ ፍጡር ማህበራዊ ናቸው። አብረው መኖር መፍቀዳቸው ማህበራዊ (አኒማል) አድርጓቸዋል።“
„ህገ መንግሥት እና ህግ ልዩነት አለውን?“ የጋዜጠኛ ብሩክ ጥያቄ ነው ይህ።
„ኖ ይሄ በእኛ ህግ መንግሥት የሚባለው ነገር እንዳልኩህ መንግሥት ማድረግ የማይቻላቸው ነገሮች፤ በብዙ የሚተነትን ነው። የማይገረሰሱ መብቶች፤ የሰብዕዊ መብት ነፃነቶች፤ የጠቅላይ ሚኒስተሩ ሥራ እና ሥልጣን እና ተግባር፤ የህዝብ ተወካዮች ሥልጣን እና ተግባር፤ ባስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መደረግ የሚችሉ ነገሮች ተብሎ መንግሥት መሥራት የሚችላቸው ነገሮች ሥልጣን ገደቡ ፤ የሥልጣን አጥሩ የተበጀበት ነው። ለመንግሥት የተጻፈ ነው። መንግሥት መሄድ የሚችልበትን እርቀት የሥልጣኑን ጥግ እና ወሰኑን የሚያብራራ ነው። ለህዝብ የተጻፈ የሚመስላቸው አሉ ብዙ። ጠቅላይ ሚኒስተሩም ባንድ ወቅት፤ ይህ ህገ መንግሥት የሚሰጠውን የመናገር መብቶች አና ሌሎች መብቶች ላፍ እያደረጉ፤ ይህ ህገ መንግሥት አይወክለኝም ማለት የሚያስኬድ አይደለም ብለዋል። ይሄ ሎጅካሊ ስህተት የሆነ አካሄድ ነው። ህገ ምንግሥት ለእኔ የሚሰጠኝ መብት የለም። የመናገር መብት ከተፈጥሮ የሚገኝ ነው። የማሰብ፤ ሰው የሚፈልገውን ነገረ የማመን መብት ከተፈጥሮ የሚገኝ ነው። የህይወት የንብረት መብትም እንደዛው። ለዛም ነው የማይገረሰሱ የሚላቸው። ስለዚህ እኔ ይህን ብዙ ጊዜ ይሄን ነገር ህገ መንግሥት የሚባለውን ነገር መንግሥት ሲጠቀመው የምታዬው ህዝብን ለማጉላላት፤ ተቃዋሚን ለማሰር እና ሌሎች ሌሎች ለማድረግ ሲፈልግ ነው። አንድ ማሰተዋል ምን አልባት ያልቻሉት ነገር ግን በዛ ሁሉ ውስጥ ያ ህግ የተጻፈው እናንተ ከተጻፈው አትለፉ ያላችሁ ድርሻ መሄድ የምትችሉበት እረቀት እስከዚህ ነው ብሎ መንግሥትን የሚወስን ነው። ወደ መንግሥት የሚጠቁም ነው እንጂ ወደ ህዝብ የሚጠቁም አይደለም። በህገ - መንግሥት ላይ አለ አላለም መንግሥት ላለህ የመናገር መብት ዕውቅና ይሰጣል እንጂ ኦር ህገ -መንግሥቱ ይሰጣል እንጂ መብቱን አይሰጥህም። የምለው ነገር ግልጽ ከሆነ። ስለዚህ ወደ ህዝብ የሚያይ ሳይሆን ወደ መንግሥት የሚያተኩር ነው። መሄድ የምትችለው እስከዚህ ድረስ ነው። ይህ ነው ቦታህ። ይህ ነው የሥራ ድርሻህ። ይህ ነው የሥራ ክፍፍልህ። በዚህ በዚህ መልኩ ነው የምትሠራው፤ በዚህ በዚህ መልኩ ነው ወደ ሥልጣን የምትመጣው፤ እስከዚህ ድረስ ነው መሥራት የምትችለው። ለምሳሌ አሁን ስለፕሬዚዳንቷ የተጻፈው፤ ስለ እርሰ ብሄሯ የተጻፈው አንቀጽ ላይ ለ6 ዓመት ነው የአገልግሎት ዘመናቸው ከሁለት ጊዜ በላይ መመረጥ አይችልም ይላል። ይህ ከህዝብ ጋር የሚገናኝ አይደለም። አንድ ፕሬዚዳንት ለምን ያህል ጊዜ መመረጥ እንደሚችል፤ ምን ያህል ማገልገል እንደሚችል፤ ከዛ በኋላ ምን ማድረግ እንደማይችል የተጻፈ ነው። የጠቅላይ ሚኒስተሩ ሥልጣን እና ተግባር ተብሎ የተጻፈውም እንደዛው ነው። ስለፌድሬሽን ምክር ቤቱም የተጻፈው እንደዛ ነው። ስለ ህዝብ ተወካዮች እንደዚህ እያልን ብንሄድ ወደ ህዝብ የሚያመለክት ሳይሆን ወደ መንግሥት ይሄ ነው ድርሻህ፤ ይሄ ነው ሥራህ፤ ይህ ነው ሥልጣንህ ይህ ነው ገደብህ የሚሉ ናቸው። ለዛም ነው ህገ መንግሥት እንጂ ህገ ህዝብ ያልተባሉት ነው የእኔ ሙግት „
ምርኩዝ።
https://www.youtube.com/watch?v=FMxS7xJZKXQ
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ዲፕሎማሲ እና የውስጥ አሰላለፍ #Getaneh_Kassahun
#Godana_Yacob
https://www.youtube.com/watch?v=Y18gJNIH9to&t=763s
በሰብአዊ መብት ኮሚሽን “በትግራይ የተደረገው የጦር ወንጀል ተብሎ መመዝገብ አለበት” አቶ ጎዳና ያዕቆብ #Godana_Yacob
https://www.youtube.com/watch?v=LoAAA5wFj5o&t=298s
Ethio 360 Special Program የቃል ኪዳን ሰነድና ምርጫ ! Friday Feb 19, 2021
https://www.youtube.com/watch?v=gmmxY1RLzP0
Ethio 360 ሁለንተናዊ ዕይታ "ጦርነቱ እና የኢትዮጵያ መፃኢ እድል" Sunday Nov 22, 2020
https://www.youtube.com/watch?v=Ll4BqFtAZlk
Ethio 360 Special Program "መንግስት ህወሃትና ኦነግን ለምን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ ከበደው? " Thursday Nov 12, 2020
https://www.youtube.com/watch?v=VjXiWIDXYCw
Ethio 360 Special Program የኢትዮጵያ ፓለቲካ ወዴት እየሄደ ነው? Thursday Oct 22, 2020
98,077
views
•Streamed
live on Oct 22, 2020
1.5K130SHARESAVE
እዬተከታተላችሁ ማድመጥ ኢትዮጵያን የማዳን ጎዳና ነው።
ይህን እምጽፍላችሁ ኦነጋዊው ኦህዴድ ወዶ አይደለም ሃዘን ተቀመጥኩ ብሎ መግለጫ ያወጣው። የ አቶ ጎዳና ያቆብ አቅም እያደናበራቸው ነው። "እራሱ ማነው ኦሮሞ" የሚለው ጉልበታም አምክንዮ የ50 ዓመት ህልማቸውን አይሆኑ ነው ያደረገው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/04/2021
ጎዳናዬ የኢትዮጵያን ትንሳኤ መሻት ነው።
ጎዳናዬ ሰውኛ ተፈጥሮኛ ሥርዓት በአገሬ እንዲሰፍን መፍቀድ ነው
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ