አንዲት መንገድ አለች ከምድረ በዳ ውኃ የማታስለምን። የአቤልዕንባ ጠብታ። አብን የአማራው አቤል ድምፅ ነው።

ንኳን ወደ በቡሽ ሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልን።

 

አንዲት መንገድ አለች ከምድረ በዳ ውኃ የማታስለምን። የአቤልዕንባ ጠብታ።

አብን የአማራው አቤል ድምፅ ነው።

አብን የስለትም ልጅ ነው።

"እግዚአብሔር በአንድም በሌላም

ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"


 

 

#ጠብታ

የንገረው አዲስ ድምፅ ጎጃም፤ ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም ወለጋ፤ እናቴን ድውድው አደረጓት ደቡብ ጎንደር፤ ወዋ ጎቤ እና ቲሙ፤ ስንቱ ደመ ከልብ ሆኖ የቀረ የአማራ ደም ይጮኃል።

ከዬት እንደምጀምር አመናታሁኝ። እርዕስ ጽፌ መፃፍ አልችልም። እርዕስ ቢሰጠኝም አልችልም። አካል ከሌለው ቃለ ወንጌል ልነሳ።

#ቤት አፍርሶ መንገድ ላይከመውደቅ ፈጣሪ ይጠብቀን። አሜን።

የአዲስ ድምጽን ተከታታይ ቃለ ምልልስ ጥሩ ጊዜ እዬመረጥኩ አዳመጥኩት። ጥሩ ውይይት ነበር። በሳል ልጆች አብን አለው። የሰከኑ መንፈሶች አይቻለሁኝ። ቲምሊደር ላይ ይሆን ችግሩ ብዬ አሰብኩኝ። እሱ ብቻ ሳይሆን #የአሳቸው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ንጥቂያም አለ። የመንፈስ ዘረፋ። የአቅጣጫ ቀያሽ ምህንድስና። እራሱ አማራ ብሎ መጀመሩ አይመቻቸውም።

#በቃ ማሰብ።

ምክንያቱም አማራ ምን አለው?

ማን አለው? ዕውነቱ ምንም፤ ማንም ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለውም ይሁን እተካለሁ የሚለውም ይሁን በቁጥር አንድ ለአማራ ህዝብ አንዲት መንገድ ብቻ ናት ያለችው። ጥብቆ መንገድ። ያም አብን ተሟሙቶ ማስቀጠል። ለእነሱ ሰርጋቸው ነው። የአብን አለመኖርን ሁሉም የዪ።ሚፈልገው ነው። ለጋሱ አማራ የወንዝ ዳር አሽዋ አይደለምን?

እርግጥ ነው አሁንም ከገዳ ሥርዕወ መንግሥት መዳፍ ውጪ ይሆናል ብዬ ተስፋ አላደርግም። መንግሥት አይደሉም። ልምድም፥ ተመክሮም፤ ክህሎትም፤ ቅባዕም፤ ተከፋይ አማካሪም፤ ከሁሉ በላይ ፈቃደ እግዚአብሔርን የሚጠይቁ አድማሰ ብዙ ሁነቶች አሉ። ከዚህ አንፃር ስለማዬው ምርር ያሉ ሃሳቦችን አላቀርብም። ምክንያቱም አንድ ብቻ ነው። አብን ማስቀጠል ወይንም አፈራርሶ ምድረ በዳ ላይ ውኃ አፍልቁ ብሎ መጮህ።

#ጠቀራ

በአብን ውስጥ ሰማዕትነቱ የዛሬ ሊመስል ይችል ይሆናል። የአማራ ደም የፈሰሰባት ቀዬ ኤርትራንጨምሮ #የአቤል ድምፅ አለባት። እግር ብረቱ፤ መሰወሩ፤ ዱላው፤ መታፈኑ፤ ማምከኑ፤ መሰደዱ፤ መወረሩ፤ መወረሱ፤ መገለሉ፤ በዚህ ሁሉ የአብን ህልመኝነት አለበት። ነበረበት። ለዚህ ነው ምንም ውጤት ሳያስመዘግብ ሚሊዮኖች ማህላቸው የሆነው።በውስጥ የበሰለ፤ ያሰበለ ፍላጎት ነበር።

ትውልዱ በተከታታይ ይገበራል። አብዛኛው ግን የአማራ ማህፀን እና አብራክ ነው። ዜጋ፤ ኢትዮጵያ ብሎ የተደራጀ፤ የተዋቀረ፤ የተመኜ የአቅሙ ሪሶርስ የአማራ ማህፀን እና አብራክ ግብረኝነት ነው ሁሉንም ለወግ ለማዕረግ ያደረሰው። ግን የአማራ መከራ #በማሽን ዲፕሊኬት ከመሆን ውጪ #ተረፈ ዕሴት የለውም። ሌላው ቀርቶ 1/80% አትኩሮት፤ ተቆርቋሪነት እንኳን ማግኜት አልቻለም።

ዛሬ ዓለም በሙሉ ያደመበት ተፎካካሪ በለው ተቃዋሚ፤ ተቃዋሚ በለው ተቀናቃኝ፤ ተቀናቃኝ በለው ተዋህጂ ሁሉም የውጮችን ሲያገኝ በዘመነ ህወሃት አማራ አብሮ ጨቆነን፤ ዛሬም ይኽው ነው። ለምን ብትሉ አንድ ሐውልት ይቆምለታል ለውጪ ማሳሳቻ ለአገር ውስጡም ማዝያጽልመታዊ ግርዶሽ። ጠቀራ።።

አማርኛ ቋንቋ የሚናገር ብቻ ሳይሆን ቅኔ የሚያውቅ፤ ወይንም ከዛ የተፈጠረ ባህሉን ልምዱን የሚያውቅ ግን ያልሆነ። አቶ ንጉሡ ጥላሁንን። አቶ በረከት ስሞዖንን፤ አቶ ደመቀ መኮንን መውሰድ ይቻላል። ያን መንፈስ ፊትለፊት ያቆማሉ አማራ ተወክሏል ሥልጣን ላይ አለ ለማለት። ለጆኖሳይዱ ዕውቅናም ዳገቱዳጥ ነው። ከበዳዮች ጋርም እዬበደለን ነው ስሞታ ተደማጭ ዬሆነ። ረቂቅ ነው አመክንዮው።

ውስጥውስጡ ግን የአማራ ሁለመና ይራገፋል። ሁልጊዜ በአዳዲስ ሥም፤ በእሸት ሰብዕና የዜግነት ፖለቲካ ይወጠናል። የአማራ ህዝብ አቅሙ ሁሉ ለዛ ይፈሳል። ሥልጣን ላይ ያሉትም ያቆበቆቡ፤ ዘለግ ያለ የአማራ መንፈስ ከኖረ ሲያሰኛቸው በአንድ ቀላጤ ይሰርዙታል።

በዚህ ሽክርክሪት ድፍን 30 ዓመት ተጓዝን። የአማራ ንፁህ ዬአቤል ዕንባ ይጮኃል። አንዲት ጠብታ አለች። ጠብታዋ ኃላፊነቷን ተወጥታለች፤ አልተወጣችም አይደለም ጉዳዬ። ግን መንገድ፤ ግን ጠባብ፤ ግን ከለ አቅሙ የገዘፈ ግሎባል ክስተትን እንዲሸከም የፈቀደ ድርጅት። አብን።

#ልብ ካለህ ከጎምዛዛ የተሻለውን መራራ መምረጥ የማስተዋል ፀጋ ነው።

አብን ማዳን ኢትዮጵያ የሚወድ ሁሉ፤ ለሰባዕዊ መብት የሚታገል ሁሉ ዕለታዊ ተግባሩ ሊሆን ይገባል። ዛሬ ቢሮው አዲስ አበባ ነው።

ነገ #ደብረብርኃን ወይ #ባህርዳር ሂድ ሊባል ይችላል። እስከዚህ ድረስ ማሰብ ይገባል። መራራውን ስታስብ የተሻለው መራራ ጣፋጭ ይሆንልኃል። ይህን ዕድል የአማራ ህዝብ አሳልፎ ከሰጠ ሽኝቱ ጎምዛ፤ ቀኑም ደብዛዛ ይሆናል።

አዲስ ልመሥርት ብትል አዲስ አበባ መቀመጥም፤ ወደ አዲስ አበባ መግባትም ያልተፈቀደልህ ህወኃት ተጨምሮ በሚመራት ኢትዮጵያ አትሰበው። "ቂጥ ገሊቦ እራስ ተከናኒቦ" አንዳይሆን። ድክመቱ ችግሩ በሁሉም ድርጅት ያለ ነው። ከሁሉ በላይ አናርኪዝም ድርጅቱን እንዳይመራው ብርቱ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

በመጠነ ሰፊ ለገጠመው የአማራ ችግር ተቋም ያስፈልጋል። ከአለ ተቋም መልካም ልታስብ ትችላለህ። ግን ተስፋህን አታገኜው። "ልጅ የያዘውን ይዞ ያለቅሳል።" ቤትህን ፍርስርስ አድርገህ ጎዳና ላይ መውጣት ወይንስ ቤትህ ውስጥ ሁነህ ችግር መጋፈጥ??????///// ቢያንስ ተስፋህ መጠለያ ይኑረው።

#ዬታዘብኩት

ሌላው የአደረጃጀት መርሁ ወደ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ያዘነበለ ነው። ጠናና መንገድ ነው። መርሁን ስለማውቀው ነው ይህን እምለው። በተጨማሪም፤ በንቅናቄ እና በፓርቲ መካከል የታክቲክ እንጂ የስትራቴጂ የድርጅት አፈጣጠር መርህ አፈፃፀም ግሎባል ነው።

እንዲሁም ያልገበኛ #አዲስ ደንብ ተረቋል። መላ አባላቱ ካልተወያዩበት የጉባኤው ማፅደቅ ብቻ ተግባራዊ አፈፃፀም ላይ ሳንክ ይገጥማል። ፕሮሲጀራሊም አያስኬድም። አጥርቶ መጀመር ነው ስኬት።

አዲስ አድባንስ የሆነ ሃሳብ ሊያቀርብ የሚችል አባል ሊኖር ይችላል። ይህ መገደቡ አግባብ አይደለም። ቢያንስ ለጉባኤ አባላት ረቂቁ ሊላክላቸው ይገባል። ከፀደቀ በኋላ ተቀበሉ ቁልጭ ያለ የሶሻሊዝም #ተጫኝ ምልከታ ንድፍም ነው። በዛ አጭር ጊዜም ፕሮግራሙም፤ ደንቡም እንዴት ተመርምሮ ሊፀድቅ ይችላል? ፕሮግራም እና ደንብ እኮ የህይወት መመሪያወች ናቸው።

እና ዕይታው የተሸፈነ ስለሆነ ሎጅኩ አያስኬድም። ጋዜጠኛ አበበ በለው ላቀረበው ጥያቄ መልሱ አላረካኝም። አበጥረን፤ አንጠርጥረን፤ ሰልጥንበት መደበኛ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ሆነን የሠራን አደራጆች አለን። አፍሶ ለቅሞ፤ ለቅሞ ማፍሰስ እንዳይሆን።

በባህርዳሩ ጉባኤ የተወከሉም ቢሆንም ግን #አባላት አዲሱን ደንባቸው፤ ፕሮግራማቸውን፤ መሪ ዕቅድም በፖለቲካ አጠራራቸው መሠረታዊ ሰነዶች ቀድመው ማወቅ አለባቸው። መብታቸው ነው። እንደ እኛ በዜና ከሆነ ባባይታወርነት ከሆነ ከአሁኑ በባሰ አብን ማህበራዊ መሠረቱን ያጣል? ብዙ ጊዜ ጽፌበታለሁኝ። የእኛ ሰው ማዶ ማዶ ስለሚይ እንጂ በነፃ ማብራሪያውን ያለድካም ሰጥቻለሁኝ።

#የሆነ ሆኖ።

ዘመኑ ጥሩ ስለሆነ አጀንዳው፤ ደንቡ ረቂቁ፤ ፕሮግራሙ፦ መሪ ዕቅዱ ከጉባኤው በፊት ለአባላት ሊደርስ ይገባል። ኤሌትሮኒክስ ፖስታ ቤት አለ እኮ። ከህትምትም ከቴንብርም ነፃ ነው። ዛሬ ያለ የአማራ ትውልድ በተለይ የጎጃም አማራ ደም ለገበረለት #የአማራ #የማንነት እና #የህልውና ተጋድሎ ቀናዒ ነው። #እምነትም #የሚጣልበት

#ቁልፍ ጉዳይ አዲስ ድምጽ አብን አጀንዳው ነው።

"በደረጃችን" ትንተናውን ማለት አይገባውም። የእሱ ነገር ወደ ቀደመው ሙያ ሳብ ስለሚያደርገው የምሩን ከሆነ የምለው አለኝ። ኦዲዬንሱ ሄትሮጂኒዬስ ነው። ለዛ የሚመጥን ሊሆን ይገባል። ጋዜጠኛ አበበ በለው የፓርቲን አደረጃጀት፤ አመራር መርሆ ማጥናት ግድ ይለዋል። በመደበኛ። አብሮ ስለሚሠራ። ለቤቱ ቀናዒም ስለሆነ።

#አመራሩ በሞግዚት እንዳይሆን። እንደ ማጠቃለያ።

ስጋቴ አመራሩ በስማ በለውእንዳይሆን። ቦታው ተለቆ መሪው ግን? አቶአባዱላገመዳግ ሥልጣን ላይ የለሙ። ግን ኦህዴዳቸው በጫካም በቢሮም ኦነጋዊ መንፈሱን ዘውድደፍቶ ያሻውን ያደርጋል። በሌሎች ድርጅቶችም እንዲሁ ነው። እንደዛ ከሚሆን የተሻለው ዕውነትን ማበጠር ላይ ይሁን።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

04/08/2022

ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል። እንጠሙን!

ትዕግሥትም ሲሟጠጥ ፍቅር ይሰደዳል።እናስተውል!

 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።