ዝልቦ የፖለቲካ የክስ ጭብጥ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ዝልቦ የፖለቲካ የክስ ጭብጥ።
#በጥንቃቄ ለሚያነቡ ህሊናዊነት ብቻ የተፃፈ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ዕፍታ።
ማሸበር ፍኖተ ካርታው የሆነው የዶር አብይ አህመድ አሊ መንግሥት ጋዜጠኞችን የከሰሰበት ጭብጥ ዝልቦ ሆነብኝ። ዝልቦ የባህል ካስማ በሆነችው እቴጌ ጎንደር ቆስጣው ሳይከተፍ የሚሠራበት ሙያ ነው። ማባያ - ወጥ - ልትሉት ትችላላችሁ።
ዝልቦ ጃኬት በዝናብ በስብሶ ተዛንፎ ተቆልፎ እንደ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ጋድም ስታይሊንግ ሲገጥም ርሶ አቤቶ ጃኬት ሲያነባ ዝልቦ ይባላል። ዝልቦ እንደዚህ ዬአመራር ጥብብ፣ መላ ቅጥ አጥቶ ወና ሲሆን #ዝልቦ ፖለቲካ ማለት ቻልኩኝ እኔው።
የድንች፣ የቆስጣ፣ የወተት፣ የበጋ ስንዴ፣ የፒኮክ፣ የአቦካዶ፣ የእሳር አገዳ ፖለቲካ በዘመናችን አዬን። በእኔ ዕይታ የፌንጣ፣ የጃርትም ፖለቲካ እንዳለ እጽፋለሁ። የፖለቲካ ግሽፈትም። ኢንፍሌሽን።
#ጠብታ።
#ቁጥር አንድ።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጨካኙ ህወኃት ከውጭ የሳትላይ ድጋፍ እንደሚያገኝ ገልፀውልናል።,ስለዚህ የአማራ ጋዜጠኞች በትውስት የክስ ትሪኪ ሊከሰሱ አይገባም።
#ቁጥር ሁለት።
አይደለም መረጃ ሉዓላዊነትን የተዳፈረ ግዙፋ የሌላ አገር አንቶኖብ አውሮፕላን አቃለው እንደ እንሽላሊት ውቅያኖስ አቋርጦ #ተሽሎክልኮ¡ ትግራይ አረፈ" ብለውናል ዶር አብይ አህመድ። በሰማይ ላይ አንድ አውሮፕላን እንደ እባብ፣ እንሽላሊት ወይንም 50 እግር ተሽሎክልኮ ሲከንፍ እሰቡት። አይጨንቃቸውም የመሪነት ተጠያቂነት እና ኃላፊነት። ክብር እና ፕሮቶኮልም።
የባዕድ አገር አውሮፕላን ዘና ብሎ ደንበር ጥሶ፣ ሉዓላዊነታችን ጨፈላልቆ ትግራይ ውስጥ ማረፋን ፍክት ብለው እንደ መንገደኛ ተራ የእኔ ቢጤ ሰው ገልፀውልናል። አበስኩ ገበርኩ። እግዚኦታ።
የስለላ አድባንስድ ተቋም የፈጠሩ ኢንሳን፣ የመሩ ኢንሳን፣ የኢንተለንጀሱ፣ የዲጅታል ቴክኖሎጂ ባለሙያው፣ ማስተር ማይንዱ እኮ ናቸው በሚመሩት አገር ውርዴት የሚያላግጡት። ካሰኛችሁ ውሽክ በሉ። ይፈቀዳል።
አቅም እና ክህሎት፣ መሪነት እና ወኔ በአራባ እና ቆቦ ኦርኬስተር ባንድ መሥርተው ዳንሱን ሲያስነኩት። ንጉሥ አይከሰስ ነገር? ከዚህ ቀን በኋላ መሪነት ባልኖረ በህዝብ የተመረጠ የመወሰን አቅም ያለው ፓርላማ ቢኖረን። #ፎርሸዋልና። ይህ ማዕረግ ሆኖ በአደባባይ ቀረበ። ማህከነ።
ኢትዮጵያ በባዕድ አገር በሱዳንም ተወራ ዝም አለች። ውዳቂ ትርክት ናፈቃቸው። ያልደረሱበት የታሪክ ረግረግ የለም። ያልፈቀዱት የዘመን ትርምስ እና ቅጂ የለም። ሁሉንም ልሁን ብለውናል። ጠረኑ የማን ይሆን? ኢትዮጵያ ጎባነወት ናትን ዶር አብይ? ሌ/ ኮነሬል አብይ? ይጨንቃል።
ሰው ጠፋ። በዚህ ዘመን እኮ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳለች፣ የኢትዮጵያ አዬር ክልል ተጥሶ የባዕድ አገር አውሮፕላን አረፈበት። ይህ ጥልማሞት ታሪክም በእጅ ተሰራ።
#ቁጥር ሦስት።
ኢትዮ 360 በአባይ ግድብ ጉዳይ እና በህወኃት ወታደራዊ መሰናዶ ፈትፍቶ አጉርሷቸዋል ለኦህዲድ ኦነጋዊው ሥርዓት። ምርጫው ተሳክቶ ህጋዊ ዕውቅና እንዲያገኙም በትጋት፣ በተከታታይነት ሠርተውላቸዋል። ለእኔ ምርጫ አጀንዳ አልነበረም። ገፊ ምክንያቱ በጭካኔ የታጨቀ ስለነበር።
የኮነሬልነቱ ወኔ ተፈጥሮው ባይሳሳ ስለ ህወሃት ቀድሞ የተሰጠው የ360 ሚዲያ መረጃ ነፍስ አድን ነበር። አቀራረቡ የተደራጀ ነበር። ሊከፈልበት የሚገባ። መረጃ የማሸነፍ ሚስጢር ነው። ግን ዓራት ዓይናማ ቆቅ ሙሴ ሲገኝ። ቆፍጠን ያለ ሁነኛ ሲገኝ።
#ቁጥር ሦስት።
በጠቅላይ ሚሩ ቢሮ ከህወኃት ጋር የሚሠሩ ኦነጋውያን የሉንም? ኦነግ እና ሕወኃት በኢትዮጵያ የሉዓላዊነት አመክንዮ ልዩነት አላቸውን? ለሁለት አካል የሚሠሩ የሉንም ቤተ - መንግሥት ውስጥ፣ ካቢኔ ውስጥስ? ዥንጉርጉር።
#ቁጥር አራት።
ግሎባሉ ዬዲፕሎማሲ፣ የግሎባል የአህጉር፣ የግሎባል የሰባዕዊነት ድርጅት ህወኃትን በቀጥታ፣ በአካል፣ ፊት ለፊት ብቻውን፣ ካለ ታዛቢ አግኝቶ መርዝ እንዲግተው ማን ነው የመግቢያ፣ የበረራ ቢዛ ዬሰጠው? ጠቅላይ ሚር አብይ አይደሉምን? #ጥምልምል። ጥምንምን። ጥምዝምዝም።
#ቁጥር አራት።
የዲሲ ግብረ ኃይል ለክሪስማስ ኢትዮጵያ ሲገቡ ማን ይሆን "ዬኖ ሞርን ቲፒኤልኤፍን ግሎባል ንቅናቄን" ያስቆመው? ሌ/ ኮ አብይ አህመድ አልነበሩምን?
#ቁጥር አምስት።
ኢንባሲወቻቸው ምን ሲሰሩ ባጁ? የሚገርመኝ ይህ ነው። ሲዊዘርላንድ ውስጥ ስኖር ማን የኢትዮጵያ አንባሳደር እንደሆን አላውቅ። ደረጃውንም አላውቀውም። በጥብጫቸውም አላውቅም። ቦታው የት እንደአለም አላውቅም።
ጥሞና ላይ እያለሁ EMS ላይ የሲዊዘርላንድን አንባሳደር ቃለ ምልልስ አድርጓቸው ነበር። " በሰው ማዕበል " ህወሃት መጣብን አሉን። ይህ ፖለቲካዊ ዕሳቤ ለእኔ የምድር እንቧይ የሆነ ምክንያት።
እኩል እስታንደርድ ያለው የኢትዮጵያ መንፈስ ሲዊዘርላንድ ላይ አለ። በዲፕሎማሲ ታች። ሲዊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኦስትራሽ፣ ጣሊያን ቤልጀም ያሉ አንባሳደሮች በውህድም ተቀናጅተው ስንት ቁምነገር በከወኑ።
በህብረት ተግተው ቢሠሩ። ሲዊዝ እኮ ለሥራም አንድ ማህበራዊ ቀውስ ኮሽ የማይልባት ቅድስት አገር ናት። ለዲፕሎማሲም ኦስትራሽ፣ ሲዊዝ፣ ኒወርክ፣ ዲሲ ዕንብርት ናቸው።
በተለይ ሲዊዝ የተረጋጋ ተግባር ለመከወን ልብ ናት። ግን ልባሞች ተመድን 12 ጊዜ ብድግ ቁጭ አደረጉበት። ለዛውም ፖለቲካ ሠራሽ በሆነ ፌክ ትወና።
ወንዶች ሳይቀር ተደፍረዋል፣ የመርሳ ወጣቶች በመርዝ ሙከራ ተደርጎባቸዋል። በኤድስ የተያዙ የአማራ ሴቶችን እንዲደፍሩ ተደርጓል፣ ሰሞኑን ቆቦ የሰረቁትን ጀኔሬተር ሰው ላይ ጭነው ሲሳለቁ ነበር።
ወንዝ ውኃ ሙሊት እንኳን ያሻግራል አያሻግርም በአማራ ነፍስ ሬሳ አሸክመው ይሞክርቡታል። የኮንቦልቻ የሰው ልጅ ቃጠሎ ጢሱ ረዥም ጊዜ ቆይቶ ነበር። አብን ቀረጽነው ያሉት ሁሉ ነበር። ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ቋት የሚደፋ የዲፕሎማሲውን ጥቃት ሊቋቋም የሚችል የተደራጀ የፋክት ክወና የለም።
ነፃ በወጡት እንደ ወልቃይት ባሉት ህወኃት ውጊያውን በተስፋ እንዲቀጥል በጀት እንኳን አልተመደበም። ለዚህ ተጠያቂው ማዕዚ፣ ጎበዜ፣ አሳዬ? ከርባት ሆነ ጉርድ ቀሚስ ዲፕሎማሲያዊ ተግባር አይደለም።
#ቁጥር ስድስት።
#የመከላከያ ሚሩ ከህውኃት የተገኙ አይደሉምን? ናቸው እያልኩ አይደለም። ከሥልጣናችሁ ፍርፋሪ ጋር ምንም ንክኪ የሌላቸው ወገኖቼ የተወነጀሉበት አግባብ አይገበኛም። ወሮ ሙፍርያት ካሜል፣ አቶ አባዱላገመዳ፣ የማን ናቸው? ከላይ እስከታች ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴን የማን ናችሁ? አጥማቂያችሁ ማን ነው? ንገሩኝ ባይ …
#ቁጥር ሰባት።
የዶር አብይ መንግሥት በተለያዬ ጊዜ ከህወሃት ጋር የቀጥታ ግንኙነት አላደረገምን?
#ቁጥር ስምንት።
ህወኃት በአማራ እና በአፋር ክልል የፈፀመው ግፍ፣ በደል ለመሆኑ ዕውቅና አግኝቷልን? ለመረጃ ቋት በቅቷልን? የጥናት እና የምርምር ፋክት ዘለቅ ልብ ሞልቶ የሚያናግር ሪፖርት ተሠርቶበታልን?
ለዓለም ዓቀፋ ማህበረሰብ የተደራጀ ፋክታዊ መረጃ በመስጠት ምን ተሠራ? የአገር ነገር ሆኖ እኛ በግል የምናደርገው ጥረት የተሻለ ነው። በምንም ደረጃ ነው ያለው የዲፕሎማሲ ተግባራችሁ። የሰሞናቱ "ሙሽራ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ" ትወናችሁንም ተከታትዬዋለሁኝ።
ከ12 ጊዜ ያላነሰ የተመድ አጀንዳ ጉዳዩ ሲሆን ያ አረመኔ ድርጅት። አሁን እንኳን ከሰሞኑ ከቅጠላ ቅጠል ፖለቲካ የዘለለ ምን አንጀት አራሽ፣ ቻሌንጁን የሚመክት ዘገባ በተመድ ቀረበ? ሳዳምጠው እኔ አቅለሽልሾኛል።
የአንድ ቀን የህወሃት ውሎ ፋክት ዘመን ተሻጋሪ መፀሐፍ ያጽፋል እንኳንስ ሁለት ዓመት ሊደፍን የተቃረበው ጦርነት። #ዘረክራኮች።
ስንቱን ነዳላ ስንወትፍላችሁ ውለን እንደር ይሆን? ማሸነፋ ሲገኝ ቀረርቶ፣ ቃለ ምልልሱ የቄሮ ይሆናል። ልፊያ የኮፒ ራይት።
መሠረታዊ ጉዳዩ የአማራ መከፋት ዓለም አቅፍ ዕውቅና እንዲያገኝ አትሹም። ፕሮጀክታችሁ ይኽው ስለሆነ። የአማራ ጆኖሳይድን አሰልጥናችሁ መከወን። ማስከወን።
#ቁጥር ዘጠኝ።
#ቁጥር አስር።
ህወኃት ለሰላም ድርድሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዝግጁ ነኝ ሲል፣ ተስፈኛ ኃያላን አገራት የደስታ መግለጫ ሲያዘንቡ ድጋሚ እንከፋ አመራራችሁ የአዬር ጥቃት ፈፀመ። ሸለሸል።
የሚቁነጠነጠው የህወኃት ክንፍ በቤተ - መንግሥት የዲፕሎማሲ ኪሳራውን አዛቃችሁ። ከንቱ። ይህን መዓዚ፣ ጎበዜ፣ አሳዬ፣ ተሜ፣ አባይነህ የማን የእጅ ሥራ ይሆን?
#ቁጥር አስራ አንድ።
ተናጠላዊ የጦር አቁም ወስናችሁ ህወኃትን በመንፈስም፣ በቁስም፣ በአካልም፣ በህሊናም ሲደራጅ፣ ያን ያህል አማራ እና አፋርን አራጦ ይዞ ሲያሰቃይ ትራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ ታንኮራፋ ነበር። ዕብንነት። ለመሆኑ ስንት መቶ ህዝብ ይሆን የምትመሩት?
#ቁጥር አስራ ሁለት።
የአማራ ህዝብ እንዳይደረጅ ማገት፣ የተደራጀው እንዳይመክት መበተን፣ ማሰር፣ ማንገላታት፣ ማፈን፣ ማሳደድ ማን በዚህ ሁለገብ መንጥር ዘመቻ ላይ ተጠቃሚ እንዲሆን ይሆን? ለህወሃት የሎጅስቲክስ ድጋፍ በመንፈስም በአካልም፣ በሞራልም ማን ነው? እናንተው አይደላችሁንም?
ይህን መሰሪ ዝልቦ ተግባር አቅዳችሁ ስትከውኑ ህወሃት የአማራ ክልልን ጥሶ አራት ኪሎ እንዲገባ አይደለምን? ለዚህ ያሰራችኋቸው ጋዜጠኞቻችን ተጠያቄ እንደምን ይሆናሉ?
የአማራ ሕዝብ ጉዞው ሲስተጓጎል፣ ልጆቹ በደጁ ሲረሸኑ፣ ህወሃት እዬሄደ እዬመጣ ሲያራቁተው በኢትዮጵያ፣ ባለው መንግሥት ቢያዝን ሊያስፈርድበት ይሆን? ይህ እንዲሆን ማን ኮኦርድኔት አደረገው?
ከ4500 - 8000 ዬአማራ ፋኖ ሲታሠር፣ ከሰኔ 15/2011 ጋር በተያዬዘ ብልህ የአማራ ዬጦር መኮንኖቹ ካቴና ሲፈረድባቸው ዕውን ህወኃት ተመልሶ ስልጣን እንዲይዝ የተሰላ ፕሮጀክት አይደለምን?
የፋኖ አደረጃጀት ባይታወክ ህወሃት ያስበው ነበርን ምዕራፍ ሦስትን ጥቃት? ህወኃት እንደ ፋኖ ድሮናችሁን አይፈራም። ምክንያት እንተዋወቃለንለን። ምን እንዳለን ያውቁናል። እኛም እናውቃቸዋለን። ዱሩ ገደሉ፣ የአዬር ፀባዩ ምህንድስና ለፋኖ በእጁ ነውና።
ለዚህ ሁሉ ዝልግልግ ምልግልግ ገመናችሁ።
ለዚህ ሁሉ ሙርቅርቅ ዝብርቅርቅ አመራራችሁ።
ለዚህ ሁሉ ዝልቦ የፖለቲካ አቅም ክሳታችሁ የአማራ ፀሐፍት፣ ጋዜጠኞች ተጠያቂ ሆኑ። ፍትልትል ያለ የሚጎፈንን ክርፋት።
በልካችሁ ሊነገር ይገባል። የእናንት በሥርዓተ - መንግሥት አመሠራረት፣ አመራራ ወናነት የአማራ ጥንግ ድርብ አንደበት እና ብዕር ይታገታል፣ ይታፈናል፣ ይታሰራል፣ ይከሰሳል፣ ይገደላል።
ብዕር ብቻ ያላቸው ዓራትዓይናማ የአማራ ልጆች በእናንተ አቅመ ቢስነት፣ ስልተ ቢስነት፣ ክህሎት አልባነት ሊከሰሱ ቀርቶ ሊወቀሱ ባልተገባ ነበር።
ጦርነት እንደማያስፈልግ ልክ እንደ እኔ መዓዚ ሞግታለች፣ የጦርነቱ ክስተት ጦሱን በሚገባ ጋዜጠኛ ጎበዜ ቀድሞ አብራርቷል።
የጦር ምህንድስና ከፋቲክ ብቻ አትሰቡት። ቅብዓም አለ። በባዶ እግሩ በጓንዴ፣ በምንሽር አገር ያውም የአኽጉር ያህል አቅም ያላት ውብ እናት ኢትዮጵያን አበጅቶ ሰጥቷችኋል የትናንት ጀግና በእጀ ጠባብ፣ በግብግብ።
ጀግና በፕሮፖጋንዲስት አይፈጠርም።
ጀግና ፕሮፖጋንዲስትም አይደለም።
ፕሮፖጋንዳም ጀግና አይደለም።
የእናንተ የህሊና ከርስ የሚሞላው ግን በባዶ ዬፕሮፖጋንዳ ኳኳቴ ነው። ሃቅ ትፈራላችሁ። ኢትዮጵያ ደንበሯ፣ ኢትዮጵያ ዬአዬር ክልሏ ተጥሶ ተኝቶ የሚያድር መሪ እንሆ ዘንድሮ አዬን። ማቅም ለበስን።
ይታሰብ የአንድ ክፍለ አገር የጦር ጉሰማ መርታት፣ ማንበርከክ፣ አመድ ማድረግ አቅቶ እንዲህ ሰርክ ማቃተት? ህወሃት በ4 ኪሎ ቤተመንግሥት አለ፣ ተንቤን በርኃም ህወሃት አለ፣ ወለጋም ምድርም ሕወሃት አለ። የግድ ተጋሮ መሆን አይጠበቅም። ዶክተሪኑን የሰለቀጠ ሁሉ ህወኃታውያን ነው። እናንተን ጨምሩ።
ህወኃት ያስታቀፋችሁን ድውይ ሕገ መንግሥት፣ ሕወኃት ያስታቀፋችሁን የአፈፃፀም መመሪያ፣ ሕወኃት ያወረሳችሁን ውራጅ ዬአባላት መንፈስ፣ ህውሃት ያስረከባችሁን ፍዝ አካላት ተሸከምቻሁ አለማፈራችሁ በዘመነ ህወኃት የታሠሩ፣ የተንገላቱ ወገኖችን ስታሳድዱ። ማህበረ - ማፈሪያ።
አቅማችሁን ጠይቁ።
ክህሎታችሁን አወያዩ።
ፓርክ እና መዝናኛ ወኔ አይደለም።
እንደ አንበሳ መሆን ካቃታችሁ እንደ ፒኮክ እያሽካካችሁ ሞክሩት። ከአማራ ሊቃናት እራስ ውረዱ።
ለሰከንድ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ በህወኃት ለመተዳደር ትናንት አልፈቀድኩም፣ ዛሬም አልፈቅድም ወደፊትም አልፈቅድም። የንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክን ቤተ - መንግሥት ተረክባችኋል። ጠረናችሁ፣ ውርስ ቅርሳችሁ ግን ህወሃታዊነት ነው።
አንዲት ስንዝር ከዛ ፈቅ አላላችሁም። የማሸነፍ አቅሙ ሙሽትም ቋት የማይገፋውም ማስተር ማይንዱ ሕወኃታዊ ስለሆነ ነው። ውስጣችሁ ይቀበለዋል ህወሃትን። ህወሃትን ትፈራላችሁ በጽኑ። ህወሃትን አብዝታችሁ ትናፍቃላችሁም። መያያዣው ስለጠፋችሁ። የእኔ የምትሉት አገር መሪ ሌጋሲ የላችሁም እና። ልሙጥ።
ለብጣችሁ፣ ለብጣችሁ ብትለጣጥፋት ከጭካኔ፣ ከነዲድ፣ ከፀረ ሰው፣ ከፀረ ተፈጥሮ፣ ከመታበይ፣ ከውድመት፣ ከፍርስራሽ ክምር ፈቅ አላላችሁም። የዳኑትን ሁሉ አጥምቃችሁ እንሆ አብራችሁ ትንኮላበሳላችሁ።
አቅም ነው የሚያስከብረው። እና "አህያውን ፈርቶ መደላድሉን" ሆነ እና አማራን በአራቱም መዕዘን ሰቅዛችሁ እንዲህ በእሪታ በደም ገበጣ ትጫወታላችሁ።
ህወሃት ምን አለው? በዲፕሎማሲ እኮ አፈር ድሜ አስግጠነው ነበር። ዛሬ የሚሞግታችሁ ዓለም ትናንት የእኛ ነበር። ድካሙን ከስራችሁ አከሰራችሁት።
አቅም ሲያንሳችሁ የቁንጫን መወጣጫችሁ የአማራ ህዝብ ማህፀን እና አብራክ ሆነ። ለዛውም ለስልቡ የኦነግ ፍግፍግ ፖለቲካ። ለኩሬው የኦነግ ፖለቲካ። መጥኔ እናንተን ለተሸከመ በትረ - መንግሥት። ስንቱ ላደገደገለት።
ዓለማችን ይኽው ይህን እዬሠራ ሲልክ ባጄ። የሳትላይ ሙሉ ድጋፍ ያገኛል ተቀናቃኛችሁ። ያሠራችኋቸው አማራወች ብዕርና ማይክ ነው ያላቸው።
የሆነ ሆኖ ተረበኛው ህወኃት ይህን የሳይበር መረጃ ድጋፍ ለመገንጠልን ጥርጊ ለመሥራት ይህን ይፋ ተደረገ። ከቻላችሁ እነሱን ሞገቱ። ምዕራባውያንን፣ አውሮፓ ህብረትን፣ ተመድን፣ የሳይበር ደጋፊ ድርጅቶችን። አቅሙም ወኔውም ካላችሁ። ዝልቦ!
ወጣቶችን ፍቷቸው። የአማራን ወጣት የማጨድ ልዩ ፕሮጀክታችሁ ስለመሆኑ አሳምሬ አውቀዋለሁኝ። እያሰገራችሁ በስውር እዬፈጃችሁን ነው።
ዝም እምለው ለዛ ጥሙርሙር ሲኦል ለህወኃት አቅም እንዳልሆን ብዬ እንጂ ምን አላችሁ? የፖለቲካ አቅም ማለቴ ነው? ድክመታችሁን አደራጅታችሁ መምራት የተሳናችሁ፣ በፕሮፖጋንዳ አጥሚት ትርትር የምትሉ። ዕድሜ ለባለ ቅባዓዋ ኢትዮጵያ በሉ። በኪነ ጥበቡ አላችሁ።
ለኩሽ መሥፋፋት 50 ሚሊዮን ትመድባላችሁ፣ ለቤተ መንግሥትስ? ቤተ መንግሥት እያለን? ተችላችኋል። ይህም ሆኖ ጥጋቡ አላስችላችሁ አለ። እንጡሩብ አሰኛችሁ። መለጠጡ ይላጣል ይከስማልም። ጠብቁት። ተስፋችን አምላካችን ነውና።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/10/2022
#አንሰበርም!
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ