እነኝህ ወጣቶች አዲስ አበቤ ናቸው።
1) እነኝህ ወጣቶች አዲስ አበቤ ናቸው። ግንቦት 7 አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል አድርጋችኋል ተብለው ወደ ጦላይ እስር ቤት ከተወረወሩት 1300 እስረኞች ማህል ተለይተው ሳይፈቱ የቀሩ ናቸው። ስለ እነሱ መብት የሚሟገት ቀርቶ የሚያስታውሳቸው የለም።
2) አምስት አዲስ አበቤ በአደባባይ ተረሽነዋል። ሥማቸውን አናውቅም፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲሁ። ደመከልብ ሆነው የቀሩ የእኛወች ሰማዕታት።
3) በአድዋ ድል፣ በካራማራ መታሰቢያ ጎላ ብለው የታዩ ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ ያልሆኑ የተሰወሩ፣ የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደሉም፣ የተደበደቡም በገላኑ ኦሸትዝ እና በአዲስ አበባ ሚስጢራዊ እስር ቤቶች አሉ። ይህን የታፈኑ ጋዜጠኞች ወለሉ ደም በደም ሆኖ እንዳዩ ገልፀዋል።
ቢያንስ በትውስት ራዕይ ከመንጎድ በያዙት ፀንቶ መስዋዕትነትን ቀንሶ፣ አቅምን ቆጥቦ በማስተዳደር ለጨካኞች አቅም በገፍ ሳይቀልቡ ዘመንን መምራት የሚችል የማስተዋል አቅም ስስነት በመጨንገፍ ብቻ ጥቃትን ማወራረድ ያለፍንበት ህይወት ነው።
ስለዚህ ማስተዋል ያለ ልዩነት የሰጠንን ፈጣሪን እያመሰገን ሥራ ላይ እናውለው ነው የጭብጡ ፍሬ ነገር።
ወደ እስር ቤት የሚጋዘው የወገን የዕድሜ፣ የራዕይ ዘረፋንም አብሮ እስከመጨረሻው መጋፈጥ ሊገፋ አይገባውም።
ክብረቶቼ እንዴት ናችሁልኝ?
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/11/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ