#ክብር ድንበር የለውም። እነኝህን ባሊህ ባይ የሌላቸውንም ተመልከቱ።

 

#ክብር ድንበር የለውም።
እነኝህን ባሊህ ባይ የሌላቸውንም ተመልከቱ።
 
 May be an image of 3 people
 
ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ጋር ታቅዶ የነበረው በአዲስ አበባ አብያተ ቤተክርስትያንን ማንደድ፣ ማህበረ ምዕመኑን ማወክ፣ ጥቁር ማልበስ እንደ ዝዋይ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የታለመ ነበር። ይህን እሳቸውም አለመሸሸጋቸውን ገልፀው እንደነበር በጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ትንታኔ በወቅቱ አዳምጬ ነበር።
 
የሆነ ሆኑ እነኝህ ለማተባቸው የቆሙ ብፁዓን እስር ቤት ሲጋዙ ይህ ሁሉ የቤተክርስትያን የተዋህዶ ሚዲያ እያለ አጀንዳ አልሆኑም። ምን አልባት በህይወት መኖራቸው እንደ ትርፍ ታይቶ ይሆናል።
 
እነኝህ ቅዱሳን የተረሱ ናቸው። ቤተ ክርስትያንም ቸል ስላለችው በራሷ መንበር ላይ የመፈንቅል ሙከራ የተደረገው በዚህ ምክንያት ነው። ቀላሉ ችግር ቸል ከተባለ ግዙፍ ችግር ማሳዘሉ አልተስተዋለም። ክብር ድንበር የለውም።
 
ግን ስለክብር ተጋድሎው ሲሶ እንኳን አልደረሰም። ስለዚህም ረጋጮች አድባራትን በድሮን እዬደረመሱት ይገኛሉ።
ሌላው አማራ ክልል ያለው ውድመት የተዋህዶም ስለመሆኑ ለቤተክርስትያኗ ባይታዋር አመክንዮ ሆኗል።
 
ይህም ብቻ አይደለም በገፍ ሰርክ የሚረሸነው አማራ በተዋህዶነቱም ስለመሆኑ ቤተክርስትያኗ የዘለለችው ይመስላል።
እንዲሁም ከ20 ሺህ - 50 ሺህ እስር ላይ የሚገኜው የአማራ ሊቅ/// ሊሂቅ/ አርሶ አደር እግር ብረት የተወሰነበት የተዋህዶ ልጅነቱም ስለመሆኑ ከማስተዋል ጋር ቤተክርስትያኗ ትልልፍ ያደረገችበት ዕድምታ ነው።
 
በጠቅላላ ቅድስታችን የራሷን ጉዳይ አሻግራ እዬተመለከተች በአስተዳደራዊ ተግባር ላይ ብቻ ስትታክት ይስተዋላል። ዋሻዋ፣ ጥላ ከለለዋ ማህበረ ምዕመኗ ጉዳትስ???
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
እነኝህ ብቁወች አዲስ አበባን አናስደፍርም ያሉ የሃይማኖት አርበኞች ናቸው።
ውዶቼ መልካም ቀን፣ መሸቢያ ውሎ አደር። ቸር ያሰማን፣ ቸር እንሁን አሜን።
"እግዚአብሄር ይስጥልኝ"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/12/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።