ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እሳት እና ውኃ የአቨው የእመው አውራ ጥበብ።

  እ ሳት እና ውኃ የአቨው የእመው አውራ ጥበብ። " የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያዘጋጃል። " ( ምሳሌ ፲፮ቁጥር ፱ )   # ዕፍታ ለሰላምታ። እንዴት አደራችሁልኝ ክብረቶቼ ? ኑሩልኝ። አሜን። እንዴት አደርሽልኝ ክብሬ እናት አገሬ ኢትዮጵያ ? ኑሪልኝ። አሜን። # ጠብታ ። ነዷል። እንደዚህ ሁነት የቅኔው ዕንቡጥ ዶር ቴወድሮስ ካሳሁን ጥቁሩ ሰውን አሳትሞ በዓለም ኦሎንፒክ እንዲገኝ ከዓለም ዓቀፍ ድርጅት ጋር ንግግር በጀመረ ጊዜ ጃዋሪዝም እንዳቆጠቆጠ፣ ጃራይዝም አገርሽቶበት በኦነጊዝም ሲያጎራ በዬፓልቶኩ በነበረበት ወቅት እንደነበረው ነው ምድሪቱ ቋያ የሆነችው። ሰርክ መንገብገብ፣ ሰርክ መለብለብ፣ ሰርክ መገረፍ፣ ሰርክ መታመስ። ቅድስት አገር፣ የተመረቀች አገር፣ ብሩክ አገር፣ ሁሉን የሰጣት አገር መፈጠሯ የሚጎረብጣቸው፣ መኖሯ የሚቆረቁራቸው ኃይሎች ጊዜ እዬጠበቁ፣ ወቅት እዬጠበቁ ሰላሟን፣ ቅድስናዋን፣ ታሪኳን እንዲህ ይዘቀዝቁታል። እንዲህ ያብጠለጥሉታል። ሞትን አጭተው ሞትን ይድሩበታል። ግጥግጡ፣ ቅልቅሉ ሞት እና ውርዴት ነው። የበቀለ ሲነቀል፣ የለማ ሲወድም። የሞላ ሲፈስ ዘመን ተዘመን በአላደገም ሲዳካር በሰው ግብር ብቻ መንዘላዘል። ክብር ሆኖ። ማዕረግ ሆኖ። # አታሞው ከድንጋይ # በላንቃ ። ዛሬ ሁሉም ትቢያ መልበስ አለበት። ሁሉም # በሻሻ መሆን አለበት። ሁሉም ሻሸመኔ፣ አጣዬ፣ ዝዋይ መሆን አለበት። ሁሉም አመድ ዱቄት መሆን አለበት ተብሎ ...