አንድ የምታውቁት መልካም ሰብዕና በድንገት እራሱን አጥቶ ከደግነት አስተሳሰቡ ወጥቶ #ክፋነትን ተደላደልብኝ ሲል #አትደንግጡ።

 

የምታውቁት መልካም ሰብዕና በድንገት እራሱን አጥቶ ከደግነት አስተሳሰቡ ወጥቶ #ክፋነትን ተደላደልብኝ ሲል #አትደንግጡ

"ሽበትስ የሰው ዕውቀቱ ነው፦የእርጅናም

ዘውዱ ያለነውር መኖር ነው።"

(መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ቁጥር )

እንዴት አደራችሁ ማህበረ - ቅንነት። ጎፋስ አማራ ክልልስ እንዴት አድረው ይሆን???? 


 

#አለመደንገጡ በብዙ ይረዳል። ምክንያቱም #እንድትረጋጉ ያደርገል። የሰው ልጅ ሲፀነስ በፈጣሪው ንጽህና፦ ቅድስና፤ መባረክ ልክ ነው ብዬ አምናለሁኝ። ቅድስናው፤ መባረኩ ፈተና የሚገጥመው ከተወለደ በኋላ ነው የሚል ዕምነትም አለኝ። ከተወለደ በኋላ #ለምን? ንጽህናውን፤ ቅድስናውን ሊያስቀጥል የሚችል ተቋም ዓለማችን ስለአልሰራች። በዚህ ዘርፍ ዓለማችን ልሙጥ ናት።

ስለዚህ ክፋ ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ፤ ወይንም በከፊል የሰው ልጅ ከተፈጠረ በኋላ #ይሞግተዋል እራሳቸውን ያሸነፋ ጀግኖች ሊኖሩ ይችላሉ። እነሱ ግን ጥቂት ናቸው። ጥቂት መሆናቸው ብቻ አይደለም። ጥቂቶችም ውሎ ሲያድር ከክፋነት ሃሳብ ጋር ሊላመዱ ይችላሉ። በተለይ ሙሉለሙሉ በክፋ ሃሳብ ሙሉ #የተነከሩ የቅርብ ሰው ካላቸው ቀስበቀስ ዝንባሌያቸው ወደዛ ይሆናል።

1) ክፋ ሃሳብ #ፈጣን ነው።

2) ክፋ ሃሳብ #ወራሪም ነው።

3) ክፋ ሃሳብ #ተስፋፊም ነው።

4) ክፋ ሃሳብ #ተጫኝም ነው።

5) ክፋ ሃሳብ #ሰልቃጭም ነው

እንደሚታወቀው የክፋ ሃሳብን ወረራ፤ የክፋ ሃሳብን መስፋፋት፦ የክፋ ሃሳብ ተጫኝነት ሊገታ የሚችል ሉላዊ #ትምህርታዊ #ተቋም ዓለማችን #በመደበኛ የላትም። ደግ ሃሳብን ሲያበረታታ የምታውቁት ሰብዕና በማታውቁት እንግዳ ባህሬ ሲዳክር የምታዩበትም ለዛ ነው። አብሮት ካላደገው ክፋት ጋር ሲላመድ ለእሱ አይታወቀውም። በቅርበት የሚውቁት ግን ይህ ሰው እንዴት ተለወጠ እያሉ ከራሳቸው ጋር ይመክራሉ።

በተለይ በራስ #ዬመተማመን ስሜት ካዘቀዘቀ #በቅናት #በምቀኝነት #በጎ ነገሮችን ወይንም ግንኙነቶችን በማቃለል እና በማጎሳቆል ላይ ሊተጋ ይችላል። በምታማክሩት መልካምነት ላይ ሁሉንም ነገር በማጣጣል፦ ሁሉንም ነገር በማቃለል፦ ሁሉንም ነገር አሳንሶ በማዬት ብቻ ሳይሆን የነበረውን የቀረቤታ ዲስታንስም ወደማራቅ #ሊያዘነብል ይችላል።

በተለይ በለታዊ ኑሮው #ጊንጥ ሃሳብን የሚያራምዱ ሰብዕናወች ከኖሩ በቀጥታ የዛ ጊንጥ ሃሳብ ቤተኛ ሊሆን ይችላል በመልካም ሃሳብ ላይ ትጋት ያለው ሰብዕና። ውጩው ደግሞ #ጩኽት ነው። በቅርቡ የክፋ ሃሳብ ትጉህ + የውጩ ጩኽት ሰብዕና ምን ሊሆን እንደሚችል እሰቡት። ክብረቶቼ ከገዘፈው ሳይሆን #ከአነሳው ከበዛው ወይንም ከበረከተው ሳይሆን #ከጥቂቱ ተነስታችሁ፤ ከራቀው ሳይሆን #ከቀረበው ማህበራዊ ግንኙነትን መነሻችሁ አድርጋችሁ #መርምሩት

በረጅም ጊዜ ሂደት ክፋትን ከዋጠ ሰብዕና ጋር የለት ኑሯቸው የተቆራኜ ከክፋ ሃሳብ አደረጃጀት አያመልጡም። በዬጊዜው ያን ክፋትን እዬተጎነጩ ቤተኛ ሆነው ያርፋታል። ቅንነታቸው #እዬተመጠጠ በጎ ሃሳባቸውን ክፋት #እያጫጫው ጠቅልለው ወደ ክፋው ዓለም #መጪ ሊሉ ይችላሉ። እንዲያውም ከነበረው ክፋ ሰብዕና ይልቅ እነሱ #ልቀውም በልጠው ሊገኙ ይችላሉ። አዲሱ የክፋነት ዓለም ጉጉታቸውን እዬጨመረ ቃላቸው፤ የአነጋገር ዘይቤያቸው ሁሉ ይለወጣል። ቶናቸው ይቀዬራል። ንግግራቸው መርዝ ቀመስ ይሆናል። ማስከፋት፤ ማሳዘን መደበኛ ተግባራቸው ይሆናል።

ታውቁት የነበረ ቸርነት ከውስጥ ሲተን እናንተው ታዩታላችሁ። ይህ ሲሆን መደንገጥ አያስፈልግም። በፍፁም። ጉዳዩን ከሥር ማጥናት ይገባል። በስፋት ስትመለከቱትም ከክፋ ሃሳብ ጋር እርቅ እንዳይፈፀም የሚያደርግ ተቋማት አለመኖራቸው ስለመሆኑ ትረዳላችሁ። ስለሆነም ከክፋ ሃሳብተኞች ከመከፋት ይልቅ ታዝኑላቸዋላችሁ። የእነሱ ብቻ ችግር አይደለም እና።

በእያንዳንዱ የግንኙነት መስመር ሁሉ ይህ ይገጥማል። ክፋ ሃሳብ ይፈትናል። ቤተኛው ለማድረግ ይታትራል። ዓለም እሱን በመደበኛ ሊቋቋም የሚችል ተቋም ባይኖራትም የግል ውሳኔ ግን በእጅ ያለ ዕንቁ ጉዳይ ነው። ደግሞ በገጠመኞች በሚገጥሙ የክፋ ሃሳብ ወረራ ላይ ራስን ማቀብ ይገባል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ የእኔ ውቦች።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

29/07/024

ጊዜ ቴርሞሜትር ነው።

ጊዜ ራዲዮሎጂም ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።