የጨካኝ መንግሥት ዕድሜውን መገመት ይቻል ይሆን?

 

የጨካኝ መንግሥት ዕድሜውን መገመት ይቻል ይሆን?
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
 
ቱርኪ ከፍተኛ የሆነ የመሬት ንደት ሲገጥመው የተከበሩ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን #ውስጣቸውን - #ለውስጣቸው በንጽህና ሲገልፁ አዬን። አስተዋልን። በዕንባ ረስርሰውም። አላዛሯ ኢትዮጵያ ውስጧን ውስጥ ያደረገ መንግሥት መቼ ታገኝ ይሆን። የምርቃታችን መነሳት በብዙ መልኩ የሚገልጽ #ክስተት። ማዘን፤ ማልቀስ፤ ችግርን መጋራት ጣር የሆነበት መንግሥታዊ አገዛዝ #ዕድሜው #ምን #ያህል ይሆን? ነገም ጣር ላይ ነው። የጭካኔ ቡፌ ስለማይ። 
 
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት #እናት ናቸው። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ። እሳቸውስ ይህ #ያላስደነገጣቸው? ይህ ያላራዳቸው ምኑ ሊያስጨንቃቸው ይሆን? ውስጥን ባርባር የሚያደርግ የሚረብሽ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ ክስተት። ጠበቅኩ፤ ጠበቅኩ ግን {}።
 
ቀዳማዊቷ እመቤት ወሮ ዝናሽ ታያቸውስ???? ከባለቤታቸው ጋር ሙሽራ ሆነው ሲመርቁ፤ ሲጎበኙ ይታያሉ። ለዕንባስ? አንዲት እናት አራት ልጆቿን በአንድ ቅጽበት ስታጣ በዓለም ዓቀፋ መድረክ የኢትዮጵውያን ልጆች እናት እሆናለሁ ያሉት ቃል የት ላይ ይሆን???? ይህ አዲስ አይደለም።ግን በዛ #ገለማም። 
 
መቼ በቃሽ ይላት ይሆን የላይኛው አላዛሯን ኢትዮጵያ??? #ያስምጣል። ጭካኔ መርሆ፡ ጭካኔ ዶግማ እና ቅኖና ሲሆን። እንዴትስ መሽቶ ይነጋላቸዋል??? #ብር ተብሎ ሊኬድ የሚገባበት #አስደንጋጭ #ክስተት ነበረ። ለእነሱም ያመለጠ #ዕንቁ ዕድል። ኢትዮጵያን መቅጣት ማሳዘን እንደ ሌጋሲ የተያዘ ገመና። 
 
እንዲህ ዓይነት ርህርህና፤ እንዲህ ዓይነት አጽናኝነት፤ እንዲህ አይነት አይዟችሁ ባይነት እንደ ናፈቀን የቀረ ጉዳይ ሆነ። ወደፊትስ? ምን ተስፋ የሚሰጥ ነገር ይኖር ይሆን???? ፀሎት፦ ድዋ።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
በቃችሁ ይበለን የላይኛው አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26/07/2024
 
ፈጣሪ ሆይ ምህረትህን ላክልን። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።