ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ?
ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የተከበረው የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን "አህያውን ፈርቶ መደላድሉን" እንዲሉ ብሄራዊ ሆኖ ግን የእስረኛ ፍቺን አስመልክቶ፤ የአማራ ክልል ላይ ጫና ለመፍጠር መሞከሩ ግርም አለኝ። #አዝኛለሁም ። በእድሜ ዘመኑ የ365 ቀናት በራሱ አቅም የመንቀሳቀስ ምንም አቅም የሌለውን አልቦሽ ክልል ላይ ሃሳቡን ማቅረብ በራሱ ኮሚሽኑን ግምት ውስጥ ይጥላል። የሆነ ሆኖ አጠቃላይ የፖለቲካ እስረኞች የእስር ፍቺ #በብሄራዊ ደረጃ ቅድሚያ ተሰጥቶት፦ በበኽረ ጉዳይ አጀንዳነት ተይዞ ሊሠራበት ሲገባ እንደ ተራ #ተለጣፊ ጉዳይ፦ የአማራ ክልል እስረኞች ብቻ እንዲፈቱ መጠዬቁ ኮሚክ እሳቤ ሆኖ ነው ያገኜሁት። ቀድሞ ነገር የህወሃትን መንበረ ሥልጣን እንዲለቅ ምዕራብውያንን ያሳመነው መሠረታዊ አንኳር ጉዳይ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ነበር። ያንጊዜ ተደማሪ፤ #ተጠማኝ ፤ ተዋህጂ ስስ ስለነበር በዬትም ሁኔታ የሚደመጠው ድምጽ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ነበር የትግሉ ሞቶ። እናም አሳካን። የሆነ ሆኖ የአማራ ጉዳይ ብሄራዊ እንጂ ክልላዊ አይደለም። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የአብይዝም መንግሥት በቆራጥነት ሊወስዳቸው ከሚገቡ መቅድመ እርምጃወች ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት የፖለቲካ እስረኞችን #ያለምንም #ቅድመ ሁኔታ መፍታት ለቀጣዩ የፖለቲካ ንግግር ይሁን ስምምነት በር ከፋች ይሆናል። እንደ እኔ ምኞት እና ተስፋ በኢትዮጵያ ምድር ማንም በአስተሳሰቡ፤ በምልከታው፤ በፖለቲካ #አቅሙ እና #አቋሙ አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊታሰር፤ ሊንገላታ፤ #ቤተሰቡ #ሊጉላላ አይገባም። በእስር ምክንያት የመኖር ተስፋው ሊዘረፍ፤ ወጣትነቱን ሆነ የ...