የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ #የፈረንሳይ ጉዞ እና ዕይታዬ።
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ #የፈረንሳይ ጉዞ እና ዕይታዬ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #እፍታ ። በጣም ረጅም ጊዜ ሆነኝ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን ፎቶ ለጥፎ መሞገት ካቆምኩኝ። ምክንያቴ #አመክንዮዊ ነው። ዛሬም ግጥም የሆነ ቁምነገር ተገጣጥሞብኝ ነው እንጂ ፍላጎት የለኝም የሳቸውን ፎቶ ለጥፎ መሞገት። የሻሸመኔ ሰማዕትነት ሂደት ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፍላጎት ሞተሩ ተተከለ። ጥረታቸውም ድሉን ሀሌታ አለ። የአሜሪካ ጉዞ እና ስደተኛው ሲኖዶስን …?// የህክምና ባለሙያወች ለምግብ እጥረት መጋለጥ አቤቱታ እና የነነዌ ሱባኤ በኢትዮጵያ እና የጠቅላዩ የፈረንሳይ ጉዞ የዛንጊዜውም ሆነ የዛሬው …??? ዘመኑን እኔ #አሳቻ እለዋለሁኝ። መሪውንም ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊን አሳቻ መሪ እላቸዋለሁኝ። የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬም አሳቻ ነው እላለሁኝ። ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ሳትሆን አሳቻ ሁኔታ ላይ እንዳለች ነው የሚገባኝ። መስቀለኛማ ወይ ስሜን፤ ወይ ደቡብ፤ ወይ ምስራቅ ወይ ምዕራብ ትንሽ ዘለግ ሲልም ስሜን ምስራቅ፤ ደቡብ ምዕራብ እያለ ይቀጥላል። አሳቸነት ግን አቅጣጫውን ለመወሰን ይቸግራል። አቅጣጫውን ለመተንበይም #ጋዳ ነው። በጠቅላይ ሚኒስተሩ አውሮፕላን ስደተኛው ሲኖዶስ ወደ አገር ሲገባ ማን ይህ ይሆናል ብሎ ተነበዬ? ማንም። ሐሤታችን ከእልልታ በላይ ነበር። ይዘው የወሰዷቸውን አትገቧትም ብለው "አገር ናት ያሏትን" ሃይማኖት ቢዛ ሰጪም፥ ነሺም ሲሆኑ ማየት የሚተነበይ አልነበረም። አሳቻነትን ቢገልጽልኝ ብዬ ነው ይህን ለንጽጽር ያቀረብኩት። ደጋፊወቻቸውም፤ አክባሪወቻቸውም ሆኑ አጋዥወቻቸው ያወቋቸው ይምስሏቸው እንጂ አያውቋቸውም። ጠ...