ሳይንስ፤ ቴክኖሎጂ፤ ሥልጣኔ ናቸው። ሥልጣኔያቸው መሠረቱ ዕውነት እና ፋክት ነው። የሁለቱ ጋብቻ መኖርን ያቀላሉ።
ሳይንስ፤ ቴክኖሎጂ፤ ሥልጣኔ ናቸው። ሥልጣኔያቸው መሠረቱ ዕውነት እና ፋክት ነው። የሁለቱ ጋብቻ መኖርን ያቀላሉ።
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እኔ እና እናንተ የምንገናኜው፤ ወደ ተሰደድንበት አገር የተጓጓዝነው ዘመኑ በፈቀደው የቴክኖሎጂ ሥጦታ ነው። አንድ አገር የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ፤ የትምህርት ተቋማትን የሚመሩ ማዕከላዊ ተቋማት መፍጠር፤ #ማሰልጠን፤ የትውልድ ኃላፊነትን መወጣት ነው።
ዘመኑ በሚፈቅደው ልክ አጀንዳውን የእኔ ብሎ አትኩሮት መስጠትም ከሌሎች የመኖር ጉዳዮች በስተኋላ ቆዬኝ እስኪ ሳይሆን #በአቻነት እንዲጓዝ በመርህ ደረጃ መቀበል እና ወደ ተግባር ለመቀዬር የሚችሉትን ያህል መጣር #የሚጣጣል፤ #የሚቃለል፤ የሚወገዝ ሊሆን አይገባም።
ቀደምት አገር ግን በብዙ ነገር ኢትዮጵያ ኋላቀር ናት። ቢያንስ ዘመኑ በሰጠው ሥልጣኔ ጋር ተጣጥሞ ለመቀጠል መጣር የተገባ እርምጃ ነው። "ትምህርት ከድል በኋላ" በእኔ ዘመን የነበረ መፈክር ነው። ያ አልጠቀመም። 50 ዓመት በጨለማ ተዋጡ ነበር። የተሰደደው ትውልድ ግን ተምሮ እንሆ የትምህርት ሚር ለመሆን የበቃው በመማሩ ነው።
የዛን ጊዜው "#አትማሩ!" ብዙ ተስፋን አቀጭጮ እና ብዙ ዕድሎችን ለሙጦ ያለፈ ጎጂ ጉዳይ ነው። ዛሬም መደገሙ ያሳዝነኛል። ዛሬ ብዙ ሰው የከተማው ጉሮሮውን አርጥቦ የሚያድረው ማህበራዊ ሚዲያ በፈጠረለት #ትሩፋት ነው። ሥልጣኔ ሊገፋ አይገባም። ሥልጣኔን መፍቀድ እንደ ነውር ሊታይ አይገባም።
ልቅና እና በልዕልና የሚገኜው #በዕውቀት ነው። በመማር ነው። መሰልጠን በድካም ሳይሰለቹ በመትጋት የሚገኝ ትሩፋት ነው። በአብይዝም የመንግሥት ሥርዓት አፈፃጸም የሚጎድሎ ጉዳዮችን ነቅሶ አውጥቶ መሞገት የተገባ ነው። ማስታመም አይገባም። የሚታዩ መልካም ነገሮችን አንደበት ፈቅዶ ማመስገን ባይቻል እንኳን የሥልጣኔን መሻት መልካም ምኞት #ማጣጣል ለትውልዱ፤ ለተስፋም ለማግሥትም ፈጽሞ አይጠቅምም።
ሳይንስን፤ ቴክኖሎጂን፤ ዘመን ሰጥ ሥልጣኔወችን አላዬሁም፥ አልሰማሁም ብትል ኢትዮጵያ በምን #ቋንቋ ከዓለም ጋር ትግባባለች? ዱዳ ነው የምትሆነው። #ዩቱብ ሥልጣኔ ነው። #ፌስቡክ ስልጣኔ ነው። #ቲክቶክ ሥልጣኔ ነው። በዚህ ሥልጣኔ ተጠቃሚ ተሁኖ ኢትዮጵያ አጀንዳዋ አደረገችው ብሎ ማቃለል የተገባ አይደለም። #አዋን! ተሳክቶላት ከአደጉት ከበለጸጉት ጋር በቀናነት በዘርፋ አትኩሮት ሰጥታ ነው? ይህ ተገኝቶ ነውን???
በዬትኛውም ሁኔታ፤ በማናቸውም ጊዜ እና ወቅት #አወንታዊነት ይመራ ዘንድ #ቅንነትን መፍቀድ ተስፋን ያለመልማል፤ ጤና አዳምም ነው። ዓለማችን የተቀዬረችው #በአወንታዊ አሳቢወቿ ነው። ኢትዮጵያም የተበጀቸው አወንታዊ ዕሳቤን በአለመለሙ ዜጎቿ #ሊሂቆቿ፤ #ሊቃናቱ ነው። እራስን #አሸንፎ ቅንነትን ምራኝ ማለት ለትውልድ፤ ለአደራ፤ ለማግሥት እና ለትውልድ ይጠቅማል። እራሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅን ነው ወይ? ቅንነትን ለስኬት ኢንበስት ለማድረግ በምን ያህል መጠን ተሰናድቷል???
የወደፊቱ የዓለማችን መሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ነው። ፈጣን ነው የዘመኑ የሥልጣኔ ባቡሩ። አብሮ ለመጓዝ ጣጣ ምንጣጣ የፖለቲካ የሴራ ትብትብ አያሻውም። ቅንነት፤ ብልህነት፤ ዊዝደም እና ትጋት በእጅጉ ይሻል። ለሰው የሚጠቅም ህልም ሰውን አቅፎ፤ ደግፎ ሊሆን ይገባል። በስተቀር በመዳህ ግራጫማ ህይወትን ማስተናገድ ይሆናል። ለትውልዱ ሲታሰብ ከዘመኑ የሥልጣኔ ጉዞ ጋር በቅንነት ቢሆን ……… ስለ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ምጥቀት ሲገለጽም #ሰላም ከሌለ፤ ትውልድ በጦርነት እየታጨደ ሥልጣኔው፤ ቴክኖሎጂው፤ ሳይንሱ #የገደል #ማሚቶ ይሆናል።
ስለዚህ ሰው አፍቃሪ፤ ተፈጥሮ ጠባቂ፤ የመኖር ዋስትና ሰጪ ሥርዓት ለመፍጠር ከራስ መሻት ጋር ማስታረቅ በእጅጉ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ምጥቀት እና ፍጥነት አንፃር ጎጂ ጉዳዮችን እንደምን ሃንድል ማድረግ እንደሚቻል ማሰብ፤ አስቀድሞ ተከላካይ ተቋም መፍጠር ያስፈልጋል።
መልካም ምኞት፤ ቀበጥ ያለ ህልም፤ ቅልጣን የበረከተበት መሻትን ለማግኜት የተቋማት ግንባታ፤ የሰውኛ መንፈስ፤ የሰው ልጅ የመኖር፤ የመመገብ፤ መጠለያ የማግኜት አቅም ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ መትጋት የሚገባ ይመስለኛል። ለህዝብ በሰላም ወጥቶ የመግባት #እርግጠኝነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የለላቀ ሃሳብ ለማፍለቅ ሰላም ያስፈልጋል። ለጠንካራ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስኬት የውስጥ ሰላም ማግኜት ወሳኝ ነው። የአብይዝም ሥርዓት የህሊና፤ የሃሳብ ነፃነት መኖር ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፤ ለፍልስፍና፤ ለሳይንሳዊ የምርምር እና የስኬት ማዕከል መሆናቸውን አምኖ መቀበል ይኖርበታል። ለገቢራዊነቱም መትጋት ይኖርበታል።
ብልጽግና ህልሙን፤ መሻቱን፤ መሪ ከተመሪ አገናኝቶ ለስኬት ለማብቃት #አሰልቺ እና #አስጨናቂ ከሆነው የቁጣ፤ የጭካኔ፥ #የስጋት ዓውድ ህዝብን የማውጣት ጠንቃቃ ውሳኔ የሚያስፈልገው ይመስለኛል። እራስን ማሸነፍ ይቅደም እያልኩኝ ነው በትረ ሥልጣኑን ለተቆጣጠረው የብልጽግና የመሪነት ምዕራፍ ዘመን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ #በቅንነት ቤተኝነት አብረን እንዝለቅ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሸበላ ውሎ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/05/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ