ራህብን ማስደንገጥ፤ ራህብ ዞግ የለውም። ለራህብ ካቴና መለገስ አይገባም።

 

ራህብን ማስደንገጥ፤ ራህብ ዞግ የለውም። ለራህብ ካቴና መለገስ አይገባም።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
የሃኪሞችን ጥያቄ ይሁን ማናቸውም ፍትኃዊ የህዝብ ጥያቄወችን የአብይዝም መንግሥት በጥንቃቄ፤ በእርጋታ እና በስክነት ሊይዘው የሚገባ ክስተት ነው። ሃኪሞች ጥያቄያቸው #ንጹሁ ነው። የተፎካካሪው ወይንም የተቃዋሚው ፖለቲካ የተግባር ራህብ ላይ ሲሆን የትኛውንም ጥያቄ ወደ ራሱ አስጠግቶ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ሃሳቡን ማንሸራሸሩ የማይቀር ነው። ታስታውሱ እንድሆነ የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴን እንደምን የተቃዋሚ ኃይሉ በዘመነ ህወሃት ሃንድል እንዳደረገው ይታወቃል። ከኦሮማራ ንቅናቄ በኋላ የድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ ረብ አለ፤ ከአብይዝም አገዛዝ በኋላ ጸጥ ረጭም አለ።
 
የሆነ ሆኖ ጥያቄ ያላቸው ወገኖች በችግራቸው ገፊነት አደባባይ ሲወጡ የአቅም ሻሞ አያስፈልግም። በመሃል የሚጎዱት #የተጎዱት ይሆናሉ። የሚጎዱት እንዳይጎዱ ደግሞ ሁሉም ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን አመጣጥኖ መከወን ይኖርበታል። አንድ ሃኪም #የሚሊዮኖች እስትንፋስ ነው። አንድ ሃኪም የሚሊዮኖች ቀጣይ ትውልድ #ሮልሞዴል ነው። አንድ ሃኪም የግሎባሉ ዓለም #ዜጋ ነው። አንድ ሃኪም #እናትም #ቤተሰብም አለው።
 
በሌላ በኩል አገር የሚመራ፤ አገር የሚያስተዳድር መንግስት ኮሽ ባለ ቁጥር ከመደንገጥ ጥያቄውን መርምሮ በአቅሙ ልክ መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል። የኢትዮጵያ ቅን እና ትጉህ ሃኪሞች መኖራቸው ችግር ውስጥ ስለመግባቱ ማመልከታቸው #ቂም ሊያዝባቸው፤ ከደረጃ #ሊይስተጓጎሉ፤ ከቀጣይ የትምህርት ዕድል እስኮላር ሊታገዱ አይገባም። ቀጣዩ ይህ ሊሆን እንደሚችል ስለማስብ ነው ይህን የምጽፈው። በዞጋቸው እዬተነጠሉ የበቀል እርምጃ ሊወሰድባቸው አይገባም።
 
ተቀዋማዊ፤ ተፎካካሪ፤ የሥርዓት ለውጥ ፈላጊ በፈለገው ሁኔታ አቅሙን ሊሻማ ቢችልም መንግሥት ቀዳሚ ሃላፊነቱ እሱ በሚመራት አገር ያሉ ህዝብ ነክ ጥያቄወችን በማድመጥ ለመፍትሄው መትጋት ነው ተግባሩ ሊሆን የሚገባው። በፍፁም #ራህብን #በካቴና #ማስደንገጥ አያስፈልግም። 
 
#መሪነት #ዳኝነትም ነው። ስለሆነም በዬትኛውም በኢትዮጵያ የጤና ተቋም የሚሠሩ ቅን ሃኪሞች ምንም ዓይነት ወከባ፤ እንግልት፤ መገለል እና እስር እንዳይገጥማቸው ማዕከላዊ መንግሥት አስቸኳይ ሰልኩራል ሊያስተላልፍ ይገባል። በትዕግሥት በበዛ መቻል የሃኪሞች ሆነ ቀጣይ ተከታታይ ጥያቄወችን በብልጠት ሳይሆን በብልህነት መፍትሄ ሊያበጅለት ይገባል። ለመጀመሪያው ጥያቄ የተገባ መልስ ከተሰጠው ለቀጣዩ ጥያቄ ምላሽ የስክነትን ጎዳና ይጠርጋል። 
 
የታሰሩ ሃኪሞች ይፈቱ። ዘላቂ መፍትሄም ይሰጥ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ ግን እንዴት አደራችሁ ማህበረ ቅንነት።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/05/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
 
"(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአርባምንጭ 3 ዶክተሮች ታሰሩ፡፡ በቅርቡ እየተከናወነ ካለው የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጋር በተገናኘ ሶስት ዶክተሮች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ፡፡ 
 
የታሰሩት ዶክተር ባርናባስ ሳሙኤል፣ ዶክተር መላኩ አልማውና ዶክተር ሀብታሙ ጌታቸው መሆናቸውን የገለፁት ቤተሰቦቻቸው የታሰሩትም በቡድን ሆነው የተነሱትን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ 
 
ከታሰሩት ውስጥ ሁለቱ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ መምህራን ሲሆኑ አንደኛው ደግሞ በአርባምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክተር መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የአርባ ምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አምባሳደር ዱማ ግን ይህንን አስተባብለዋል፡፡
 
በሆስፒታሉ ውስጥ የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን ጥያቄ በውይይት መፍታታቸውን የጠቀሱት አምባሳደር ዱማ ጨምረውም ‹‹ማንም የታሰረ የለም›› በማለት መልስ መስጠታቸውን ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ባቀረበው ዘገባ አስታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ወረዳ በሚገኘው ወረዳ 9 ጤና ጣቢያ ገብሩ ማላክ የተባለ ፋርማሲስት መታሰሩን ዘገባው አስረድቷል፡፡"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?