#ሁለት ጊዜ የተደመጠ #ዕድለኛ ቃለምልልስ።
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም፤
ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"
እንዴት ናችሁ ቤተ ቅንነት። ደህና ናችሁን?
ህወሃት ተሰረዘ፤ ህወሃት #ቀጠነ፤ ህወሃት #ወደለ፤ ህወሃት ነፍሱ ከሥጋው ተለየችም በውነቱ የእኔ አጀንዳ አይደለም። #ተጠቃሚ የነበሩት ሰርክ ይወዝወዙለት። አይደለም የህወሃት መስለሉ - #መሰልሰሉ፤ ጎልቶ ቢወጣ በለስ ቀንቶት አልደነቅበትም። ለምን?? የምፈልገውን ፍላጎቴን ጸጥ ባለ ዊዝደም ገብ ሂደት ሥልጣኑን ፈቅዶ እና ወዶ ከማዕከላዊ መንግሥት ገዢነነት ተሰናብቷል። እራሱም ድምጽ ሰጥቶ። ለዚህም ነው ሙሉ ፯ ዓመት ጸጥ ብዬ እምከታተለው። ከሚወቅሱትም ሆነ፦ ተስፋ አድርገው ምልሰቱን ከሚመኙትም፤ ከሚሞግቱለትም ወገን አልነበርኩም።
ህወሃትን በዘመነ #ጋሜዬ ገና ጩጬ ሳለሁ፤ በፖለቲካ ሆነ በዕድሜ የማውቀው ድርጅት ነው። ሻብያንም እንዲሁ። የሆነ ሆኖ ያን "የቆጡን አወርድ ብላ" እንደሚባለው #መታበዩ መራራ ስንብቱን አጎናጽፎታል። "አልጠግብ ባይ" ምን ሲል ያድራል እንደሚባለው። ዕድሜ #ለሃምሌ ፭ቱ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ክስተት ማብቃቱን ዓውጆልናል። በሌላ በኩል መቼወንም ዘመን ህወሃት አውራ የዞግ ፓርቲ ሆኖ #ራሱን ችሎ እንደማይመጣም እርግጠኛ ነኝ። ስለሆነም ቅንጣት አቅም አላዋጣም።
ህወሃት ከሌላ ተቋም እራስ ሊወረድ ግን ይገባል። #መክሰስም፦ #መወንጀልም ካለበት ትዕቢተኛውን የወቅቱን የትግራይ ክልል መስተዳድር የአቶ #አባይ ወልዱን አስተዳደር ነው። አሁንም አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ መስተዳድር ፕሬዚዳንት ስለሆኑ የአገር መሪነት ስሜት አላቸው። ሲናገሩ ጥንቃቄ የሚጎድላቸው ለዚህ ነው። ከሌሎች የመስተዳድር ፕሬዚዳንቶችም እሳቸው እጬጌ እንደሆኑ ያስባሉ። ይህ በሁለመናቸው በማዬው #መኮፈስ የተገነዘብኩት ግብረ መልስ ነው። #አያዋጣም።
ከሥርዓት ውጪ የሆነ #የአናርኪዝም ሂደት ነው። የሆነ ሆኖ ውስጤን የሚያሳስበው በህወሃት ውጣ ውረድ የእቴጌ የትግራይ ህዝብ በተለይ ምንም የማያውቁ ህፃናት #ለአቅመ ፖለቲካ ያልብቁ ቅዱሳን ልጆች በእጅጉ ያሳዝኑኛል።
ትናንት በ12/05/2025 በብልጽግና ገብ ሚዲያወች ጊዜ ይሰጠው ሲሉ አዳምጫለሁ። ለጥሞና ጊዜ። ጥሞና እና ህወሃት? ቃሉን ያውቀዋል? ዲስፕሊኑን ህወሃት ሊወጣ ሊለወጥም???? መንግሥታችን ይህን በማድረጉ አይጎዳም ዓይነት ነበር ትንታኔው። ይህ የአብይዝም የመንግሥታቸው ፍላጎት ሊሆን ይችላል። አንጀቴ ተንሰፍስፏል እና ሽፋን ስጡልኝ፦ ለቀጣይ የማሻሻያ እርምጃዬ ተብሎ ሊሆን ይችላል። ይህም ቢሳካ ለእኔ ምንም ነው የህወሃት ጉዳይ አጀንዳየ የሚሆነው አገርን የመምራት ዕድል ከገጠመው ብቻ ነው።
የሆነ ሆኖ የህወሃት እስትንፋስ ይቀጥል አይቀጥል አጤ ሂደት ኤሎሄ ላይ እያለ፤ ብልጽግና የማንዘርዘሪያ #መንሹ ይዞ ብቅ ብሏል። ሁለት ክስተት በመንትዮሽ። አንዱ ይራዘምለት የሚል መለከት፤ ሌላው ገመናው ይዘረጋገፍ እና ከፈን አልባ #ይሰጣ።
ይህ የህወሃትን #ህዳሴ ለሚመኙ መካች፤ ሞጋች ጭብጥ ይመስለኛል። #ሚዛን የራስ ነው። በዚህ ረግረግ ውስጥ ራስን ነክሮ የህወሃት ዕድሜ ለማኝ መሆን የቀደመን፤ ምን አልባትም ብቁ የፖለቲካን ሰብዕና #ድብ ያደርጋል። አቋሙንም #ድብድባ ገብ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል። ሞት እና ወርቅ ፍለጋ፤ ዘረፋ እና ጭካኔ???
እኔ እምለው አለኝ በዘመነ ህወሃት ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ፍቅርም ሲያልቅም ትእግስት ይሰደዳል እል ነበር። በዚህ ቃለ ምልልስ አፍቅሮተ - የህወሃት ቲም ከመራራ ሃቅ ጋር ፊት ለፊት መጋጠማቸው አይቀሬ ነው። በሌላ በኩልም የህወሃትን አቅም ከፋኖ መንፈስ ጋር ለማዛመድ ለሚሹትም የሰላ ፋስ ነው። ቃለ ምልልሱ ክፍል ፩ ነው። ክፍል ሁለት ምን ሊሆን እንደሚችል ባላውቅም ይህ ቃለ ምልልስ አፍቅሮተ ህወሃትን ሆነ እራሱ ህወሃትን የያዘውን የሃሳብ ጦርነቱን ወደ መቋጫ የሚያሻግር ቃለ ምልልስ እንደሆነ ነው የተረዳሁት።
ቃለ ምልልሱ #ክስተታዊ ነው። ቢደመጥ አቅምን፤ ክህሎትን፤ ጸጋን በቅጡ ማስተዳደር የሚያስችል ልዩ ሽልማት ይመስለኛል አቶ ጌታቸው እረዳ የሰጡት #ጥልቅ መረጃ። የስሜን ጎንደርን ጥቃት የመሩት ጄኒራል ምግበ፥ በጭና የአማራ ንጹሃን ብቻ ሳይሆን ተጋሩም የሞት ማህበርተኞች ነበሩ ሲባል ሰምቻለሁኝ። የዛ ቀጠና የጦሩ መሪ በተመሳሳይ ወቅት የነገረ ወርቅ ንግድ #ቤተኛ መሆኑን ስሰማ እንደ ዘመኑ የትውልድ አባልነቴ ሰቀጠጠኝ።
ሌላ ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ያሉ ባለስልጣኖች በዚህ የፍቅረ ንወያ ሂደት ይለፍ በመስጠት ሁነት መሳተፋቸው አስደንግጦኛል። አንድ ህዝባዊ ኃላፊነት የተሰጠው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተግባሩን ሲከውን ቅድሚያ የሚሰጠውን አለማወቅ፤ ለወደፊትም ለሌላ አደጋ የሚያጋልጥ ይመስለኛል። ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ለማስታረቅ በዚህ አግባብ ከባድ ይመስለኛል። ጥላቻም፤ ቂምም ሳይኖር ግድፈቱ ግን መታረም ይገባል። ኢትዮጵያ አንድ ማዕከላዊ መንግሥት፤ ወጥ አመራር ካላት።
ሌላ ህወሃት የከሰረበት ሁነት አቶ ጌታቸው እረዳን ከመንፈሱ ማውጣቱ ነው። በአንፃሩ ብልጽግና ተጠቅሞበታል። ቀጣይ ሂደቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ባላውቅም። ጠያቂው እና ተጠያቂውስ??? ዳኙት። ተጠያቂው ጥያቄወችን አቅጣጫ ሲያስዙት ተመልክቻለሁኝ። በዚህ ውይይት የኢትዮጵያን ፖለቲካ የውስጥ አካል የሚታይበት ብሄራዊ ጉዳይ ነው። እንዴት ግን ዘመኗን ኢትዮጵያ አለፈችው? እያንዳንዱ ጉዳይ ብዙ በጣም ብዙ ፍቺ የሚጠይቁ ነበሩ።
• #ለአደረጃጀት መርህ …
ያው ህወሃት ይሁን የ፷ወቹ ፖለቲካ ርዕዮታቸው ሶሻሊዝም ገብ ነው። ከፊት እና ከኋላ ቢጠቀሙበትም። አብዮታዊ ዴሞክራሲ// ዲሞክራሲያዊ አብዮት ቢባሉም እንደማለት። ብሄራዊ ይሁኑ የዞግ የፖለቲካ ድርጅቶቹ ማርክሲስታዊ ነበሩ። አደረጃጀታቸው ላይ ወጥ ሁነት አላቸው። ጉባኤ፤ ማዕከላዊ ኮሜቴ፤ ፖለቲ ቢሮ የሚባሉ አላቸው። ደንብ፤ ማኒፌስቶ፤ መሪ ዕቅድ የሚል መርህም አላቸው። የአደረጃጀት። ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚባል። ተቋማቱን አቋሚው ትንፋሽ ለጋሹ ዲስፕሊኑ ነው።
አቶ ጌታቸው ረዳ በቀጥታ የማዕከላዊ ኮሚቴ የሆኑበት መንገድ ሳዳምጥ፤ ህወሃት መርኽ ገብ ድርጅት እንዳልነበረ ተረዳሁኝ። ግን እንደምን ያን ያህል ዓመት ገዛ??? አንድ ሰው የማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ለመሆን ውክልናውን የሚሰጠው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤው ነው። ለመዕከላዊ ኮሜቴ አባልነት የግድ በአባላት ከቅላላ ጉባኤ ተመርጦ አልፎ መምጣትን ይጠይቃል። ምርጫው በድርጅታዊ ሥራ ሊከወን ይችላል። ሂደቱ በሚስጢርም፤ በግልጽም ሊሆንም ይችላል።
ይህ ሳይከወን ነው በፈቃደ ግለሰብ ሊሆን ይችላል አቶ ጌታቸው በቀጥታ የህወሃት የማዕከላዊ ኮሜቴ አባል የሆኑት። አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቶ መከወን ይቻል ነበር። ወደ ፖሊት ቢሮ ለመሸጋገር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ይጠይቃል። ግን ያ ሰብዕና መነሻው ጉባኤ ነው። ጉባኤው እራሱ ከመሰረታዊ አስኳል፤ ወረዳ፤ አውራጃ፤ በዘመነ ህወሃት ዞን መሆን አለበት በዚህ መልክ ነው የአካላት አወቃቀር። አቋራጭ ሁነት ግን??? ስለሆነም ከሁለት በላይ ጥሰት ነው የተከወነው። ይህ ሂደት ለእኔ ንፁህ አናርኪዝም ነው። ስለሆነም ህወሃት መር ድርጅቶች ሁሉ ውስጠ ህይወታቸው #በጥሰት አመራር ነበር ማለት ነው። ስለዚህ ህወሃት ያልመነመነ ማን ይመንምን???
የኔወቹ ክፍል ሁለት ይጠበቃል። ስንት ትውልድ መኖሩን ያጣበት ነውና። ህወሃት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግብረ መልስ ይሰጣል እና ክፍል ፩ ብታዳምጡ ጥሩ ነው። እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ሠራዊትን በሚመለከት ከወቀሳ፤ ነቀሳ ነፃ ያደረጉት ይመስለኛል በጉዳት አንፃር የሰጡት መግለጫ አቶ ጌታቸው እረዳ፥ እንደ ሰው ጥንቃቄው አይከፋም። ቀጣይ ህይወትም አለና።
ሰሞናቱን ሰከን ያሉ ውይይቶች፤ ቃለ ምልልሶች እያዳመጥኩ ነው። ጥሩ ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/05/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ