የታሰሩ ጋዜጠኞችን በሚመለከት ልዩ መንፈሳዊ አጽናኝ ስጦታ ከባቲካን ተደመጠ። CPJ አጋዥ እዮር ላከለት። የልብ የሆነ ቅድስና።

 

የታሰሩ ጋዜጠኞችን በሚመለከት ልዩ መንፈሳዊ አጽናኝ ስጦታ ከባቲካን ተደመጠ። CPJ አጋዥ እዮር ላከለት። የልብ የሆነ ቅድስና።
«አዲሱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ»
 
13 ግንቦት 2025, 07:22 EAT
 
«አዲሱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ቫቲካን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር በተገናኙበት ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ጥሪ አቀረቡ።»
 
«ጳጳሱ "እውነትን ፈልገው ለመዘገብ" ሲሉ ለእስር ለተዳረጉ ጋዜጠኞች ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽ፣ የሚደርስባቸው ስቃይ "የአገራትን እና የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ህሊና የሚፈትን ነው" ብለዋል።»
 
«የፕሬስ ነጻነት መጠበቅ አለበት ያሉት ፖፕ ሊዮ 14ኛ፣ መገናኛ ብዙኃንም ይህ "ውድ የሆነው ስጦታ" የመናገር ነጻነት መጠበቅን ማረጋገጥ አለባቸውም።»
 
«ኮሚቲ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ እንደሚለው ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት 361 ጋዜጠኞች ታስረዋል።
ባለፈው ሐሙስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ሆነው የተመረጡት ሊቀ ጳጳስ ጨምረውም ጋዜጠኞች በዓለም ላይ ያሉት ኢፍትሃዊነት እና ድህነት ትኩረት እንዲያገኙ ሚናቸውን እንዲእጡ ጥሪ እርበዋል።»
 
«መገናኛ ብዙኃን በሚከፋፍሉ ወገንተኛ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከማተኮር ይልቅ እውነትን በመዘገብ "ለጽንፈኝነት እና ጥላቻ" መድረክ እንዳይሰጡ አሳስበዋል።»
 
"መልዕክታችንን የምናስተላለፍበት መንገድ በመሠረታዊነት ወሳኝ ነው፤ የቃላት እና የምሥሎች ጦርነትን ባለመቀበል፣ የጦርነት አቅጣጫን መቃወም አለብን።"
 
"ኃይል እና ጩኸት የሞላበት መልዕክት አያስፈልግም" ያሉት ጳጳሱ "ከዚያ ይልቅ መልዕክቶቻችን ድምጽ የሌላቸውን ደካሞች ድምጽ የሚያስደምጡ እና የሚሰበስቡ መሆን አለባቸው" ብለዋል።»
 
«አዲሱ ጳጳስ በተጨማሪም ለታዳሚዎች ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ያላቸውን ስጋት በማንሳት ቴክኖሎጂውን "በኃላፊነት እና በብልሃት" መጠቀም እንደሚያስፈልግ ለታዳሚዎቹ ተናግረዋል።»
 
«ጋዜጠኞች ሰው ሠራሽ አስተውሎት "ለሰው ልጅ ሁሉ በሚጠቅም ሁኔታ ጥቅም" ላይ መዋሉን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።»
«በዚህ መድረክ ላይ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ንግግር ያደረጉት በአብዛኛው በጣልያንኛ ሲሆን፣ ንግግሩን ሲጀምሩ ወደ አዳራሽ ሲገቡ ስለተደረጋላቸው ሞቅ ያለ ጭብጨባ በእንግሊዝና ቀልድ ጣል አድርገዋል።»
አዲሱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ - BBC News አማርኛ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?