ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እኔም #ጦርነት #በቃንን! በድፍረት የምገልጸው የውስጤ #ቃለ #ምህዳኔ ነው። ዘገባው #የBBC ነው

ምስል
  እኔም #ጦርነት #በቃንን ! በድፍረት የምገልጸው የውስጤ #ቃለ #ምህዳኔ ነው።   #ግንንንንንንን -----------------ግን ኢሠመኩ #ትርታው አለችን? #ነፍስ #ይማር #ብዬ ነበር።    በነገራችን ላይ ዘገባው #የBBC ነው። የጭንቅ ሂደቱን ዘገባ ሊንኮችን አያይዤ አቅርቤያለሁ። ሰሞኑን ስለፃፍኳቸው ዕይታ መሠረት ስለሆነ መረጃው። የመነሻ ዘገባውን ግን ሙሉ ዝርዝሩን #የBBC ከሥር አቅርቤያለሁኝ። ዛሬ #የድሮን ዘገባ አለ።    የጦርነቱ ሂደት እያደገ መሆኑን ያሳይ ይመስለኛል። " #ጦርነት በቃን!" የሚሉም ሰልፎች በቲክቶክ ላይ አይቻለሁኝ። ይህ የመላ ኢትዮጵውያን ድምጽ እንዲሆን እመኛለሁኝ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ሥርጉትሻ 31/01/2026 =====================///////==============---- «በአላማጣ እና ኮረም የተከሰተው ምንድን ነው?» BBC. • https://www.bbc.com/amharic/articles/c5y5z0360qro 30 ጥር 2026 "የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ኃይሎች ከአላማጣ እና ኮረም ከተሞች መውጣታቸውን እየተዘገበ ባለበት ወቅት ነዋሪዎችም ለደኅንነታቸው በመስጋት እየሸሹ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገለጹ። ግጭት ይቀሰቀሳል በሚል እና ታጣቂዎች "የሚወስዱት እርምጃ ስጋት ፈጥሮብናል" ያሉ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች አካባቢዎች በመጓዝ ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአላማጣ ነዋሪ እንዲሁም የቀድሞ የአካባቢው ባለሥልጣን እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር ሥር የአላማጣ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ዝናቡ ደስታ በከተማው ውጥረት መኖሩን እና ነዋሪዎች እየሸሹ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀ...

ባለቤት አልባወቹ የኢትዮጵያ ህፃናት #እምታ #በጦርነት፤ በመፈናቀል #ወላፈን #ከትናንት እስከ-ዛሬ የህፃናት #የምጥ - #ማጥ።

  ባለቤት አልባወቹ የኢትዮጵያ ህፃናት #እምታ #በጦርነት ፤ በመፈናቀል #ወላፈን #ከትናንት እስከ-ዛሬ የህፃናት #የምጥ - #ማጥ ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   አሳዛኙ ገጠመኝ ስለ #ህፃናት መብት የሚሞግት ተቋም የለም። መስኪን ለምኛት ነበር በብዕሬ። ቢያንስ የጉዳታቸውን ደረጃ እንኳን ማወቅ ብልሃዊ ጉዞ ነበርና። አልሆነም።   #ምዕራፍ ፲፰    #ጠብታ ።   በእያንዳንዱ ጸረ - ተፈጥሮ፤ ጸረ - ሰው ቀውስ ሁሉ የህወሃትም #የሥልጣን መሻትም አለ። ይህንን የቀውስ ትልም ለማክሸፍ ባለሥልጣኑ ብልጽግናም አቃሎ በማዬት ማገዶው ህዝብ ሆነ፤ መሞከሪያ ጣቢያው #ህፃናት ሆኑ።    አቤቶ ብልጽግና እንደኛው #ስሞታ አቅራቢ ነው። ቆፍጠን ብሎ አስቦ፤ ጉዳዩን አጥንቶ ሥርዓት ማስያዝ የሚገባውን ወሳኝ የፖለቲካ ዕድምታ በንቀት፤ በቸለልተኝነት፤ የትም አይደርሱም "በነዋል፤ ዱቄት ሆነዋል፤ አንድ ሁለት ሽፍቶች" እያለ ብቻ ሳይሆን የህወሃትን ሆድ ዕቃወችን #ቁልፍ እና ወሳኝ ቦታ እዬሰጠ የብዙኃን የዕንባን ትዕይንት ፬ኪሎ ላይ ሆኖ እንደ እኛው ይመለከታል።    ለአቤቱ ብልጽግና ዳሩ ሲታረስ ማህሉ ዳር እንደሚሆን ይጠፋዋል ብዬ አልገምትም፤ ጎዳናውን ሳስተውለው…… 1) ህዋህትን በዲፕሎማሲው ማህበረሰብ #ለማሳጣት የህዝብ ተስፋ መማገድ አለበት።    ይህ ነው የብልጽግና ቀመር። ሁልጊዜ ዕድሉን መከንበል፤ ዛሬ እኮ ህወሃትን "አትንኩብን"" የሚሉ፤ ትናንት በጸረ - ህወሃት አቋማቸው የሚታወቁ ወገኖች እዬበረከቱ ነው። ህወሃትን አምኖ የአማራ ህዝብን ዕምቅ አቅም ገፍቶ፤ ከኤርትራ ጋር የነበረውን ንፋስ አይገባውም የተባለ የቀለበት ሥርዓት ት...

#መጠሪያችን ማን ይሆን ዘንድ ከቶ ፈቀድን???? #ጦርነት እኮ #የሞት #ዓዋጅ እኮ ነው። ይህ በፍቅር እፍ ያደርገናል።

  #መጠሪያችን ማን ይሆን ዘንድ ከቶ ፈቀድን???? #ጦርነት እኮ #የሞት #ዓዋጅ እኮ ነው። ይህ በፍቅር እፍ ያደርገናል። ጦርነት እንደ እኔ #ቤርሙዳ #ትርያንግልም ነው። ይህ በመውደድ ያከንፈናል? ግን እኛ ምንድነን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰   #ግን እኛ አድራሻችን ፍጥረተ ነገራችን ከያት ይሆን? #ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዮን ወገን ያለን --- - እኛ #ለአንድ ሰዓት እንኳን የሚያቆይ የለት ደራሽ የምግብ ክምችት የሌላቸው በሺህ የሚቆጠሩ ቤተሰብ ያለን --- - እኛ --- #የሚሠሩ እጆች እያሏቸው በራህብ ምክንያት ቀያቸውን ትተው የሚሰደዱ ሺህ ወገን ያለን --- - እኛ #ልቀቁልን ተብለው ከባዕታቸው የተነቀሉ ሁነኛም የሌላቸው የሚሊዮን ዕንባ ቤተኞች የሆኑ ወገኖች ያለን --- - እኛ --- #በየዘመኑ በፖለቲካ ቀውስ የሚሰደዱ፤ የሚታሠሩ፤ የሚበተኑ ቤተሰቦች፤ የሚፈርሱ ጉልቻወች ያለን -- - እኛ --- #በኑሮ ደረጃ በነፍስወከፍ ገቢ ከዓለሜ ይሁን ከአህጉራችን መጨረሻወቹ የአፍሪካ ተርታወች ውስጥ የምንገኜው -- እኛ #በተፈጥሮ ይሁን በሰው ሠራሽ አደጋወች የወጣትነት ተስፋቸው ተጎሳቁሎ ሙሉ አካላቸውን ያጡ በርካታ ልጆች ያሉን ---- እኛ --- #በአንድም በሌላም ሰርክ የትርታችን ትንፋሽ ሞት፤ መርዶ ስንቃችን እንዲሆን የተፈረደብን የዚህ ትውልድ ቤተኞች ---እኛ --- #ለወቀሳ መቅድምነትን የምንሻ፤ ለመወቀስም ሽሽትን የምናጣድፍ እራሳችን በራሳችን የተቃረን - እኛ ……- #ለውዳሴ ፤ ለመሞካሸት፤ ለጭብጨባ ግን በጥድፊያ ላይ የምንገኝ ---- እኛ #የትውልድ ማገዶነት ፈጽሞ የማይሰለቸን --- እኛው -- #ወጣት ጡረተኛ አብዝት የሚናፍቀን -- እኛ #በግለሰብ ሰብዕ...

ህወሃት እና የአዝመራ #ዘረፋው በወርሃ የካቲት ትውፊቱ ነው። ህዋህታዊነትስ - ምን #ጠቀመ፤ ምን አከሰረ?

  ህወሃት እና የአዝመራ #ዘረፋው በወርሃ የካቲት ትውፊቱ ነው። ህዋህታዊነትስ - ምን #ጠቀመ ፤ ምን አከሰረ?   "ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘለዓለም ሲያለቅስ ይኖራል።" መጥኒ ላንች እቴጌ ጎንደር። ልብ በአቅል ግዢ ከአጤወችሽ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰። ዘለግ ያለን ትዕግሥት እና ማስተዋል የናፈቀው የወግ ገበታ ነው ለማህበረ ቅንነት።    #መቅድመ ፍሬ ነገር።   ጤና ይስጥልኝ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ከእኛ ቅዝቃዜውም ለክፋ አይሰጥም። ካናዳ እና አገረ አሜሪካ ያሉ ወገኖቻችን ከቶ እንደምን አድረው ይሆን?   በውነቱ ህወሃትን በሚመለከት ምንም ለማለት ፈጽሞ አልፈልግም ነበር። ከምል "ሙያ በልብን" ብከውን የተሻለ ቀና መንገድም ነው ብዬ አምናለሁኝ። ለዛውም እኔ የልቤ ደርሶ፤ መሻቴ ተሳክቶ #የጃርት ጉባኤው የህወሃት ተንጠራርቶ፤ ተወራኜቶ #አራጦ የመግዛት ዘመኑ #እርሾ አልባው ክትመቱን ከማዬት በላይ መታደል ስለለ ግራ ቀኙን በትዝብት፤ በዝምታ ማየቱ ምርጫያ ነው።   ነገር ግን ዘመኑን ሁሉ በድንጋጤ፤ በጭንቀት እና በስጋት እንዲኖር የተፈቀደበት፤ የተፈረደበትም ሁነትን አስመልክቶ ለአዲሱ ትውልድ ትንሽ መረጃ ብሰጠው አይከፋም በሚል ነው አመጣጤ። ህወሃትን መንገድ መሪነት የተቃጠለ፤ ኤክስፓየርድ ያደረገ የአስተሳሰብ ድህነት ነው። የህወሃት ጉዞ በየትኛውም ሁነት ሊገታ ይገባል።   " #ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል፤ ዘለዓለም ሲያለቅስ ይውላል።"   ወርኃ የካቲት የስሜን ጎንደር ገራገር ንጹህ ገበሬ ዓመቱን ሙሉ የለፋበት አእዝርቶቹን ሳይዘራ፤ ሳያርም፤ ሳያጭድ፤ ሳይወቃ የኖረ #ሰ...