ልጥፎች

ቅዱሱ ሙሴ አብዩ አሜኑ እንሆ ዛሬም ዲያቢሎስን ድል አድርገ!

ምስል
የአብዩ አሜኑ ገድለ ድርሳናት እነሆ ታዬ! ቅዱሱ ሙሴ እንሆ ዛሬም ዲያቢሎስን ድል አድርገ!                    „ ጥብብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባቱንም ምሰሶዎች አቆመች።“                  (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ©ሥላሴ 01.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·        ከዘመ ናት ህማማት ወደ ሰሞነት ትፍስህት። እንቅልፍ አልተኛሁም። እንዲህ ነኝ እኔ በማንኛውም ወሳኝ ጉዳይ ላይ ስጋተኛ እና ፈሪ ነኝ። ስለሆነም ከመተኛት መዝምሩ ዳዊትን ሳነብ ማደሩን መረጥኩት። ያኖረኝ የልብ አምላክ ዳዊት ቅኔ ነው። የሚገርመው ሰውነቴ ንቁ ነው። እንቅልፉ በኗል። እንሆ ይህም ምኞቴ ተፈጸመ „አድርገህልኛል እና ለዘላለም አምሰግንሃለሁ።“  (መዝሙር ምዕራፍ ፶፩ ቁጥር ፱) https://sergute.blogspot.com/2018/07/blog-post_76.html „አዲስ ቅዱስ ጸበል በመንፈስ ሲፈልቅ የተዋህዶ ተጋድሎው ሊገፋው አይገባም“ የሚል ብፁዕን አበው አገር መግባት አለባቸው፤ መሞት ካለባቸውም ሄደው የሰማዕትነት ጽዋውን ይቀበሉ፤ ይህን የምርቃት ታምራት ሊገፉት አይገባም ብዬ ጽፌ ነበር።  ታዳሚዎቼንም በዬፌስ ቡካችሁ ለጥፉልኝ ብዬ ተማጽኜ ነበር። ምኞቴ እንሆ ተፈጸመ። በስልክም እስከ ንግቱ 9 ሰዓት ድረስ ስወያይ ነበር ቁጭ ብዬ ያድርኩት። መንፈሴን ከተጋራችን ነፍስ ጋር። መወሰን ያልደፈረ መኖርን አይጀምርና። ቅደስት ተዋህዶ በባዕቷ ትውፊት እና...

ታላቅ የምሥራች ከኤርትራ መንግሥት ተደመጠ!

ምስል
እንሆ በአንድ ወር ውስጥ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የልቤን አደረሱልኝ። አምላኬም ፍላጎቴን አዳመጠ። ተመስገን! „ወዳጅህን ሂድና ተመለስ ነገ እሰጥሃለሁ አትበለው፣ በጎ ነገር ማደረግ ሲቻልህ።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፱) ከሥርጉተ©ሥላሴ 01.08.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        ሰላምታ። ጤና ይስጥልኝ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ እንደምን ሰነበቱ? እነኛ ደስ የሚሉ ፍቅር የሆኑ ቤተሰቦቸዎትስ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ዛሬ ዘሃበሻ የሚባል ድህረ ገፅ ላይ አንድ መልካም ዜና ሰማሁኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ እኔም አምደኛ ነበርኩኝ። ኤርትራ የሚገኘው ባቶ ዳውድ ኢብሳ ለሚመራው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅት ሁለት አዎንታዊ አማራጭ እንደሰጡት አዳምጫለሁኝ። እጅግ አድርጌ አመሰግነወታለሁኝ። ይህቺ የቡኒነት ወላዊነት የዘመናችን የልባዊነት እኛዊነት ልዩ እዮራዊ ሸልማት ናት። ቀደም ብዬም ምን ያህል መልእክቴ እንደደረሰ ባላውቅም፤ ይህኛው አዲስ የጀመርኩት ብሎግ ስለሆነ ጥቂት ቅኖች ብቻ ስለሆነ የሚታደሙበት ላያገኙት ይችሉ ይሆናል፤ ከኤርትራ መንግሥት በዚህ ስምምነት ከምፈልገው መንፈሳዊ ጉዳይ ትልቁ እና ዋንኛው ማንኛውንም የኤርትራ መንግሥት ያስታጠቀቻቸው የነፃነት አርበኞች ወደ ኢትዮጵያ እንመለሳለን ሲሉ ትጥቅ እንዲያስፈቱ በታላቅ ትህትና ጠይቄ ነበር።  አሁን የልቤን አድርሰውልኛል እጅግ አድርጌ አመሰግነወታለሁኝ። ይህ የኢትዮጵያ ሰላም መሆን ለኤርትራም በ እጅጉ ያስፈልጋታል። ስለዚህ ኤርትራ ለራሷ ሰላም እምትሳሳ ከሆነ ማደረግ የነበረባት ቀዳማዊ እርምጃ ይህ ነበር። ·        ማመ...

የማህበረ አብይ ጉባኤ ... መሪ እና ፕሮቶኮል ሹም።

ምስል
አንጄትን ቅቤ ያጠጣው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አገላለጽ ነው! „ጥበብስ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፱ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 31.07.2018 (ከገደማዋቷ ሲዊዘርላንድ) በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሰሞናቱ የማህበረ አብይ ጉባኤ የመድረክ አመራር በርካታ ዕይታዎችን አነበብኩኝ። የፕሮተኮል ሹመነትም ተደማሪነትም አለበት። የሆነ ሆኖ ያው በእሱ ዙሪያ እጅግ በርካታ ውዝግቦችን ብራና አስተናግዳለች። እሱን በሚመለከት የተፈለገው ቢባል እኔ በራሴ ውስጥ ነበርኩኝ።  የወጣሁት ከእሱ ሰብዕና አልፎ ትዳሩ ላይ ወቀሳ ሲሰነዘር ግን በህግ አምላክ ብያለሁኝ። ጽፌማለሁኝ። በጣም መጠን አልፎ መሄድ አያስፈልግም። ትዳር ላይ የሚወሰድ ምንም ነገር የለም።  ትዳር ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው አይደለም። የሰውም የእጅ ሥራ አይደለም የጣና ዘገሊላ ጉዳይ። እንዲያውም የሚስጢሩን ልቅናውን ብናወቀው ሌላ ዘሃ መጎተት ባላስለፈገን ነበር። አገርም በአህቲ መንፈስ ትጸድቅ ነበር። „ጋብቻ ቅዱስ መኝታውም ንጹህ“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ፤ ቢያንስ ይህ የህይወት ቃል አብሶ የተዋህዶ ልጆች ሊያከብሩት ይገባል። ወቃሽ ጸሐፊው የተዋህዶ ልጅ ስለነበሩ።  ከዚህ በመለስ አሁን ትልቅ ቦታ ስለተሰጠውም ነው ሊያሰኝ አይችልም 7ኛ መጸሐፌ "ርግብ በር" ላይ መልካም ነገር ስላገኘሁ ሃሳቡን ለማስረጃነት ተጠቅሚያለሁኝ። እኔ ቅንነት ባለበት ቦታ ሁሉ ዳር ደንበር የለኝም። ወደ ጉዳዬ እንብርት ስገባ መቼም ፈታኝ ነው፤ አደባባይ ላይ የተሳታፊን ጥያቄ ማስተናገድ። እኔ አይቼ አላወቅም በሰለጠነው ዓለም። አሁን የሆነው እንደዛ ነበር። ኢትዮጵያ ግን በዛ ሰሞን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ...

መሻገር እና መሸጋገር የአምክንዮ ልዩነት አላቸው።

ምስል
ስንፈጠር  መቻልም መቻቻልም ተሰጥቶናል። „በግዞትም ቤት አደባባይ ታሥሮ ሳለ የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ሲል  ወደ ኤርምያስ መጣ፣--- ሂድ ለኢትዮጵያዊው አበሜሌክ እንዲህ በለው፣-  የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣--- እንሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያን ቀን በፊትህ ይፈጸማል። በዚያ ቀን አድንሃለሁ ይላል፤ እግዚአብሄርም በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች አንጂ በሰይፍ አትወደቅም፣ በእኔ ታምነሃልና ፣ ይላል እግዚአብሄር። (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ  ፴፱ ከቁጥር ፲፭ እስከ ፲፰) ከሥርጉተ ሥላሴ 31.07.2018 (ከገዳማዊቷ የደም ገንቦዋ ሲዊዝሻ።) ·        እፍታ። አሁን ያለው ሁኔታ መሻገሪ እንጂ መሻገር አድርገው የሚመለከቱት ወገኖቼ አሉ።  ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ስለደከመኝ አሳደርኩትኝ። በፈለገ ሁኔታ ቢሆን የሚኒያፖሊስን የስብሰባ ድባብ ሳላዳምጥ አልተኛም ብዬ እሰከ እኩለ ሌሊት ቆዬሁኝ። ቅድመ መሰናዶው መስፍኔ ፈይሳ እንደ ዲሲዊ ሲያስቃኘኝ ቆዬ። ያዘንኩት ግን ለታታሪው የእርቅ ጌታ ለመስፍኔ ፈይሳ ቅድሚያ አለመሰጠቱ ነበር። የሚገርመው ትንሳኤዋን ልዕልት ልጁን ይዞ ነበር ሲንገላታ ያዬሁት። ልጅ የያዙ፤ ጤናቸው የጎደለ ደካሞች፤ ነፍሰጡሮችን በሚመለከት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ ነበር፤ በዚህ ዘርፍ የዲሲውን አድንቄያለሁኝ። አዛጋጆች ከOMN ጋር የቅድምያ ቃለ ምልልስ በኦሮምኛ እና በአማርኛ አድርገው ነበር። ምቾት የሚሰጥ አልነበርም። በበዛ ሁኔታ የመነጠል ተደሞ ነበረበት። በዚህ በመነጠል መንፈስ ...