ልጥፎች

ነሐሴ አንድ ቀን ስተራሳት አንተን ገድለኸዋል።

ምስል
ሰማዕትነት ያፈራው እሸታዊ ማንነት። „እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሄር የዘራቸው ነፍሳት ፈጥነው ይነሣሉ፤ እሱ ሰውን በውነቱ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ፈጥሮታልና፤ በምታድን ቃሉ ፈጥኖ ያስነሣቸዋል፤ ማስነሣቱን አያዘገይም።““ መቃብያ ቀዳሚዊ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ ገድለ አማራ በባህርዳር ደም የተገበረበት የአማራ የማንነት ታአገድሎ ዕሴት! አማራ የግፍ ቀንበሩን በበቃኝ ታገድሎውን አህዱ ያለበት የሀምሌ 5ቱ 24ቱ ተጋድሎ ጎጃምን በቅኔያዊ ደሙ አንድ ያደረገበት ዕለት ነው ነሃሴ 1 ቀን። እንሆነ የተጋድሎው የህዝበ ውሳኔ ዕወጃ ሰነድ በደም ማህተም የተዘከረበት የደም ዋጋ ቀን። „እሱ ሰውን በውነቱ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ፈጥሮታልና፤ በምታድን ቃሉ ፈጥኖ ያስነሣቸዋል፤ ማስነሣቱን አያዘገይም።“ የማዳን መለከት ከእዮር የተላከልን ሰሞናት ነበር ከሀምሌ 5 አስከ ነሀሴ አንድ 2008 ድረስ ያለው።   ዕሴታዊ የደም ግብር የድንጋጌ ዕለት መስከረም 1 ቀን። ትንግርት በደም ቀልሞ ተጋድሎው ጽናዊታዊ ድልድይ የተዘረጋበት ቀን ነበር ነሃሴ 1 ቀን 2008። ይህ ቀን ለአማራነት ፍጹም ልዩ ቅዱስ ቀኑ ነው። ሰማዕትነት ፈቅደው ሲቀበሉት ግብሩ በቅሎ - ጸድቆ - አስበሎ እንዲገኝ ቃል ኪዳን የሚታደስበት ስለሆነ "የበሉበት ወጪት ሰባሪ ላለመሆን" የተግባር ቋጠሮን በቆረጠ እና በወሰነ አቋም ለማዝለቅ ውል ከእነዚያ 76 ሰማዕታት ጋር ጎሎጎታን የምናስብበት፤ ቃላቸውን ብንበላ፤ ኪዳናቸውን ብናፈርስ በቁማችን እንፈርስ ዘንድ እምንወሰንበት እለት ነው።  ሰማዕቱን ማሳብ ብቻ ሳይሆን ዕውን የታገድሎው ዓላማ ገብቶን ከሆን በህይወት ያሉትን ጀግኖቻችን ድም...

ግን እባክህን አትገንግን? 80 ችግር እንደገና ግን?

ምስል
ችግር በራሷ ላይ መጫን የለመደባት አላዛሯ ኢትዮጵያ 80 ችግርን ለዘለቄታ ፈቀደች። „አንተ የዘራኸው ዘር አይበቅልም ትላለህን፤  አንተ የዘራኸው ዘር ስንኳ ይበቅላል።“ መቃብያ ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፭። ከሥርጉተ ©ሥላሴ  07.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ·       ው ዶቼ … የኔዎቹ ማንም የዛሬውን ተደሞዬን አስተውሎት አልሰጠውም። ግን ደህና ናችሁን ውዶቼ? በሰሞናቱ  በሌሎች ጉዳዮች ተወጬ ነው እንጂ እጅግ በጥሞና የተከታተልኩት ዜና ነበር ባፈው ሳምንት … ያው ባነሩ ላይ ተለጥፎ ነው ያነብኩት ...  ውዶቼ ሰምታችኋዋል አይደለም ዛሬ በዚህ „ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ዘመን አዲስ ሌላ ፈተናም መደገኑን። "የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር ተሰመረተ" የሚል ዜና አንብቤያለሁኝ። የኖረው የ43 ዓመቱን ዳገት መውጣት ተስኖን ሌላ አዲስ መከራ ደግሞ እዬበቀለ ነው።  በሌላ ፎርም እና ይዘት። ነገ የአማራ፤ የትግሬ፤ የጉራጌ፤ የወላይታ፤ የኮንሶ፤ የኩናማ፤  ከንባታ፤ የሃድያ፤ የአፈር፤ የሀረሬ ወዘተ 80 የተማሪዎች ማህበር ደግሞ ይመሠረታል። ይህ ለምን ተፈለገ የሚለው ራሱን የቻለ አምክንዮ ነው። የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር ከመፍጠር ይልቅ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር መፍጠር የተሻለ ነበር። ይህም ቢሆን አስፈላጊ አይደለም። የመማር ዕድል የሌላቸውን ወጣቶች አግላይ ነው። ጨቋኝ ነው። በዚህ መሥመርም ነው የኢህአፓ፤ የሻብያ፤ የወያኔ፤ የመኢሶን፤ የደርግ ሁሉም መከራ የመጣው። ያን ዛሬ ላይ እንድገመው ደግሞ ተብሏል። ·       ግ ርም በግራሞት። ስለምን ...

ሃይማኖት ብሄር የለውም!

ምስል
  የጅጅጋው ጥቃቱ ከብሄርሰብ ጋር መያያዝ አይገባውም። „ድሀና ግፈኛ ተገናኙ እግዚአብሄር  የሁለቱንም ዓይን ያበራል።“  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፲፫። ከሥርጉተ ©ሥላሴ 06.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት አመሻችሁ ዋላችሁ አደራችሁ። የጸና ደስታ የጸና ሃዘን ሁለቱም ሲያሰኛቸው በፈረቃ፤ ሲሻቸውም ደግሞ በአንድነት እዬሰላለቁን አመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ይቀረዋል። ባለፈው ዓመትም ይህን ሰሞን እስከ ፆመ ጽጌ መፍቻ ድረስ መሰሉ ፈተና ገጥሞን ነበር። የዛሬው የታቀደው የቅድስት ተዋህዶ እና የእስልማና ሃይማኖትን ምክንያት ፈልጎ አጋጭቶ አገራዊ ብጥብጥ ለማስነሳት ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ እርቀ ሰላሙ የውስጥ እሳት የሆነበት የመቀሌው መንግሥት አቅዶ የከወነው ነው። ይህን ፍርድ ሰጪው መዳህኒዓለም ነው። ለዚህም ነው እኔ ግንቦት 7 ሆነ ኢሳት አገር ቤት መሄድ አይኖርባቸውም የምለውም ። የአብይን መንፈስ መቀበል መልካም ነገር ነው፤ ይሄው ብራናው አርፏል። ህውከት የለውም። እናግዘው ይህን መንፈስ ከተባለ ሳሄዱ ውጭ እያሉ ብዙ ተግባራትን ሊከውኑ ይችላሉ ግንቦቶች እስከ ሚዲያዎቻቸው ድረስ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቂመኛ ነው። የፈለገ ይቅርታ ቢባል፤ ፍቅር ቢባል ልባችሁን አውልቃችሁ ብትሰጡ አይቀበለውም። ሌላውም እንዲሁ ነው። ይህን በሚኒ መንትዮሽ ጉባኤ አይተነዋል። ስለምን ልባችን ድፍን አድርጎ እንደ ፈጠረን ይጨንቀኛል። ሌላው ይህ እልቂት የአማራ ጥቃት ብቻ አይደለም። ሃይማኖት ዘር እና ጎሳ የለውም። ቅደስት ተዋህዶ የመላው ኢትዮጵውያን ቤት ናት። የሁሉም ዓውደ ምህርት ናት እንጂ አንድን ዞግ ወይንም ብሄር ብቻ እምታሰባስብ አይደለችም። ጥቃቱ የሁሉ...

አማራነት ሌላውን አጥቂነት ሳይሆን ራሰን ጠበቂነት ነው።

ምስል
ምን ስለሆነ?ምንስ ስለተገኘ? „ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፲ ከሥርጉተ © ሥላሴ  06.08.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።    ይህን የህዝብ ሙሉ የፍላጎት ድምጽ ጥሰህ እንዴት "የወጣት ብቻ" ትለላህ? ·        ጠ ብታ። የግራሞት ሰሞናት ነው። አንድ የቪዲዮ ክሊፕ አዬሁኝ „አብይ አማራን ከሁለት ከፈለው“ ይላል። ግን ቅናዊ ትህትናዊ ነው። አጀብ ነው። ምን አድርገው ነው ዶር አብይ አህመድ  አማራን ከሁለት የሚከፍሉት? የሰበኩት ኢትዮጵያዊነትን ነው። አማራ ደግሞ ሙሉ 27 ዓመት የተጨፈጨፈበት ዘሩ እንዲፈልስ የተደረገበት ዋናው አምክንዮ ይሄው ነው። ·        በመከ ራ የተወለደ የማንነት ተጋድሎ። አማራ አማራ ነኝ ያለው እኮ በሀምሌ አምስቱ አብዮ ነው። ከዛ በፊት እኮ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት ነው የቀራንዮንም፤ የጎለጎታም የመከራ ጽዋ ብቻው ዕጣ ነፍሱን  ሲጨልጥ 27 ዓመት ሙሉ የኖረው። አማራ ነኝ ሲል ደግሞ አሸባሪ ነህ ተባለ።  ስለዚህ ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት ስትባል ትናንት ያሳበዳቸው አሁን ሚኒ ጉባኤ ላይ ያሳኙን ባለተውኔቶ ሞደሬተሮች ይጨነቁበት፤ ለእኛማ የኖርንበት ማተባችን እኮ ነው። እስኪ መቼ ነው አማራ ከዛ  አፍሪካ የነፃነት ዓርማ ከሆነው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማው ውጪ ለሰከንድ መንፈሱ ወጥቶ የሚያውቀው?  አሁን አንዳንድ የውጭ አገር ሚዲያዎች አዲስ ዝግጅቶች አያለሁኝ በዛ ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማ ፊደሎችም ዝግጅቱም ተሽሞንሙኖ የሄዱበት ዥንጉርጉርነት ...