ልጥፎች

ይድረስ ልብ ላላቸው የጎረቤት አገሮች መንግሥታት እና ዜጎቻቸውም።

ምስል
ብል።  „በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች፤ እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለኃጢያተኞች ተፈጠረች።“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·         ይድረስ ልብ ላላቸው የጎረቤት አገሮች መንግሥታት እና ዜጎቻቸውም። ትናንት ቀን እኩል ላይ ማህል ላይ የለጠፍኩትን የአቶ ጃዋር መሃመድን ቃለ ምልልስ አዳምጥኩት። የቅድሚያ ማስጠንቀቂያም ይመስላል። ለጊዜው አንዱን ብቻ አነሳለሁ። ቀጥዬ በዚህው ቃለ ምልልስ ውስጥ ሁለተኛው እና ሦስተኛውን አትኩሮቴ የሳበውን ነጥብ መርጬ በሌላ ጹሑፍ እምጣበታለሁኝ።  ምንድን ነው የአገሬ ሰው የሚለው „ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው“ እንደሚሉት መሆኑ ነው … ብቻ ልብ ያላቸው መልዕክቱን በሚችሉት ሁሉ ቢያደርሱት መልካም ነው። ይህ ጉዳይ „ሳይቃጠል በቅጠል ነው።“ እስኪ መጠንቀቅ ይልመድብን። እስኪ አስቀድሞ ይሆናል፤ ይመታል ብለን እንሰብ። ጆሮ ያለው ልብም ይኑረን። የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ ተግባሩን የጀመረበት አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ነበር። በጫና እና በጠለፋ አንቆ ለማስቀመጥ ብዙ ተብሎበታል፤ ብዙም በወል ተሞክሯል። ዛሬ ላይ እንዲያውም በቅጡ ሳያስናዱ እዬተባሉ ደግሞ ይወቃሳሉ። ምኑን? ይመጣበታል። ቅኑ ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ሥራ ሲጀምሩ እንደ አዲስ ጠ/ ሚር አልነበረም። ዘመኑን ሙሉ ሲሳራበት እንደኖረ እንደ ጓዳቸው፤  በአዲሱ ማንነት ከህይወቱ ጋር አብሮ እንደ ኖረ የተወሃደ - በቅጡ የተደራጀ፤ ህሊናውን ለሁለገብ ፈታኝ አምክንዮዎች እና ክርክሮች ያሰናዳ፤ ጥልቅ በሆነ ሁኔታ ሉላዊ፤ አህጉራዊ እና ብሄራዊ ግንዛቤው በዳበረ እና በለማ መሰናዶ ነበር የጀመረው። ለ...

በተስተካከለ ሙላት ለመኖር ሆኖ መገኘት።

ምስል
አሽካካች „እግዚአብሄር እሱን መርጦታል እና ለባለመዳህኒት ሥራውን ሥራለት እሱን ትሸዋለህን እና ካንተ አታርቀው“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጨረሯ ብቻ ደረሰኝ። ምን ደረሰኝ ብቻ አዳረሰኝ። እሷ ግን አትታይም። ስብሰባ ትሆንን? ወይንስ ሰማያዊ አልጋዋ ላይ ተኝታ … ወይንስ ጫጉላ ጊዜ ላይ ትሆን ወይንስ ከባዘታማዋ ፍራሽ ተኮፍሳ? ክብር ሲወድላት ደግሞም ሲያምርባት የለችም። ብቻ የለችም። ግን አለች ትንፋሿ ሀገር ያዳርሳል። መንፈሷ ይሆን የሌለው? ይሆናል። ምን ይሆናል ነው እንጂ። ግን ለምን? … እእ … ለምን …. እለምን …? ጠብኩ፤ አልመጣችም። ለእኔ ለእራሱ የላከችው ለብ ያለ ጉድ ነው። ልም ነገር። ስትገርም። ለእናንተስ ይሄው የ እኔ ዕጣ ፈንታ ደረሳችሁ ይሆን? … አላውቅም። ቀና ብዬ ፈራ ተባ እያልኩ ተመለከትኳት … „ነገ ሌላ ቀን ነው“    አሃ! ብላ ጽፋለች። ዝቅ ብዬ ስመለከትላችሁ ደግሞ „ይኽም ያልፋል“   ብላ ጻፈች … ጎሽ! አልኩና ተረጋጋሁ። ግን ለምን? አላውቅም።  ለመሆኑ ያነበብኩትን እርግጠኛ ነውን? „ ነገ ሌላ ቀን ነው „ ብላ ስለመጻፏ እንደ ገና አዎን እንደ ገና አሻቅቤና ሻቅሌ*  ሳዬው ተለውጦ … „የማይቻለውንም መከራ ቢሆን በትእግስት ቻይው“ ብላ ጽፋልኛለች። ወይ ጉዴ ግን … ለምን? አላውቅም። ዝቅ ብዬ እንደ ገና … አዎና! እንደ ገና ተመለከትኩኝ። „ከመከራው በስተጀርባ ክብር አለ“ በማለት ደግማ ጽፋለች።  ምን ማለት ነው ይሄ? ደግሞ እሷን ብሎ ትንቢተኛ፤ እሷን ብሎ ስለነገ ራዕይ ተንታኝ በታኝ … ከደንቀራው ጋር ስትደልቅ ከርማ ብዬ ልኮራፋት ስል በአንድ ...

ተፈጥሮን ያዘመነው የማሰብ ፍልስፍና ልቀት ነው።

ምስል
መሆንን በማሰብ፤ መሆንን በመቻል፤ መሆንን በመሆን። „ይህ ህዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤“  የማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 28.09.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።   v   መ ቅድም። መሆን በመሆን ቢጣፋ? መሆን በመሆን ቢባዛ፤ መሆን በመሆን ቢቀመር በመሆን ውስጥ መኖርን ያጠይቃል። መሆንን ማሰብ፤ መሆን በመቻል ማቻቻል፤ መሆንን በመሆን ማትጋት ሁሎችም የተፈጥሮ መብቶች ናቸው። ልዑል እግዚአብሄር የሰጠን። እርግጥ ነው መሆንን ማሰብ ገደብ የለውም።  መሆንን መቻል ግን የሚከብዱ ነገሮች ይኖራሉ። መሆንን በመሆን ዕውን ለማድረግም እንዲሁ።አንደኛው ለምሳሌ ሊሆኑ የፈለጉትን አለማግኘት ነው።   v   መ ሆንን ማሰብ። መሆንን ማሰብ የሚነሳው ከራስ ብቻ አይደለም ከቤተብም ከአካባቢም ሊሆን ይችላል። ብቻ መሆን ማሰብ እስከ ዕድሜ ልክ አብሮ አድጎ እስከ ገሃዱ ዓለም ሥጋዊ ስንብት ድረስ አኗኗሪ ነው። በዚህ ውስጥ ማሰብ ራሱን የቻለ መክሊትም አለው። ከአካባቢ ወጣ ያለ ምናባዊ፤ ፍልስፍናዊ እሳቤም ይኖራል። ማሰብ ድንበር የለውም እንደ ተፈጥሮ ጸጋ ለሚያዩ አካላት። መኖር የተፈጠረው በማሰብ ሃሳብ ውስጥ ነው። ማናቸውም የመኖር ሁለመና መሰረቱ በማሰብ ልቅና የተገኘ ነው። ከማስብ ልቅና፤ ከማሰብ ብልጽግና ውጪ የሚፈጠሩ የፈጣሪ ፍጡራን እና ተፈጥሮ ብቻ ነው። ተፈጥሮን አሰልጥኖ፤ ተፈጥሮን ዘመናይ ያደረገው የማሰብ ፍልስፍና ልቀት ነው።   v መ ሆንን በመቻል ማቻቻል። ሊሆኑ የፈለጉትን ቢያገኙትም በመሆን ውስጥ ካልተከተበ ብላሽ ነው መሆንን ማሰቡም ሆነ መሆንን በመቻ...

እንባ ያቆረዘዘው የ2011መስቀል።

ምስል
ሹግ እና ብርሃኑ አለቀሱ። እጃችሁን ለእግዚአብሄር ስጡ፤ ለዘላላሙ ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፤ ጽኑ ቁጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሄርን አምልኩ። (መጸሐፈ ዜና መዋዕል ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፰) ከሥርጉተ©ሥላሴ 28.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የዕባማውም ሹግ ግማድ ጉሽ! ከቀደሙት ዓመታት መስቀል ሳይመስለኝ ያለፈው የዘንድሮው የ2011 ነው። ፈጽሞ ጠረኑ ድብርት እና ደመመን ተጭኖኝ ነው ያለፈው። ቤተሰቦቻቸውን ለማዬት በተጓዙ ኢትዮጵውያን የደረሰው የመኪና አደጋ ማግስት ነው ባዕሉ የተከበረው። እንደ ብሂሉ ባሳብው  „እንዳያም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ ዓይነት ሆኖ ውጥረት ተፈቅዶለት ተከብሯል። ሁሉም አምጦ እንዳከበረው አስባለሁኝ። የመርዶ ያህል መጪውን ጊዜ እያሰበ …  በ ዕንባም ሰምጦ። እኔ የ2011 የደመራ ባዕል ያለቀሰው የመስቀል ባዕል ብለው ይሻላል። ከሁሉም ዘመን እጅግ ጫና እና ውጥረት በብሄራዊ ደረጃ በበዛበት ሁኔታ የታሰበበት በዓል ቢኖር ዘንድሮ ነው። እርግጥ  ነው የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ በተካሄደበት ወቅት በዕሉ በጎንደር ተሰተጓጉሏል፤ ጫናውም በብሄራዊ ደረጃ እንደ ነበር ባስታውሰውም፤ ያን ጊዜ የነፃነት ፈላጊው ጉልህ መንፈስ ጎልቶ ሲሆን አሁን ግን ማተቡንም የሚያፈታተን የልታወቀ መንገድ እዬናጣው ነው አዬሩን ነው የታሰበው... ወዮልሽ ቤተሳይዳ!  ለነገሩ የ2011 የሬቻ ባዕልስ የሚለውን ለሚዛን ግብረ መልስ ነገ የሚሰጠን ይሆናል?  ያን ጊዜ በዘመነ አማራ ተጋድሎ ባህርዳር አንድ ብጹዑ አባት እዮር ልኮ ልጆቻቸውን በመንፈሳቸው አቅፈው እና ደግፈው አጽናንተው እና አበረታተው፤ ችግሩን አብረው ተጋረተው ከጎኑም ተ...