ሥነ ግጥም - ለአረጋጊ ባለመክሊት ዬኛው።
„አቤቱ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።“ መዝሙር ፩ ቁጥር፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 11.10.2018 ከጭምቷ ሰዊዘርላንድ *** ያን ቀን „ቀኑ“ ተከስቶ ወፍ ጎሽ! ብሎት ያዬሁ ለታ ስብሰለሰል ስወያይ „ከቀኑ“ ጋር እንዲያ ለ እ ፍታ መተከዜን ዘብ አቁሜ ለ አ ፍታ ብቻ ብቻ ህልም ሲፈታ እንዲያ እና እንዲህ ሲፈታታ፤ የነፍስ ውሽክታ - በመልካም የልብ ስንኝ ፈገግታ፤ የቅኔ ቤት፤ የዋሸራ፤ የመንፈቀ ሌሊት - ልዑቅ ዕድምታ ተረገጥ ሆነ የመገኘት የኔታ! ያለተረዱት ቢፈልጉት፤ ባይፈልጉት ያልፈለጉት ሳይረዱት፤ ባይረዱት የተረዱት በእሺታ አይሆ ንም ን አ ረዱት! ሲሆን ሲሆን ማታማታ የነበረ ለናት እንጂ አልነበረም ለህምታ። ሲያማክረው የሩቅ አገር ወፍ ያወጣው ያለስርቅታ ያ ቀንዲሉ የዘመን ተደሞታ፤ በአርምሞ - በክህሎቱ ተመስጦ ያለውካታ ቀነ የሰጠው የቅንነት ብርቱ እርካታ፤ የአባት አደር የወልዮሽ የሎሬቱ ገበታ! የህልመኛ ባዕት ብጡልነት ትርታ ያልነበረ ለቱሙታ፤ ግን እንጂ በቅብዕው ያልነበረው ቅሬታ ስለ ምህረት ተስፋው ስለዘለቄታ የንጽህና ድንግልና ግርምታ፤ የዘመን ሙሉ ስንዳታ! ሴራን ላይወዳጅ፤ ላይ ዳ በል ከካኳቴ ጋራ ከሆታ ቂምን ላይቋጥር፤ ሊሆንለት ብቻ ብቻ ለይሁንታ፤ የርህርህና አንበል ያ ብላቴና፤ ያ ከርታታ ከልብ እንጂ ማዳመጥን ማህተሙ የተመታ። በሩቅ ምናብ ሆኖ ሰታዘበው፤ ... ጥድፊያ ሲሮጥ ሲያሯሩጥ በትዝበቱ ሲከትብ ሲመሰጥ በእጬጌታ፤ አድብየለሽ ሲባክን ሲጋት የሲቃ ኩልልታ ... የጠዛ እልልታ ያ ባተሌ ልበቅኑ ይታደማል በጸጥታ። ሲያድጥ ሊያላልጥ የሸር ጎርምጥ አይ ተድሮ ሲኮበልል ሊሸ...