ልጥፎች

ለንጉሥ ታከለ ኡማ ሲባል ግለት በአደባባይ።

ምስል
ያቅለሽልሻል። „በታካች ሰው እርሻ   እምሮ በጎደለው ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ  16.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።  ለነገሩ እኔ ብዙም አይደንቀኝም ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው ያዬሁት። የዛሬ ሹመት ስንት ቀናት እንደሚሰነበት ደግሞ ወጀብ ይጠዬቅበት። መፈንቅለ መንፈሱ በጉልህ ዛሬ ማዬት ያስችላል። ጉለበታሙ አርሲኛው እና ጉልበታሙ አደዋኛ ጋብቻው የደራ ይመስላል።  ሌላው ሴቶች እኩል በኩል ቁጥር መሆኑ እናትነት አህትነት እርህርህና ሲሉን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጫካ እንዴት እርህርህና፤ ፋቲክ እንዴት ርህርህና፤ ምላጭ እንዴት እናትንት፤ ጭካኔ እንዴት ደግነት፤ ጋዳይነት እንዴት ጽድቅ ስለመሆኑ ፊት ለፊት በቀዳማይነት  ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄርን ሮል ሞዴል አደርገውልን ነው። ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜልም ቢሆን ሥራ በዝቶባቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ ነው የተባለው። እንደ እኛ በፖለቲካ ድርጅት ለሰራ ሰው እቃ እቃ ጨዋታ ነው። ለጠ/ ሚር ቦታ የሚያሰጉ ሴት እዬሆኑ መጡ፤ አሁን በቅርብ በወሰዱት እርምጃ የለውጡ ኮከብ አንስት መሆናቸው፤ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው አስፈራን፤ የለውጡን ታሪክ እኛው እንጠቀልለዋለን ቢባል በስንት ጣሙ። አሁንም ድርብርብ ያለ ሃላፊነት ነው ያተሰጣቸው በዛ ላይ ሥሙ "የሰላም"እና ምግባሩ የማይገናኝ ነው።  ለእኔ እንደ ዕንባ ጠባቂ፤ እንደ ሴቶች እና ህጻነት፤ እንደ ሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ነው የማዬው። ለውጥ በምለው ወስጥ ያለወን የሴራ ገመድ ምዕራባውያን እንዳያዩት ለመሸበብ ነው። እሳቸው እንዲሙሩት የተፈለገው ተቋማት  የኦሾቲዝ ታሪክ ነው ያላቸው። በሌላ በኩል  እኔ ይህ ዲሞሽን ...

ጠ/ ሚር ዶር አብይ ለልዩ ሃይሉ ትህትና መቀለባቸውን እደግፈዋለሁ።

ምስል
መጋጋል ። „እግዚአብሄር የእውነት ዳኛ ነው፤ ሃይለኛም ታጋሽም ነው። ሁልጊዜ አይቆጣም“ ከሥርጉተ© ሥላሴ  13.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በሰሞናቱ የልዩ ሃይል አመጥ ጉዳይ የሁለገብ ሊቀ ሊቃውነቱ ሻለቃ ዳዊት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ያው ሙያዊ ነው። እሳቸው ሉላዊ ዕውቀትም፤ ልዩ ተመክሮም ያላቸው ሊሂቅ እጬጌም ናቸው። በሌላ በኩል መጀመሪያ ላይ ከምንም ያልቆጠሩት ሁሉ አሁን ውይይቱ ሦስት ቀን ነበር ሲባል ማጋጋሉን ተያይዘውታል። መጀመሪያ ላይ ነው ጠረኑ ትክክል አለመሆኑን በርቀት ማዬት፤ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ለመንግስት መስጠት። ቀደም ብሎ ጉዳዩን ማጥናት፤ መተንተን እና መረጃውን ከተለያዬ አቅጣጫ የመገምገም ምህንድስና ሊደረግበት ነበር የሚጋባው። ቀድሞ ነገር እንደዚህ ያለ ነገር ሲደመጥም ወዲያው ማብራሪያ መስጠትም የተገባ አይደለም። ችኮላ አያስፈልገውም። ተደሞ ያስፈልገዋል። ርጋታ እና ስክነትም ይጠይቃል። አሳድሮ አገላብጦ አይቶ ከስሜት ጋር ሳይስጠጉ፤ በራስ ፍላጎት ሳይቸነክሩ የጭብጡን ማንነት ብቻ በራሱ ማንነት ራሱን አስችሎ መመርመር ነበር የሚገባው። የሆነ ሆኖ እኔ አስተያዬቴን ዛሬ ልሰጥ የፈልግኩበት ምክንያት ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮወርጊስ ዕይታ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል አይደለም የሚሉትን ነው። እሳቸው ዘመን ጠገብ ባለሙያ ስለሆኑ እሳቸውን አሻቅቤ መተቸት አልችልም። ክህሎቱም ተመክሮውም ብልጹግ ነው በሲቢሉም ሆነ በወታደራዊ። መሬት ላይም ሰርተውበታል። ነገር ግን እኔ እንደ ሰው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል ነው ብዬ ነው እማስበው ። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እያስተማሩ ያሉት የሃሳብ አቅም ከባዱን ተራራ ንዶ፤ ደልድሎ፤ ሸካራው...

ግልጽነት ገዳም በመግባቱ ቋቅ ነገሰ።

ምስል
ግልጽነት ገዳም በመግባቱ ቋቅ ነገሠ። "እናንተ የሰው ልጆች እስከ መቼ ድረስ       ልባችሁን ታክብዳላችሁ?" ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?"  መዝሙር ፬ ምዕራፍ ፪  ከሥርጉተ © ሥላሴ  15.10.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እኔ የሚገርመኝ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ የያዙት በአደባባይ ተረሽነው 1200 ነፍሶች ጦላይ ላይ ባለቤት፤ ጠያቂ ሁነኛ ድርጅት ሳይኖራቸው ፍዳቸውን እያዩ በሌላ በኩል ደግሞ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ቀን ሰሞን ምክክር ውይይት ዲስኩር ይደመጣል። ይህን አጣጥሙ መጀመሪያ። እኔ አይደለም የምላችሁ ፋክት ነው የሚያፋጥጠው የጠ/ ሚር ጽ/ቤትን። እኔ እኮ የማይጠቅመው ነገር እንደሚጠቅም ሁሉ እንዲቀጥል የሚፈቀደልት ምክንያት ነው የማይገባኝ። ትናንት የኤርትራው ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ ጎራ እንዳሉ አዳመጥን። ያዳመጥነውን አላምጠን መወጥ ይገባ ስለነበር እኔ አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉ ነው ብዬ ነው እማስበው ብዬ የጻፍኩትም ለዚህ ነው። አቶ ፍጹም አረጋ ደግሞ ይህን አስተባብለዋል በዓለም አቀፍ ሚዲያ ወጥተው። ሆደ ሰፊነት ይሆን 5 ወጣቶችን በአደባባይ አስረሽኖ 1200 ባለቤት አልባዎችን ጦላይ ፍዳ እያስከፈለ፤ የጫት፤ የሺሻ፤ የቁማር፤ የዝርፊያ ፓርቲ ተፈጥሮ የተለጠፈላቸው፤ ጎንደር እና ወሎ ተነጥለው ከዛ የመጡ ወንጀሎኞች ማለትስ ምን ማለት ነው? አይገባንም ይህ? ልብም ህሊናም አለን። ግልጽነት አዲስ ለውጥ አራማጆች መርህ ይሆናል ተብሎ ታውጆ እምናዬው እምንስማው ግን ድብቅነት እንደ ነገሠ ነው። ከስሜን አሜሪካ ከጠ/ ሚር ጉዞ መልስ ጀምሮ ያሉ ነገሮች በህልማችን ለምናምን ሰዎ...

አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን?

ምስል
አቶ ዳውድ ኢብሳ  የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን? „አንተን በፍራሃት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“ መዝሙር ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 14.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አቶ ካሳሁን ጎፌ መግለጫን የገባኝን ያህል ስጥፈው ቆፍጠን ያለ ነው ድፍረቱ ከኖረ ብዬ ነበር። አቃለው አሳንሰው ሲዩትም ደግሞ አይደለም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምስራቅም አስጊ ነው ብዬ ነበር። የአፍ ወልምታ ለተባለውም ያልኩትን ብያለሁኝ። ሲጀመርም እኔ የአቶ ዳውድ ትምህክት መሰረት እንዳለው፤ በቀላል መታዬት እንደሌለበት ሞገደኛ እና ከባድ ውሳኔ ስለመሆኑ ገልጫለሁኝ። የ5ቱ የ ኦሮሞ ድርጅቶች ውሳኔም ከዚህ ጋር የሚዋደድ ነው። አሁን ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ በስኳር ፖለቲካ ኢትዮጵያ እንደ ገቡ አዳመጥኩኝ። ፍቅሩን ያሰንብትላቸው እንጂ እፍ ብለዋል። የጣሊያኑ መሪ ወደ ዛው አቅንተው እንደ ነበርም አድምጠን ነበር። እና ተመለሱ ይሆን ወይንስ ምጥዋ ላይ ተበለስ ጋር? ከዙፋን አስወርዶ በጥድፊያ ያሰመጣው የኤርትራን መንግሥት ምን ቢኖር ነው ብለን ማሰብ ግድ አለን። ደረታቸው ነፍተው ሲናገሩ የሰነበቱት አቶ ዳውድ ኢብሳ በሦስተኛ አገር ሽምግልና ከልሆና በጅ አልልም ያሉ ይመስላል። ሌላ ከሚመጣም ወዳጃቸው አገር ብትሆንላቸው ይሻላቸዋል። ነገም በ አገርነት እንቀጥላልን ባይም ናቸው። ወጣት መሪም ታች ካለ በቂ ነው ብለዋል። ምርጫው የሳቸው ነው። ማን ደፍሮ ይናገራል ጭጭ ረጭ ሆኗል። ከእትጌ ኤርትራ ቤት ዘው ከተባለ መውጫ የለም፤ ወይ መዋጥ ወይ አብሮ መስመጥ ነው … ግን ኢትዮጵያን ማን ነው እዬመራት ያለው? በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ኤርትራ ታጣዋለች ተብሎ የታሰበው ረጅም እጅ ይሁነኝ ተብሏል።...