ልጥፎች

ዘመን ያልፈታው እንቆቅልሽ፤ እኮ ምን ሳውቅልህ።

ምስል
  ዶር አንባቸው   መኮነን አደራ ተብልቶ፤ ቃልኪዳን ታጥፎ ተንሳፋፊ በግለት፤ አቶ አሚር አማን የጤና ጥበቃ ሚ/ር ቀጣይ በክብር።                                                               ዘመን ያልፈታው እንቆቅልሽ፤                  እኮ ምን ሳውቅልህ?

የምናከብርህ ዶር አንባቸው መኮነን ከጎንህ ነን!

ምስል
እንኳን ደስ አለህ አዴፓ¡ „ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፵፱ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 18.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                                                                      ·       እ ፍታ። የኔዎቹ እንዴት ናችሁ፤ ብዙ ሰው ሹመቱ የራሳቸው ነው እኛን ምን አገባን የሚሉ አሉ አሁን እኮ መንግሥት አለ ብለን ስለምናምን እንጂ እኔ አዲትም ቀን በሹመቶቻቸው ዙሪያ ጽፌም አላውቅም፤ ፓርላማም ጉባኤውን በትጋት እማዳምጠው ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ነው።  ሌአለው ቀርቶ እዚህ ሲዊዘርላንድ ማን አንባሳደር እንደሆነ፤ አንባሲው ቢሮው አድራሻው የት እንደሚገኝ ሁሉ አላውቀውም፤ ምን ይዶለኛል፤ ምንስ ያገበኛል፤ እኔ ዜጋ አይደለሁምና። አሁን አስተያዬት የምንሰጠው የ እኔ ከማለት ነው እንጂ ይህን ራሱን አይተን አይተን እናቆመዋለን። እኔ በተለይ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ስላዬሁት ብቻ ሳይሆን ከስሜን አሜሪካ መልስ ጠ/ ሚሩን የማስወገድ አደጋም ተደርጓል ብዬ አስባለሁኝ፤ ምክንያቱም አብዩን አሜኑን እጅግ አቅርቤ አዬ ስለነበር ፈጣሪ መልዕክት ልኮልኛል ብዬ አምናለሁኝ። ያ ሳይሳካ ሲቀርም እገዳ ማዕቀብ፤ ቅደመ ሁኔታ ተቀምጧል ብዬ ስለማስብ አሁን እዬሆነ ያለው ነገር ብዙም አልደነገጥበትም። እኛ ነው እየሠራን ያለነው እያለን ...

አቶ ታገሰ ጫፎ አፈ ጉባኤ ሆኑ።

ምስል
አቶ ታገሰ ጫፎ አፈ ጉባኤ ሆኑ። „ሳሙኤልም ወደ አምልኮቱ መለሳቸው፤ የልቦናቸውም ዓይኖች በሩላቸው።“ መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፴፫ ቊጥር ፶፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ  18.102018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አቶ ታገሰ ጫፎ ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜልን ተክተው አሁን በሙሉ ድምጽ ካለ ሌላ እጬ ተዋዳዳሪ የኢትዮጵያ ፓርላማ እንደመረጣቸው አየሁኝ። በሰሞናቱ ስብሰባ ከፓርላማ ተሳታፊዎቹ በሚቀርበው ጥያቄ ላይም ማብራሪያ ሲሰጡ አዳምጬ ነበር።  የሆነ ሆኖ ያው ሌላ እጩ የለም፤ ተቃውሞ የለም። ድምጸ ተዕቅቦ የለም። እንግዲህ አቶ ታዳሰ ጫፎ በዘመነ ወያኔ መራሹ ግንባር በኢህአዴግ ከሥር ጀምሮ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች አብሮ የኖሩ፤ በድርጅታዊ ህይወት የበቀሉ፤ በቀለም ትምህርትም የገፉ፤ ስለሆናቸው የህይወት ታሪካቸው ሲገለጥ ሰምቻለሁኝ ቀደም ባሉ ቃለ ምልልሶችም መጠነኛ መረጃ አለኝ። በሙሉ ዕድሜ ላይ ስለሚገኙ የተገባ ነው ባይ ነኝ። ታሪካቸውን ጠለቅ ብዬ አላውቀውም። የገረመኝ የፓርላማው ጉዳይ ነው። የቀረበለትን ምግብ ሳያማርጥ መዋጥ ብቻ ነው የማህያው ውል። የተሻለው መስሎኝ ነበር ግን ያው ዴሞክራሲያዊ ማዕክላዊነት የሚባለው ፈሊጥ አሁን እዬሠራ ስለመሆኑ በዬስብሰባዎቹ እያስተዋልኩኝ ነው። 100/100 ህም? መቼም በ2010 የተጀመረው የስብሰባ ዘመን ለ2011 አጋብቶበታል። መደበኛ ስብሰባዎችን ማለቴ ግን አይደለም። የሆነ ሆኖ ምን ተሰማሽ በአቶ ታገሰ ጫፎ ብባል ጥሩ ስሜት ተሰምቶኛል።   እኔ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የአቶ ጃዋር አህመድ፤ ብቻ ሳይሆን የኦህዴድም  ቀዳሚ ምርጫ ስለሆነ ያ ሪኮምንዴሽን እና ለሳቸው የሚሰጠው ነጥሎ ከአማራ ክልል የማቅረብ፤ የመንከባከብ እና...

እኮሳ!

ምስል
እኮሳ ! ወደ ዬት ? „ከሱም የተነሳ ባንደበቴ ነገር ተነገረ፤ ምድርም ጠፋች ብዬም እጮኽ ነበር።“   መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ © ሥላሴ 17.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የራስ ተሰማ ናደው ቅኝተኛ ቀኝ ጌታዎቻችን። ·        እኮሳ!  ወደ ዬት ጥሩ ጥያቄ ነው። አሁን በምናዬቸው ምስቅልቅሎች አንዳንድ ጊዜ ድንጋጤ እንዳንድ ጊዜ ብስጨት፤ አንዳንድ ጊዜ ሀዘን ይሰማናል። ስለምን ቢባል አዲስ ሥርዓት ለመፍጠር ያለን ተስፋ እና ጭብጡ የሚነግረን ድብልቅልቅ፤ ውልቅልለቅ ያለ ድንገቴ መረጃ መላ ከማጣቱ የተነሳ ነው። ብዙ ነገሮች ዝንቅ ናቸው። የእነኝህ ቀውሶች መነሻ ያው የራስ ተሰማ ናደው የሴራ ምህዋር ሲሆን ነጠል አድርገን ለማዬት ግን እኔን በሚገባኝ ልክ ትንሽ ልፈትሽው። ለነገሩ እኔ ከሰሜን አሜሪካ ጉዞ መልስ የሆነው በአባ ዝምታ የሐምሌ ዕድምታ ብዙ ኮልሚያለሁኝ። አማራን በተመለከት ምንግዜም ያው ነው። ብዙም አልጠበቀነም ባልጠበቀነው ልክ የሆነውን ከዕለቱ ጀመርነን ታዝበናል። አንቦ ይናገር! ግን ዛሬም ትንሽ በተያያዘ መልኩ ልበል፤ ቀውሰኞች በጅረታቸው እስኪ ይፈተሽ … ·        ቀድሞውንም የወያኔን ዓላማ ሲያራምዱ የነበሩ ግን ተጋሩ ያልሆኑ በፍጹም ሁኔታ የአብይን መንፈስ የማይፈቅዱ አሉ። እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አይነት እነኝህ ከአኩራፊው ማህበር መዶል እንችላለን።   ·        በፍጹም ሁኔታ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጪ መሽቶ የማይነጋ የሚመ...

ለንጉሥ ታከለ ኡማ ሲባል ግለት በአደባባይ።

ምስል
ያቅለሽልሻል። „በታካች ሰው እርሻ   እምሮ በጎደለው ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ  16.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።  ለነገሩ እኔ ብዙም አይደንቀኝም ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው ያዬሁት። የዛሬ ሹመት ስንት ቀናት እንደሚሰነበት ደግሞ ወጀብ ይጠዬቅበት። መፈንቅለ መንፈሱ በጉልህ ዛሬ ማዬት ያስችላል። ጉለበታሙ አርሲኛው እና ጉልበታሙ አደዋኛ ጋብቻው የደራ ይመስላል።  ሌላው ሴቶች እኩል በኩል ቁጥር መሆኑ እናትነት አህትነት እርህርህና ሲሉን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጫካ እንዴት እርህርህና፤ ፋቲክ እንዴት ርህርህና፤ ምላጭ እንዴት እናትንት፤ ጭካኔ እንዴት ደግነት፤ ጋዳይነት እንዴት ጽድቅ ስለመሆኑ ፊት ለፊት በቀዳማይነት  ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄርን ሮል ሞዴል አደርገውልን ነው። ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜልም ቢሆን ሥራ በዝቶባቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ ነው የተባለው። እንደ እኛ በፖለቲካ ድርጅት ለሰራ ሰው እቃ እቃ ጨዋታ ነው። ለጠ/ ሚር ቦታ የሚያሰጉ ሴት እዬሆኑ መጡ፤ አሁን በቅርብ በወሰዱት እርምጃ የለውጡ ኮከብ አንስት መሆናቸው፤ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው አስፈራን፤ የለውጡን ታሪክ እኛው እንጠቀልለዋለን ቢባል በስንት ጣሙ። አሁንም ድርብርብ ያለ ሃላፊነት ነው ያተሰጣቸው በዛ ላይ ሥሙ "የሰላም"እና ምግባሩ የማይገናኝ ነው።  ለእኔ እንደ ዕንባ ጠባቂ፤ እንደ ሴቶች እና ህጻነት፤ እንደ ሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ነው የማዬው። ለውጥ በምለው ወስጥ ያለወን የሴራ ገመድ ምዕራባውያን እንዳያዩት ለመሸበብ ነው። እሳቸው እንዲሙሩት የተፈለገው ተቋማት  የኦሾቲዝ ታሪክ ነው ያላቸው። በሌላ በኩል  እኔ ይህ ዲሞሽን ...