ኦነጋውያን ማቆላመጡን ማብቃት ይገባል።
ግርዝዝ። „ይህ ትዕቢት ምን ጠቀመን፤ ከትዕቢት ጋር ያለ የኦሪትስ ባለጠግነት ምን አመጣልን።“ መጽሐፈ ጥበብ ፭ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በጠ/ሚር አብይ አህመድ የ100 ቀናት ክንውኖች ውስጥ ተካቶ ከነበረው የጉብኝት ቀጠና ወስጥ አንዱ ደንቢ ዶሎ ነበር ። ደንቢ ዶሎ ላይ የነበረው ህዝባዊ ስብሰባ የኩርፊያ፤ የቁጣ የውጡል ነበር ። ለምን መጣችሁብን ዓይነት ነበር። የሚገርመው እና የሚደንቅው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ ኢህአዴግ የሚያስጨፈረውም ከዛ ሰፈር ትውር አላለም ነበር። በቦታው የተገኙት ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ነበሩ። ታዳሚዎች ግን ውስጣቸው ቅጥል እያለ ነበር ንግግሩን የተከታተሉት። ያቀረቡት ጥያቄ ሁሉ ወልደ ግራ ነበር። ፊታቸውን እንደ ኮሶ ኮስኩሰው ነበር አንግዶችን የተቀበሏቸው ። ፊታቸውን እንደኮሰኮሱም ነበር የሸኟቸው። እና እኔ እህታችሁ ከልብ ስለሆነ ሁሉንም ነገር የእኔ ብዬ የምከታተለው ደንቢሻ የምትፈልገው የደንቢን ንጉሥ ብቻ ነው። እዛ ሰፈር ዶር መርራም አቶ ጃዋርም ቦታ የላቸውም ብዬ በተከታታይ ስቸከችክ ባጀሁኝ። ይህም ብቻ ሳይሆን ግንባር ስለሚባለው ፍልስፍናም የጠብታ ያህል የሚያውቁት ስለሌለ እባካችሁ እዛ አካባቢ ትንሽ የሚላስ የሚቀመስ የህሊና ተግባር ፈጽሙ ብዬ ኦህዴዶችን ተማጸንኩኝ። እርግጥ ነው የለማ ቡድን ሥራ በዝቶበታል። በዛ ላይ ልብ ለልብ የመሆንም አዳጋ አለበት። በተጨማሪም ጥድፊያ ላይም ነው የልቡን ለማድርስ ባገኘው የሥልጣን የበላይነት አጋጣሚ ለማስፈጸም። በዚህ 6 ወር ውሰጥ የሦስት አራት አመት ክንውኖችን ከውኗል። በሌላ በኩል ለውጡ ገና ሳይጠናም ነበር ዶር መርራ ...