ልጥፎች

ጎንደር አደብ መግዛት አለበት። ሰላሙንም መጠበቅ ግዴታው ነው።

ምስል
ጎንደር ልብ ይግዛ!አደብም ይኑረው! „ሃሌ ሉያ።  እግዚአብሄርን በመቅደሱ አመስግኑት።“  በሃይሉ ጠፈር አመስግኑት።“ ከሥርጉተ©ሥላሴ  07.11.2017 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                                               https://www.youtube.com/watch?v=q2vm1rTRJgY ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን ስለተበተነው የውሸት ወረቀትና እና ስለሰሞኑ ጉዳይ የተናገሩት 28,02,2011 አሁን ከሆነ ኤቢ አድበርታይዘመንት የሚያዘጋጃቸውን ቅንብሮች እከታተለሁኝ። ተመስገን ብያለሁኝ። ነገረ ጎንደር ነገረ ሥራው መከረኛ ስለሆነ መረጃዎች ጭጭ ሲሉ ይጨንቀኛልና። በመንግሥት ደረጃም ከሚዲያም የተገለለ ነው ጎንደር። ጎንደር የሚፈለገው ኧረ ጎራው ሲፈልግ ብቻ ነው። አሁንም ጫና በጠ/ሚር አብይ አህመድ ላይ እንዲኖር ስለሚፈለግ ሲጯጯኽ አዳምጣለሁኝ።  የአብይ ለማ መንፈስም ለጎንደር ቀልቡን መስጠት ይኖርበታል። አሁን የተመረጡት ከንቲባ ዶር ሙሉቀን አዳነ ልክ የሱማሌው ችግር በተፈታበት መንገድ አይነት ነው። የዚያን ያህል መንፈስ በገፍ ሊሰጠው ይገባል። ብአዴንም ዕድለኛ ነው እንዲህ አይነት ብረት መዝጊያ ሊሂቅ ጎንደር ላይ ማግኘቱ።  የጎንደር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አደና በተለያዩ ወቅቶች ያደረጉትን ቃለ ምልልስ እና ንግግር አዳምጫለሁኝ። ለሁሉም እኩል አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ቅን ሰው መሆናቸውን ከንግግራቸው መረዳት ችያለሁኝ። የ...

"አግዚአብሄርን አመስግኑ።"

ምስል
„አግዚአብሄርን አመስግኑ።“ „እግዚአብሄርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና።  ለአምላካችን ምስጋና ያማራ ነውና።“ መዝሙር ፻፵፮ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ  07.11.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዝሻ "በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን!" ውዶቼ እንዴት ናችሁ ዛሬ ደግሞ ተነስቶብኛል። እቸከችከዋለሁኝ። ·       እ ንዲህም ሆነላችሁ … አዲስ ብርሃናማ የምሥራች ሰንበት ላይ አዳመጥኩኝ። ሰንበትንም በሰላም አሳለፍኩኝ ሻማዬን ቦግ አድርጌ። ምክንያቱም ዕለታዊ ዜና መስማት የምፈልግበት አንድ አውደ ምህረት ስላለ። ያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አህታዊነት ቀጣይነት ጉዳይ ነው። ሃይማኖታዊ ጉዳይ ከነባቢት በላይ ነው። ብዙ ሰው ተቋም የለውም ጥገናዊ ለወጡ ሲል አዳምጣለሁኝ። በመንፈሳዊ ህይወት የሁለቱም ሃይማኖቶች የእስልምና እና የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለማስማማት አንድ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ እና የተከወነው ተግባር ለመንፈሳዊ ህይወት ታላቅ ተቋማዊ ውጤት ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያ እግዚአብሄር / አላህ አላ ብላ ስለምታምን ተከታዮችም እልፍ ስለሆኑ በዚህ ዘርፍ የተከወነው ዕሴታዊ ትውፊታዊ ተግባር የቆሰለውን ታሪካችን ደግሞ የፈጠረ ነው ማለት ይቻላል ። ሁለት ትልልቅ ባላዎች አሉት ጥገናዊ ለውጡ። ጸሎቱም ነው በተከታታይ ከሞት ከተቃጣ መከራ ጠ/ሚር አብይ አህመድን በዬጊዜው እዬታደጋቸው ያለው። ጸሎት /ደዋው ከተወረወረ ሰይፍ ይታደጋል። የቅድስት ኦርቶዶከስ ብጹዕን አባቶች በዬሚገኙበት ውጭ አገር አይናችሁ ጥርሳችሁ ከሚባሉበት እንክብካቤ እና ቁልምጥ ወጥተው ወደ አገር እንገባለን ብለው ሲወስኑ ከአንድ...

መሆኑን ሳይ አልደነቀኝም።

ምስል
መሆኑን ሳይ አልደነቀኝም። „የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፤ ፈርኦንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው  ድንቁርናን ሆነች።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.11.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ዛሬ ጎልጉል ድህረ ገጽ ገብቼ ነበር። አንድ ጹሑፍ አገኘሁ እና ቀልቤን ስለሳበው አነበብኩት። እኔ ጀርመን ላይ አቶ ሺመልስ አብዲሳ ሲገኙ በምን አግባብ ብዬ ሁሉ ጽፌ ነበር። ስለ አቶ ሺመልስ አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት ሃላፊ ስለመሆናቸው በፎቶ የተደገፈ ዘገባ ነበር ጉግል ላይ ያገኘሁት። ካወጡት አስተያዬቴንም ከሥር ጽፌበታለሁኝ። http://www.goolgule.com/shimeles-abdissa/ ሽመልስ አብዲሳ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ / ቤት ኃላፊ ለእኔ እጅግ አዎንታዊ በሆነ ሁኔታ በዛ ወጀብ በበዛበት ጊዜ በጠ/ሚር አብይ እጩነት አቅም ጎን በመሆን ምስክርነት የሰጡ አንድ የኦህዴድ/ አዴፓ ሊሂቅ ቢኖሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ ብቻ ነበሩ። ለቦታውም ምጥን ያለ፤ ክውን ያለ መረጃ በመስጠት እረገድ አቅማቸው አዬር ላይ አንቱ ነበር። አሁን የት እንደ ገቡ አላውቅም። የሆነ ሆኖ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ውስጣቸው ከአቶ አዲሱ አረጋ የተለዬ አቋም እና ምልክታ ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ስጋትም ተስፋም ሁለቱም በእኔ ቦታ የላቸውም ።  ጊዜ የሚሰጠውን መረጃ ከማድመጥ ውጪ ማድመቅም ማጉላትም ማንኳሰስም በበቃኝ ተከውኗል። ብቻ ያው ኦህዴድ/ ኦዴፓ አንዱን አምጥቶ ሌላውን ቢሸኝ፤ አንዱን ሸኝቶ ሌላውን ቢያመጣ ያው የኦነጋውያን መንፈስ ተጽዕኖ ይለቀዋል ለማለት አይደፈርም። ጊዜ እዬጠበቁ የወጡ ዕውነቶች አሁን ከሆነ ሰብሰብ እንድንል ድርብ ...

የዘመን ልቅ መንገድ።

ምስል
የጥገናዊ ለወጡ ውጥንቅጥ የዘመን ልቅ መንገድ ፈተና። „በሰው ተፈጥሮ ያለ ሞትን መጠራጠር ፅኑ ነው።  ከናታቸው ሆድ  ከተወለዱት ጀምሮ በሁሉ እናት  በመቃብር ሆድ እስኪቀበሩ ድረስ በአዳም ልጆች  ላይ የከበደ ሞት አለ።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  07.112018 ጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ይህን የጥገናዊ ለወጥ ዝንባሌ የዛሬ ዓመት ደግፌ መፃፍ ስጀምር ዛሬ በዚህ መልኩ ይገኛል ብሎ ብዙ ሰው አላሰበውም ነበር። መልካሙን ነገር ድጠን በትችት ላይ ስለምንባዝን ነው እንጂ ኢትዮጵያ በዘመኗ እኛ ላለንበት ትውልድ በአዎንታዊነት እንዲዚህ ዓመት የዓለም ሚዲያ አመደኛ ሆኗ አታውቅም ነበር። ሐሴታችንም በውነቱ ልክ አልነበረውም። እኔ በግሌ ብዙ ደስታዎችን አግኝቻለሁኝ።  ቅድስት ኦርተዶክስ ተዋህዱ አህታዊነት ራሱ ገድል ነው። ሁለገብ ውጤቶቹም ህልም የሚመስሉ ነበሩ። ጉልበታም እና ጥበባዊ አቅሙም የሚታመን አልነበረም። ከዬት ተሰጠን እንዲህ ዓይነት ምርቃት ያሰባለ ነበር። ያ ሰበለ ም ነበር።  በሌላ በኩል ያው አሉ ለመባል ብቻ ጥቂት ሰዎች ሥማቸውን ጎላ አድርገው ሲያስጠሩ የነበሩትም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባልነትም አብዛኞቹ እጃችሁ ከምን ሲባል ባ ዶ እጃቸውን ብቻ አገር ቤት እንደ ገቡ ይታወቃል። ፉከራው ቀረርቶው ማሰናከሉ ግን ሞገድ ላይ የነበረው ጉጉስ የብራና ቋቶች ይመሰክራሉ። ዛሬም አገር ገብተው ቀን ለውጡን መደገፍ ማታ በመናድ ላይ ሲታትሩ የተገኘው ብልጭታ በመጉሸት እና ተስፋ በመቀልበስ ጣረሞት ላይ ይገኛል። ብሄራዊ ሃላፊነቱን የተረከበው ኦህዴድ /አዴፓ በያዘው ጥንካሬ በእርጋታ መጓዝ ሲገባው በአማካሪ ስስነት፤ በራሱ ውስ...