ልጥፎች

በተደራጀ ህሊና ታቅዶ እዬተከወነ ያለው መሳጭ ጥሞና።

ምስል
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ህሊና የታደመበት የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተከበረ! „በሕይወትም እንድትኖር እንድትበዛም፣ አምላክህም  እግዚአብሄር ልትወርሳት በምትገባበት ምድር እንዲባርክህ አምላክህን እግዚአብሄርን ትወድድ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዙን ፍርዱን  ትፈጸም ዘንድ ዛሬ እኔ አዝዝሃለሁ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፴ ቁጥር ከ፲፮ እስከ ፲፯ ከሥርጉተቐ@ሥላሴ (Seregute@Selassie) 08.12.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዝ የ27 ዓመቱ የእርግጫ እና የልግጫ ዘመን እነሆ አፈሩን ፈጭቶ ሰኔሉን አዘጋጅቶ ቹቻውን ታጥቆ ዛሬ ወደ ቀብር ተላከ - ዛሬ። የዛሬ ዓመት የብሄረ ብሄረሰቦች ቀን በሰመራ ሲከበር „ስብስቆ“ በሚል ዕርእስ ጽፌ ነበር። ቃል በቃል እያዳመጥኩኝ ነበር የጻፍኩት ፈቃዱ ካላችሁ ይኸውና ኢትዮ ሬጅሰተር ላይ ታገኙታላችሁ። https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/archives/42674 የጠቅላይ   ሚ / ር   ሀይለማርያም   ደሳለኝ   ስብስቆ December 9, 2017 ዛሬ ዕለቱ ደግሞ የወያኔ ልብ ተገጥሞለት የኖረው የአፋር ክልል የሊሂቃኑን ጉባኤ እያከሄደ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። አሮጌን አውልቆ አዲስ መንፈስ ሊያጠልቅ መንገድ ጀምሯል። እንደ እኔ የመጀመሪያውን ሴት ሊሂቁን ወ/ሮ አይሻ መሀመድን ያደርጋል ብዬ አስባለሁኝ። ያለፈው ዓመት ሰመራ ላይ ሲከበር መከራው ጭነት ነበር … ዛሬ ደግሞ ጧፍ ሰማራ ላይ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወፍ አላወጣውም፤ በለስ አልቀናውም በመውደቅ ላይ መውደቅ ተነባበረበት። ለነገሩ የየእጁም ነው የሰጠው። መሸነፍን እያቃተው ገርገጭ እያደረገው ነው። ዛሬ ...

የግፍ መፈተኛ ሊቀ ትጉሃን አቶ መኮነን ገበዬሁን በምልሰት ሳስባቸው።

ምስል
ግፍ። „እግዚአብሄርን ደጅ ጥና መንገዱንም ጠበቅ፤ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ሃጢያተኞችም ሲጠፉ ታያለህ።“ መዝሙረ ዳዊት ፴፮ ቁጥር ፴፬ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie 07.12.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።                                    ሊቀ ትጉሃን አቶ መኮነን ገበዬሁ አልሞቱም                                                  ታሪክ አለላቸው።   መነሻ! https://www.youtube.com/watch?v=dn4hRAZj3Xw አቶ   ገዱ   እንዳርጋቸውን   ያስለቀሰው   የአባቱ   የአቶ   መኮንን   ገበየሁ   በሼክ   አላሙዲን   ተንኮል   እንዴት   እንደሞቱ   ሲገልፅና   ሀብታቸው   እንደተቀማ ።   በምልሰት ልሰባቸው ሊቀ ትጉሃንን አቶ መኮነን ገበየሁን። መቼም ይህን መረጃ ሸር ሳደርጋችሁ አዬ የሥርጉተ ነገር ደግሞ ከዚህ ምን እግር ጣላት ትሉ ይሆናል። ልዑሌ አምላኬ ከብዙ የሕይወት ዘርፎች እሳተፍ ዘንድ ሹልክ እያደረገ ያሰዬኝን ታሪካዊ ሂደት ክፈለ አካል ነው ዛሬ እማጫውታችሁ። ይህን ቅንብር አሁን አዬ...

አንድ ጥበብ የጨለመበት።

ምስል
አንድ ጥብብ  የጨለመበት። Eine Art Dunkelheit . „አንተ ረዳቴ እና መድህኒቴ ነህ አምላኬ ሆይ አትዘገይ።“ መዝሙረ ዳዊት ፴፱ ቁጥር ፩፯ ከሥርጉተ © ሥላሴ(Sergut © Selassie)                                      የሥነ ጹሁፍ እና የመጋዚን ዝግጅት ት/ቤት ውዶቼ ይህን ጹሑፍ የጻፍኩት በ2006 ነበር በፈረንጆች። ያን ጊዜ ሳኡ ከሚባል የስደተኛ መጋዚን ዝግጅት ቡድን ጋር እሳተፍ ነበር። ያን ጊዜ የተጻፈ ነበር። ያን ጊዜ ብዙ እርማት ቢያስፈልገውም በጀርመንኛ ብርቱ ጸሐፊ ነበርኩኝ።ታዳሚም አርቱን ዘይቤውን ይወደው ነበር። ለመጽሄቱ ግጥም የጀመርኩት እኔ ነበርኩኝ። ዛሬ ሳቆመው ቆመ ይባላል። ዛሬ በጣም ደካማ ነኝ። ወደ ቁልቁል ልበለው። ወደ ሦስት ዓመት ሊሆነኝ ነው ስለላውም ስለበዛብኝ ትምህርቱም የማታው ቆመ ጽፌም አላውቅም በጀርመንኛ።   ታሪኩ ዕውነተኛ ነው። ቀን አልፎለት በ2016 ደግሞ የቲያትር ሥልጣና ነበረኝ። እና ለኮርሱ የፍጻሜ ዕለት ለህዝብ በቀረበው ቲያትር ላይ ደግሞ በድጋሚ በአማርኛ እና በጀርመንኛ በድምጽ ቀርቧል። ከሥርጉተ ቁጥር ሁለት ዩቱብ ላይ በድምጽ የተሠራው ለጥፌዋለሁኝ፤ ወደ ፊልም የመቀዬር ሃሳቡ ነበረኝ።  እዚህ ሲዊዝ ውስጥ ስትጀመሩት አየር ላይ ነው ትልሙ እንኩት የሚለው፤ ከሃበሻ ጋር ከሆነ። ኢፍትሃዊነት // እናትን ከሠራሁ በኋዋላ ወደ 10 የተዘጋጁ ፊልም ነበሩኝ ግን እንዴት? አያንቀሳቅሳችሁም። መፈናፈኛ የለም ሁለማናችሁ የታሠረ ነው። ምንም አይቀርባቸውም፤ ከእነሱም ...

ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ።

ምስል
ጥልፍ „ አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን “ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫ ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute© Selassie 06.12.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።                                                 በርን ቤተመጻህፍት ባዘጋጀው የሥነ ጥበብ መሰናዶ።  **           ጠብታ! ዘለላ-                የመንፈስ ወለላ                       መዳፈ-ጥልፍ                            ጠፈፍ!                  አልቦሽ ጠረፍ          ብራና ላይ ሲ...