ልጥፎች

በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ። ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል!

ምስል
በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ። ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል! „ለቤቱ በዓይነ እርግብ የተዘጉ መስኮቶች አደረገ። በቤቱም ግንብ ዙሪያ በመቅደሱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግንብ  ዙሪያ  ደርብ ሠራ፤ በዙሪየውም ጓዳዎች አደረገ፤“ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፮ ከቁጠር፭ እስከ ፮  ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute©Selassie  20.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·         የእልልታ ዕለት መነሻ … https://www.youtube.com/watch?v=lDymVE596Jc ዶ / ር አብይ ወልቃይትን የአማራ የሚያደርገውን አዋጅ አፀደቁ Ethiopia Abiy Ahmed     የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ረቂቅ ዓዋጅ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ / ዛሬ ። በ33 ተቃውሞ በ4 ድምጽ ተዕቅቦ። በጉባኤው ላይ የተገኙ 350 አባላትም ነበሩ። ረቂቅ ዓዋጁ የጸደቀው በ317 ድምጽ ነው። ተመስገን ከእልልታ ጋር ክብር ለእሱ ለአማኑኤል ይሁን። አሜን! ·        ዛሬ ለታላቋ ትግራይ ህልመኞች ሌላ የመርዶ ቀን ነው።  ለእኛ ግን የኢሰብአዊነት አወራሪሱ የማህበረ ደራጎን ዘመን ግብዕት ስለሆነ እንላልን እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል። ሰው ገድሎ፤ አሰቃይቶም፤ ሰላምንም ነስቶም፤ ዘርፎም፤ ወሮም ለማይደከመው ብቻ ሳይሆን ደልቶት መኖርን ለተመኘው የህውሃት ህልም ዛሬ ደግሞ ሌላው የምሾ ቀኑ ነው። ለእኛ ደግሞ የሐሤት ቀናችን እልልታ ነው! እንግዲ...

የግርግር ፖለቲካ ግብዕቱ ተፈጽሟል።

ምስል
የግርግር ፖለቲካ ግብዕቱ ተፈጽሟል። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.12.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·        መቅድም። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ቅኖቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አላዛሯ ኢትዮጵያ ከምትታመስበት መከራ አንዱ በግርግር ፖለቲካ ነበር። በግርግር ፖለቲካ አቅም አላግባብ መባከኑ ብቻ ሳይሆን፤ በገፍ ተጨፍለቀው ወይንም ተደፍጥጠው የሚቀሩ ቅኖችን  ዘመን ሲያስተናግድ ኖሯል በድል አጥቢያ አርበኞች።    ·        እፍታ። በአንድ የግርግር ማዕቀፍ የሚነሱ ሃይሎች የሰከኑ ጉዳዮችን በአሉታ እና በማግለል የመንፈስ ጥሪትን መበከላቸው ብቻ ሳይሆን፤ የቅንነት አንበሎችን ጽልመት በማልበስ ከሜዳ ውጭ በደቦ የሚያደርጉበት ዘመን ጠገብ መከራ እንሆ ዘንድሮ አላዛሯ ኢትዮጵያ መገላገሏን መጋቢት 24 ቀን 2010  አብሯል። በጣም የዘለበው የአላዛሯ ኢትዮጵያ አሳር የነበረው፤ አውሎን የተጠለለ ውሃ ያዘለው ተራራ ማለት ያስችለኛል የግርግር ፖለቲካ ነበር። አንድ ህዝባዊ ንቅናቄ በተነሳ ቁጥር በኮፒ ራይት በመታመስ አዳዲስ ድርጅቶችን በመፍጠር፤ መንፈስ በመበተን ሲተራማስ የነበረው፤ ጭራሽ ስክነት የነሳው ወጀብ ከኢትዮጵያ የተነቀለበት አዲስ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን - ዛሬ። ዛሬ የሰከኑ፤ ደርባባ፤ በሳል የፖለቲካ ሊህቆች የግል ኢጎቸውን ሳይሆን ለ50 ዓመት የዘለቀውን የግራ ፖለቲካ የሥልጣን ጥማት ባይረስ በአመራር ብልጫ፤ በጥበብ በተዋደደ ክህሎት...

ነፍስ ይማር። አሜን!

ምስል
ነፍስ ይማር። አሜን! „ከምድር ስተገኘህ ወደ መጣህበት መሬት እስከትመለስ ድረስ  … እንጀራህን በፊትህ ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ“ ዘፍጥረት ፫ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                                                     ዛሬ ኢትዮጵያ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ነው። ይህ ብሄራዊ የሀዘን ቀን የታወጀበት ምክንያት ደግሞ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በስጋ ከእናት ምድራቸው በመለየታቸው ምክንያት ነው። ሟቹ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህድ ቤተክርስትያን ወደ አንድ መምጣቷ ከስደሰታቸው የኢትዮጵውያ የፖለቲካ ሊሂቃን አንዱ ናቸው። እርቁን በንጹህ ህሊናቸው፤ በንዑድ መንፈስ ተቀብለውታል። ብጹዕን ቅዱስ ሊቀና ጳጳሳትን ጨምሮ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክን ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀሪዮስንም ከቦታው ድርስ ተገኝተው ጠይቀዋል። እንኳን ደህና መጣችሁም በለዋል። የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የአቡነ መርቀሪዮስ ባዕለ ስመትም በብሄራዊ ደረጃ መከበር እንዳለበት ቃለ ምህዳን ሰጥተዋል። በባዕሉ ላይም በአካል ተገኝተዋል።     ብጹዐኑ ሊቀ ቤተክርስትያናት ከስደት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በሚመለከ...

ጥማት።

ምስል
ጥማት!! „እግዚአብሄርም እንዲህ ይላል፤ --- በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፤ በመድሃኒቴም ቀን ረድቼህ አለሁ፤ እጠብቅሃ አለሁም፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፣ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፤ የተጋዙትንም ውጪ በጨለማም የተቀመጡትን ተገለጡ  ትል ዘንድ ቃል ኪዳን አድርጌ ለህዝቡ  ሰጥቼአለሁ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ፵፰ ከቁጥር ፰ እስከ ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                       የለማ የዴሞክራሲ ጀግንነት እንዲህ ነው በአፍሪካ ፊደል ያሰቆጠረው ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አጀንዳችን ባለቀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አብሮ ደመር በመቀመጥ ሳይሆን በ27 ዓመት ውስጥ በጠፉን፤ በሾሎኩን ወደፊትም መጥፋቱም ሆነ መሽሎኩን ለመገደብ ወሳኙን ግንዱ ላይ ማተኮር የተገባ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ግንዱ ደግሞ አዲሱ ትውልድ ነው።  ከ7 እስከ 18 ዓመት ያለው። ያን ነው አንጸን ነፍስ ባለው የዜግነት ትሩፋት አንጸን መገንባት ያለብን። ያ ነው የዛሬው የቤት ሥራችን ሊሆን የሚገባው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ።  እንደ ሥርጉተ ሥላሴ እኛም ማስቲካ የሆን ይመስለኛል።  ያለቀ አሮጌ ቆርቆሮ ለምን አፈሰስክ፤ ስለምን የወዬበው ግድግዳህ ወረዛ፤ ስለምንስ መቆም የተሰነው ምርጊትህ ፍርክርክ ብሎ ህልምህ እንዲህ እና እንዲያ ሆነ እያለን የምናባክነው ጊዜ የተገባ አይመስለኝም። ይልቁኑ በቆሰለው፤ በተጎዳው፤ በደማው የማግስት ድልድይ ላይ እያንዳንዳችን ልናደርግ ስለሚገባው ብናተኮር እና ብንሥራ መልካም ...