ልጥፎች

የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መዳረሻችን ለፖለቲካ ሥልጣን ይሁን። 21.07.2022

ምስል

13 10 2022 Tsegaye Radio

ምስል

Tsegaye Radio 29 10 2022

ምስል

ሽዋ እና ስጋቱ። የሊቃናቱ ዬማስተዋል ፀጋን ይማጠናል።

ምስል
ሽዋ እና ስጋቱ። የሊቃናቱ ዬማስተዋል ፀጋን ይማጠናል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   በኦነጋዊው ኦህዴድ የሚመራው የጫካው ኦነግ ከህወሃት እኩል ቁመና ያለው ሲሆን ዬሚጎድልበት አንድ ነገር ብቻ ነው። እሱን አልናገርም። ለገዳይ ቢላዋ ሞረድ ማምረት ስለሚሆን። ዬሆነ ሆኖ ወለጋ ላይ ታይቶ ዬማይታወቅ ዬመከራ ጦሮ አለ። እጅግ የከፋ። ሽዋ ላይም እያንዣበበ ነው። ኦነግ ሙሉ መሰናዶ አድርጓል ዬሚል ጭምጭታ ነው ያለው። ሽዋን ዳግሚያ ወለጋ ዬማድረግ። ትኩረት ይሰጠው ዘንድ እማሳስበው ለአማራ ሕዝብ ነው። ሽዋ ውስጥ ለሚኖሩ አማራወች። አትኩሮቱ በአማራ አመራር ሥር ባሉት በአጣዬ፣ በሽዋ ሮቢት፣ በካራ ኩሬ ይሁን እንጂ አዋሳኝ አካባቢወችም ሥጋቱ ያካልላቸዋል። ቢያን በመንግሥት ተብዬው ያለው ወከባ ቢቆም፣ የይፋት ፋኖወች ከእስር ቢለቀቁ የተሻለ ይሆናል። ሽዋ ላይ በግል የሰከኑ አቅሞች እንደ አባት አደሩ አያለሁኝ። ችግሩ ተቋማዊ አለመሆኑ ብቻ እንጂ ለአማራ ሕዝብ ህሊና ብቃት ያላቸው ሊቃናት አሉ። ማያያዝ ቢቻል መልካም ነበር። ነገር ግን የስሜን አሜሪካ የፖለቲካ ወይፈን እያለ መከራው ዝልቅ ነው። ስንት የማይደፈር፣ የማይነካ፣ ለአብይዝም ከአቅም በላይ ዬሆኑ የአቅም መቅኖወች እንዴት ባለ ፋክክር ድብ እንዳለ እያስተዋል ነው። ዬሆነ ሆኖ ሽዋ ላይ ያላችሁ የሰከናችሁ፣ የረጋችሁ፣ አደብ የገዛችሁ ህሊናችሁን ውራጅ ለማድረግ ላልወሰናችሁ ልቅናወች በትህትና እማሳስበው የማዳኑ ተግባር ላይ ከህግ በታች ሆኖ ለወገን ደራሽ የሆነ ተቋማዊ ተግባር ቀድሞ ቢከወን ጥሩ ነው። ኦነግ አዲስ አበባን እንደጠቀለለው ሽዋን ካልጠቀለለ ፈጽሞ አይተኛም። ይህ እንዲሆንም ዬቤተ መንግሥቱም ፈቃድ ነው። ግማሽ ሚሊዮን ኦሮሞ ወገኖቻችን ከሱማሌ ክልል ወደ ሽዋ የተዛወሩበት ሚስጢርም ይኽው ...

ለበደል ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ለበደልም የፖለቲካ ተንታኝ አያስፈልገው። በደሉን የሚመክት እራሱን በዲስፕሊን ያረቀ ተቋም እንጂ።

ምስል
ለበደል ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ለበደልም የፖለቲካ ተንታኝ አያስፈልገው። በደሉን የሚመክት እራሱን በዲስፕሊን ያረቀ ተቋም እንጂ።   የአማራን ሕዝብ በነፍስ ወከፍ በሩ ድረስ ሄዶ ቤቱን መቃብር ሲሆን፣ ጓሮው የራሱ አካል ሙት መንፈስ እና ሽታ ሲጎፈንነው፣ ቤተ እምነቶቹ ሲደፋሩ፣ ልጆቹ በፊቱ በማገጡ ሰብዕናወች እዬተሰደቡ ሲደፈሩ ………፣ ማሳው ሲነድ፣ የጤና ተቋሙ አመድ ሲሆን፣ የትምህርት ዓውዱ ሲወድም፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማቱ በግፍ ወደ አመድነት ሲቀዬሩ፣ ተሰልፎ ሲረሸን፣ በአንድ ጉድጓድ በግሪደር በተቆፈረ ጉድጓድ ካለ ሃግ ባይ ሲያሸልብ፣ አትወልድም፣ አትከብድም ተብሎ ጽንስ ወጥቶ መላገጫ ሲሆን፣ ሰግቶ የሸሸውም አስፓልት አቆሸሽክ ተብሎ ሲንገላታ፣ ስብሰባ ተጠርቶ ሲረሸን፣ ሲታረድ፣ ጭካኔው፣ አረማዊነት አገር ምድሩን ሲያካልለው ዬፖለቲካ ሳይንቲስት፣ የማይክ ኤክስፐርት አያስፈልገውም። ችግሩ እራሱ ካሪክለም፣ ችግሩ እራሱ መፀሐፋ ነው። ምፅዓት የፊደል ገበታው የሆነ ህዝብ ቢኖር አማራ ብቻ ነው። ቀለጤው ፖለቲከኛ ዬአማራ ሕዝብ አልተበደለም ይላል። እንደ ሽንብራ ቂጣ እዬተገላበጠ ዬእሱ ወገን ካልተሰቃዬ ለእሱ የድሎት ዕለቱ ነውና። ዬሆኖ ሆኖ ግፍ በቃ ብለው ብቅ ዬሚሉትም በመደዳ ሲረሸኑ፣ ሲታገቱ፣ ሲታሰሩ፣ ሲሰወሩ፣ ሲፈረጁ ያያል፣ ይሰማል፣ ይኖርበታል ጭምቱ፣ ቅኑ ደጉ አማራ። ይህን ሁሉ ግፍ ችሎ ደግሞ የሁሉም ጎደሎ ማሟያ አቅሙ፣ ፖለቲካው፣ ሥነ - ልቦናው፣ ትውፊት ትሩፋቱ ይሆናል። ዬሰጠው፣ የቻለ ህዝብ የማይቻለውን ችሎ፣ የጭካኔ ሪሰርች እዬተሰራበት፣ እንደ ጥንቸል ቤተ ሙከራ ሆኖ ይወገዛል፣ ይረገማል። አንድም ቀን ስለ እሱ ደፍረው ለመመስከር፣ በስቃዩ በመከራው ሁሉ ያልኖሩ፣ ያልነበሩ ደግሞ ማት ያወርዱበታል። ዬሚገርመው እዬተጫኑት መንበርህ ል...

መላጣ ቀን ቀኑ አለመጠናቀቅ። ዛሬም ከትናንት በስትያ ላይ። ዬእኛ ዘመን ላይበቃ። 12,700????

ምስል
መላጣ ቀን ቀኑ አለመጠናቀቅ። ዛሬም ከትናንት በስትያ ላይ። ዬእኛ ዘመን ላይበቃ።   ትሁታዊ አቤቱታ ስለትውልድ ተስፋ። ትምህርት ሚ/ርን ይመለከታል። ውሳኔውን እንደገና እንዲያዬው አመክኖዊ ጭብጦችን አቅርቤያለሁኝ። አስታሪቂ ሃሳብ ነው። የልብ ሽፍትነትን የሚያስቀር። የልዩነት ክረቱን የሚያለዝብ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" በዘመነ ህወሃት ደራ ውስጥ እራሱን በቤንዚን አቃጥሎ ያለፈ መምህር ነበር። አማራ ነው። ሰማዕትም። በዘመነ የቅንጅት ተጋድሎ እነ ህፃን ነብዩ እና እነ ሺብሬ ደስአለኝም ሰማዕትነት ተቀበለዋል። በዘመነ ሰማያዊ እነ ጠበቃ ሳሙኤል አወቀም ሰማዕትነት ተቀበለዋል። ዬዛን ጊዜ መሪ ታጋዮች ዛሬ በሁለት ጎራ ተጠቃለዋል። ህገ መንግሥቱ አንድ ነው። ፀረ አማራ። ፀረ ዜግነት። ፀረ ጥንታዊነት። ፀረ መልካምነት። ፀረ ተዋህዶ። ፀረ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና ሞራል። ዛሬ ሲስረከረክ፣ ሲጎሽ፣ ሲፈላ፣ ሲበርድ፣ ሲንዶቀዶቅ፣ ሲገነፍል፣ የባጀው የ50 ዓመት የዴሞክራሲ ትግል ጥቅልል ብሎ በሁለት ጎራ ከትሟል። ኦነጋዊው ኦህዲድ መራሽ እና ህወሃታዊው መንገድ። እንጥፍጣፊ የለውም። ብታገለባብጡት ቋቱ ከዚህ ነው። አቅም በገፍ ይዋጣል። አቅም በገፍ ይገበራል። ለረጅም ጊዜ የአማራ ልጅ የአቅም ማኔጅመንት ፊደል እንዲቆጥር ጽፌያለሁኝ። ልባሞች አድምጠውታል። ዛሬ ቅንጅት አለን? ዛሬ ሰማያዊ አለን? ዛሬ ኢዴፓ አለን? ዛሬ ግሎባሉ ግንቦት 7 አለን? ዬሉም። ዛሬ ቅንጅት አለን? ዛሬ መኢሶን አለን? ዛሬ "ኢህአፓ" አለን? ሁሎችም ዬሉም። ስለ እነሱ የተሰውት ግን መቃብር ውስጥ አፅመ ርስታቸው በጀምላም በተናጠልም ይገኛል። ዛሬ ያሉት ኦነግ እና ህወሃት ብቻ ናቸው። ህወሃት ቤተ መንግሥት ዬለም። ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ጀምሮ የግሎባሉ ዬትንፋሽ...

"ዬጥሎ ሄያጅ ፖለቲካ።" (መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ።)

ምስል
"ዬጥሎ ሄያጅ ፖለቲካ።"   (መምህርት እና ፀሐፊ መስከረም አበራ።)   "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   ፀሐፊ እና መምህርት መስከረም አበራ ትናንት ከንቃት ሚዲያ ጋር በነበራት ቆይታ የታመቀ የቁጭት መሪ ፖለቲካ ንድፍ አቅርባለች። "ጥሎ ሄያጅ" ስሰማው ደነገጥኩኝ። ክውም አልኩኝ። ዕለታዊው፣ ዓመታዊው፣ ዘመን ተዘመን የዚህ ጉልህ አመክንዮ ሰለባ ሆኗል መስዋዕትነቱ ሁሉ ትውልድም ባክኖ ብቄተ ቢስ ሆኗል። "ጥሎ ሄጅ " ኃይለ ቃሉ ተጠያቂወችን አበክሮ የሚያፋጥጥ አዲስ የአመክንዮ የወርቅ እንክብል ነው።    ዬዛሬ ጽሑፌ ዓላማ ሰሚ ከተገኜ "ላም እረኛ ምን አለ?" ዬሚለውን የአባት አደሩን ይትብኃል አድማጭ ከተገኜ ከዚህ በላይ መሄድ እንደማያስፈልግ አጽህኖት ሰጥቼ በትህትና ለማሳሰብ ነው።   ያለን፣ የነበረን ተቀባይነት ማጣት ከሁሉ የከፋ ኪሳራ ነውና። "አወዳደቄት አሳምረው" ይላሉ ባለ ቅኔወች ጎንደሮች። የመልስ መልስ መልካም ነው። የሃሳብ ሙግት መልካም ነው። ግን በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል። ከትርፋ ኪሳራው እንዳያመዝን ጥሞና ወስዶ ፈቀደ እግዚአብሔር ቢጠዬቅበትም የተገባ ነው።    መሸነፍን አውቆ መቀበልም #ብልጥነት ሳይሆን ብልህ ስትራቴጅስትነት ነው። አልፎ ከሄዱ መዘዙ መጠነ ሰፊ ነውና። በተለይ ሥማቸው፣ ሰብዕናቸው መንበር ላይ ዬሚገኙ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች የብልህነት ስትራቲጂስት ሊሆኑ ይገባል። ያለን፣ የነበረን አጥብቆ የመያዝ ጥበብ።    ቢያንስ የደከሙበት ዘመን በጥሪት አልቦሽ እንዳይደመደም ማሰብ፣ ደግሞ ማሰብ ይጠይቃል። ተኝተው ይሰቡት ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች።   መሪወች በአጭር ተጎርደው ባክነው ዬሚቀርቡትም የሃሳብ ማኔጅመንት ተቋማቸው እንደ አንድ ተማላ ...