ልጥፎች

#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።" #ኢትዮጵያ የማንም "ውሽማም" አይደለችም። ማህከነ። "ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርልኝ።"

ምስል
#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።" #ኢትዮጵያ የማንም "ውሽማም" አይደለችም። ማህከነ። "ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርልኝ።"     • ይኽው ሊንኩ።አገር ከበለጠባችሁ፤ ዬጊዜ አታሞ ካልረታችሁ። https://www.youtube.com/watch?v=jaaelCVVHic&t=451s የአሁን ዋና ዋና መረጃዎች!DereNews Oct. 19 2022 #derenews #zenatube#Ethiopiannews# ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" ስትባል፣ ኢትዮጵያ "ዬማንም ተወሻሚ" ስትባል አይጎረብጥም፣ አይቆረቁርም? ስለማን የምን ንጥረ ነገር ይሆን ዬሚተነፈሰው? ውስጣችን ለእናታችን እንዲህ ሸካራማ፣ ኮረኮንችማ፣ አሜኬላ በቀል። ከእናት አገር ጠረን ዕለታዊ ሰብዕና በልጦብን ይሆን? #በር ። ኢትዮጵያ ከቅኔም፣ ከስዋሰውም አልፋ እና ንራ ኢትዮጵያ #ሰማያዊ #ምስባኽክ ናት።።።።።።።።።።።።። ቫወልም ናት። አናባቢ። ኮንሰነትም ናት ተነባቢ። #ቅምሻ ። ጎንደር ላይ ሲዘንብ የባጀው የዲን በረድ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ መጥቷል። በተለይ "ኢትዮ" ብላችሁ ምንም ተቋም የምትከፍቱ፣ የምትጀምሩ ወገኖቼ በልኳ ለመሆን እሰቡበት። ኢትዮጵያ ረቂቅ መንፈስ ናት። የራሷ ዬሆነ አንጡራ ማንነት ያላት የድንቅነሽ ድንቅ ናት። ዲስፕሊኑን የመጠሪያዋን ዬሚመጥን፣ የሞራል አቅም ይጠይቃል። የአውራ አገር መጠሪያ ነውና። ዬማይፋድስ፣ ዬማይነጥፍ ፏፏቴ ሥም ነው ያላት ኢትዮጵያ አገራችን። ይህን ብዬ ዬፃፍኩት በ2014 ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው ላይ ነበር። በፀጋዬ ራዲዮም በተደጋጋሚ አቅርቤዋለሁኝ። በቅርቡም ጹሐፋን በንባብ ዩቱብ ቻናሌ ለጥ...

ቢሆን። ምኞት ነው ተስፋን ያጨ። #የአይዟችሁ ሠራዊት ያስፈልጋል።

ምስል
ቢሆን። ምኞት ነው ተስፋን ያጨ። #የአይዟችሁ ሠራዊት ያስፈልጋል።     በቀጣይ ሊሆን የሚገባው ዬእርዳታ ሥርጭት ተጓዳኝ አመክንዮ ነው። ላም እረኛ ምን አለን ማድመጥ ላልተሳናችሁ ነው ይህን ዕይታዬን እማጋራው።    ማህበረሰቡም ይህን የአቨው አስተውሎ ሊያደምጠው ይገባል። ሁሉ ነገር በመንግሥት ብቻ አይሆንም። ሲቢል ድርጅቶች ይህን ክፍተት ሊሞሉት ይገባል።    "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   ህወሃት በለቀቀው ቦታ ሽሬ ይመስለኛል የተከዘነ የእርዳታ እህል ለነዋሪው ሲከፋፈል አዬሁኝ። መልካም ነገር ነው። ህይወት ማትረፍ ለሥጋ ሳይሆን የነፍስ ነውና።    ለምን ዬተደራጀ ተግባር አልተከወነም ልል አልችልም። አንድ ኩታራ ልጅ ነበር ሥም ጠሪው። በጦርነት ቀጠና ውስጥ ላለ አስተዳደር፣ ሠራዊት በልጅነት ስላዬሁት የሚክዶናል ቨርገር እንዳልሆነ እረዳለሁኝ።   ይህ ባይሆን ምርጫዬ ነበር። እርስ በርስ ውጊያ ስልጣኔ አይደለም። በእኛ ቢበቃ። ዬሆነ ሆኖ እህሉ ከታደላቸው ነዋሪወች ውስጥ አንዲት እናት አዬሁኝ።    ነጠላቸውን ውልቅ አድርገው እንደ ገመድ እንዲያገለግል፣ ፍግም ብለው ተጎንብሰው 25 ኪሎ ይሆናል በዓይን ስገምተው ያን ተሸከሙ። እና ወደ ቤት ተጓዙ።   በዚህ ውስጥ ብዙ ርብሽብሽ፣ ብጥብጥ ዬሚያደርግ ሃሳብ ነሰተኝ። እስከመቼ? ስለምንስ? ለእነኝህ ደካ እናቶች ያልሆነ ዬ50 ተጋድሎ አልቦሽ ሂደቱን በምልሰት ቃኜሁት? እናቴን ያሰቃዬኋት፣ ያስጨነቅኳት፣ ያከላተምኳት ታወሰኝ። እናም አንጀቴ ተላወሰ።   ስፈጠር እንዲህ ሆኜ ስለሆነ መዳን አልችልም። የበዛ ችግር አለብኝ። በጣም ዬበዛ። እኔን ደፍሮ መርዶ ዬሚነግር አልነበረም። ዛሬ ደግሞ ሰርክ መርዶ ሆነ ያው ማ...

#ከውስጥ ማድመጥ እና ስኬቱ።

ምስል
#ከውስጥ ማድመጥ እና ስኬቱ።     ከሥር ደግሜ ፖስት ያደረኩትን ጹሁፍ ምክንያታዊነት ልገልጥ ነው። ተያያዥ ጉዳዮችም ይነሳሉ። በ21/10/2022 የፃፍኩት ዕውነት እኔ ሲዊዝ ሆኜ በስብሰባው ያገኜሁትን ፊድባክ ነበር። ውስጥን ያላገኜ ድካም ስለታዘብኩኝ። ትናንት 23/10/2022 እዛው ስብሰባ ላይ ዬነበሩ፣ ባለ 7 ነጥብ ዬአቋም መግለጫውን አብረው አዘጋጅተው ያነበቡ የስብሰባው ታዳሚ ደግሞ እንዲህ ይላሉ በEMS። ሙሉውን እናንተው አዳምጡት።   "……… ስህተት ነበር። ሳነበው አንድ ደቂቃ ዬማይሞላ ነበር። 7 ነጥብ ነበረው። ያ እንዳይተላለፍ የተሸማቀቅኩበት፣ እና ዬሆንኩትን፣ ዬተሰቃዬሁትን ስቃይ፣ ቴሌቪዥን ላይ አለመተላለፋን እስካይ ድረስ፣ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው። እዛ ላይ ያሉት ልጆችም እንደዛው። ምክንያቱም አላሸነፍናቸውም። ብዙወቹ ፊታቸውን ሸፍነው ነው ዬሚታዩት። ……" (አቶ ጌታነህ ከበደ ከቄራ አዲስ አበባ) ሊንኩ ይለጠፋል።   https://www.youtube.com/watch?v=Ep9Gl4wlugM EMS Eletawi Sat 22 Oct 2022   ማሸነፍ ልብን ነው። ልብ ከሸፈተ ድልድዩ ሰባራ ይሆናል። በዛው በህወሃት ህገ - መንግሥት፣ በህወሃት አሰባሳቢ ሎጎ እዬተመሩ ድርጅቱን ማውገዝ ዬፋደሰ ነው። እራሱ ማዕከላዊ መንግሥቱ የሚመራው በህወሃት መንፈስ ነውና። ታጥቦ ጭቃ። ይህም ሆኖ በፍግፍግ፣ በማቃለል አያያዝ የታነፀን ልቦና መርታት ጋዳ ነው። ህወሃት አንፆታል። የህወሃት ፖለቲካ ጣዖትነት አይደለም በትግራዋይ በኢትዮጵያም፣ በመላ ዓለምም መንፈሱ አለ።    እሱን ገድሎ በአዲስ መንፈስ የሚመራ የፖለቲካ አቅም፣ አቅመኛም አላዬነም። ከተቃዋሚ በለው፣ ከተዋኃጅ፣ ከመሪውም። በኢህአዴግ በውራጅ አባላት እና...

የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መዳረሻችን ለፖለቲካ ሥልጣን ይሁን። 21.07.2022

ምስል

13 10 2022 Tsegaye Radio

ምስል

Tsegaye Radio 29 10 2022

ምስል

ሽዋ እና ስጋቱ። የሊቃናቱ ዬማስተዋል ፀጋን ይማጠናል።

ምስል
ሽዋ እና ስጋቱ። የሊቃናቱ ዬማስተዋል ፀጋን ይማጠናል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   በኦነጋዊው ኦህዴድ የሚመራው የጫካው ኦነግ ከህወሃት እኩል ቁመና ያለው ሲሆን ዬሚጎድልበት አንድ ነገር ብቻ ነው። እሱን አልናገርም። ለገዳይ ቢላዋ ሞረድ ማምረት ስለሚሆን። ዬሆነ ሆኖ ወለጋ ላይ ታይቶ ዬማይታወቅ ዬመከራ ጦሮ አለ። እጅግ የከፋ። ሽዋ ላይም እያንዣበበ ነው። ኦነግ ሙሉ መሰናዶ አድርጓል ዬሚል ጭምጭታ ነው ያለው። ሽዋን ዳግሚያ ወለጋ ዬማድረግ። ትኩረት ይሰጠው ዘንድ እማሳስበው ለአማራ ሕዝብ ነው። ሽዋ ውስጥ ለሚኖሩ አማራወች። አትኩሮቱ በአማራ አመራር ሥር ባሉት በአጣዬ፣ በሽዋ ሮቢት፣ በካራ ኩሬ ይሁን እንጂ አዋሳኝ አካባቢወችም ሥጋቱ ያካልላቸዋል። ቢያን በመንግሥት ተብዬው ያለው ወከባ ቢቆም፣ የይፋት ፋኖወች ከእስር ቢለቀቁ የተሻለ ይሆናል። ሽዋ ላይ በግል የሰከኑ አቅሞች እንደ አባት አደሩ አያለሁኝ። ችግሩ ተቋማዊ አለመሆኑ ብቻ እንጂ ለአማራ ሕዝብ ህሊና ብቃት ያላቸው ሊቃናት አሉ። ማያያዝ ቢቻል መልካም ነበር። ነገር ግን የስሜን አሜሪካ የፖለቲካ ወይፈን እያለ መከራው ዝልቅ ነው። ስንት የማይደፈር፣ የማይነካ፣ ለአብይዝም ከአቅም በላይ ዬሆኑ የአቅም መቅኖወች እንዴት ባለ ፋክክር ድብ እንዳለ እያስተዋል ነው። ዬሆነ ሆኖ ሽዋ ላይ ያላችሁ የሰከናችሁ፣ የረጋችሁ፣ አደብ የገዛችሁ ህሊናችሁን ውራጅ ለማድረግ ላልወሰናችሁ ልቅናወች በትህትና እማሳስበው የማዳኑ ተግባር ላይ ከህግ በታች ሆኖ ለወገን ደራሽ የሆነ ተቋማዊ ተግባር ቀድሞ ቢከወን ጥሩ ነው። ኦነግ አዲስ አበባን እንደጠቀለለው ሽዋን ካልጠቀለለ ፈጽሞ አይተኛም። ይህ እንዲሆንም ዬቤተ መንግሥቱም ፈቃድ ነው። ግማሽ ሚሊዮን ኦሮሞ ወገኖቻችን ከሱማሌ ክልል ወደ ሽዋ የተዛወሩበት ሚስጢርም ይኽው ...