ቢሆን። ምኞት ነው ተስፋን ያጨ። #የአይዟችሁ ሠራዊት ያስፈልጋል።

ቢሆን። ምኞት ነው ተስፋን ያጨ። #የአይዟችሁ ሠራዊት ያስፈልጋል።



 
 
በቀጣይ ሊሆን የሚገባው ዬእርዳታ ሥርጭት ተጓዳኝ አመክንዮ ነው። ላም እረኛ ምን አለን ማድመጥ ላልተሳናችሁ ነው ይህን ዕይታዬን እማጋራው። 
 
ማህበረሰቡም ይህን የአቨው አስተውሎ ሊያደምጠው ይገባል። ሁሉ ነገር በመንግሥት ብቻ አይሆንም። ሲቢል ድርጅቶች ይህን ክፍተት ሊሞሉት ይገባል። 
 
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ህወሃት በለቀቀው ቦታ ሽሬ ይመስለኛል የተከዘነ የእርዳታ እህል ለነዋሪው ሲከፋፈል አዬሁኝ። መልካም ነገር ነው። ህይወት ማትረፍ ለሥጋ ሳይሆን የነፍስ ነውና። 
 
ለምን ዬተደራጀ ተግባር አልተከወነም ልል አልችልም። አንድ ኩታራ ልጅ ነበር ሥም ጠሪው። በጦርነት ቀጠና ውስጥ ላለ አስተዳደር፣ ሠራዊት በልጅነት ስላዬሁት የሚክዶናል ቨርገር እንዳልሆነ እረዳለሁኝ።
 
ይህ ባይሆን ምርጫዬ ነበር። እርስ በርስ ውጊያ ስልጣኔ አይደለም። በእኛ ቢበቃ። ዬሆነ ሆኖ እህሉ ከታደላቸው ነዋሪወች ውስጥ አንዲት እናት አዬሁኝ። 
 
ነጠላቸውን ውልቅ አድርገው እንደ ገመድ እንዲያገለግል፣ ፍግም ብለው ተጎንብሰው 25 ኪሎ ይሆናል በዓይን ስገምተው ያን ተሸከሙ። እና ወደ ቤት ተጓዙ።
 
በዚህ ውስጥ ብዙ ርብሽብሽ፣ ብጥብጥ ዬሚያደርግ ሃሳብ ነሰተኝ። እስከመቼ? ስለምንስ? ለእነኝህ ደካ እናቶች ያልሆነ ዬ50 ተጋድሎ አልቦሽ ሂደቱን በምልሰት ቃኜሁት? እናቴን ያሰቃዬኋት፣ ያስጨነቅኳት፣ ያከላተምኳት ታወሰኝ። እናም አንጀቴ ተላወሰ።
 
ስፈጠር እንዲህ ሆኜ ስለሆነ መዳን አልችልም። የበዛ ችግር አለብኝ። በጣም ዬበዛ። እኔን ደፍሮ መርዶ ዬሚነግር አልነበረም። ዛሬ ደግሞ ሰርክ መርዶ ሆነ ያው ማህበራዊ ሚዲያ እንጂ በቤተሰብ ቅንጣት አይነገረኝም። አግደውኝ ነው ዬኖሩት ፌስቡክ እንዳልሳተፍ።
ዬሆነ ሆኑ አካባቢውን ለሚያስተዳድሩ ለወደፊት ዕይታዬን ላጋራ። ይህ ችግር ስላልተቀረፀ ነው እንጂ ጌዴኦ፣ ሱማሌ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ አፋር፣ አማራ ላይም ዬደረሰ ይሆናል።
 
ምክንያቱም ሲስተሙ ሰውኛነት ከራቀው 50 ዓመት ሆኖታል። መተዛዘን፣ አይዟችሁ መኗል። ከውስጣችንም ዬለም።
እኔ የሥርዓት ለውጥ ስመኝ የጭንቅላት ሥር - ነቀል ለውጥም፣ የተጠረገ ፃዕዳ ልቦናም ጉድጓድም፣ ጎድጓዳም ያልሆነ እንደሚያስፈልግ አበክሬ አምንበታለሁኝ። ሀ ሄዶ ለ ቢመጣ ዬኢትዮጵያ እናቶች ዘወትትር ዕንባ ነው የሚለቅሙት። 
 
ዬሆነ ሆኖ ወደፊት ለእናቶች ዬእርዳት እህሉን የሚያደርስ ከቤታቸው ድረስ ግብረ ኃይል ሊደራጅ ይገባል። ወይንም እዬገፋ የሚወስዱበት #ካሬታ በነፍስ ወከፍ ሊዘጋጅላቸው ይገባል። 
 
አማራ፣ አፋር፣ ትግራይ ወጣቶች በጦርነት ታጭደዋል። ዬቀሩ ወጣቶች ግን በዚህ መሰል ተግባር ቢሠማሩ መልካም ነው። ዬወጣት ማህበራት ቢያንስ የሰባዕዊ ተግባራት ላይ ቢያተኩሩ። 
 
በአርቲስት ሜላት ሠርግ ዬታደሙ ወጣቶች "ደራሽ" የሚባል ተቋም ብልሆች ጎንደሬወች እንዳላቸው በስይፋሻ ሸው ቃለ ምልልሷ ገልፃለች። 
 
ቁጥራቸው ወደ 300 እንደሚጠጉ፣ ሴት አባል እሷ ብቻ እንደሆነች። ለነገሩ አንባሳደራቸው ናት። አሁን "የባሌ አንባሳደር ነኝ" ስላለች ድልድዩ ካልተቋረጠ። ዕንቁ ነገር ነው።
 
የሊቀ ትጉኃኑን ዬጎንደሮችን "የደራሽ" አባላትን ለመከራ ለችግር ፈጥነው ዬሚደርሱ አገር በቀል ቀይ መስቀል ልንላቸው እንችላለን። ወድጃቸዋለሁኝ። እንዲህ ዓይነት ትውልድ ይናፍቀኛል። አዛኝ፣ አስተዋሽ፣ አቋጣሪ ትውልድ። ዬአይዟችሁ ሠራዊት!
 
ይህን ልምድ ወስዶ በጉልበት ዬሚያግዙ ወጣቶች ቢኖሩ መልካም ነው። 25 ኪሎ ለአንዲት እናት ሸክም ይከብዳል። ይህ ደግሞ ቀጣይ ነው። ዬተወሰደው ያልቃል። ነገም እንዲህ ሊቸገሩ ነው።
 
ዬተረጋጋ አዬር ሲፈጠር ይታሰብበት። ለሴቶች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ አካላቸው ለጎደለ በአቅራቢያቸው እርዳታውን እንዲያገኙ ዬማድረግ አዲስ ስልት ሊቀዬስ ይገባል። ወይንም በዬቤታቸው ወይንም በዬሠፈራቸው በራፍ ዬማድረስ መላ ቢቀዬስ። 
 
በተለይ ከተማ ውስጥ ላሉት። መንፈሱም፣ አዬሩም ስጋት፣ ጭንቀት እና ህውከት ስለሆነ እናቶች አቅም ዬላቸውም። በዛ ላይ እራህቡም አለ። 
 
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/10/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።