ልጥፎች

#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። oct 20.2020

ምስል
  #ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።" #ኢትዮጵያ የማንም "ውሽማም" አይደለችም። ማህከነ። "ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርልኝ።"       • ይኽው ሊንኩ።አገር ከበለጠባችሁ፤ ዬጊዜ አታሞ ካልረታችሁ። https://www.youtube.com/watch?v=jaaelCVVHic&t=451s የአሁን ዋና ዋና መረጃዎች!DereNews Oct. 19 2022 #derenews #zenatube#Ethiopiannews# ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" ስትባል፣ ኢትዮጵያ "ዬማንም ተወሻሚ" ስትባል አይጎረብጥም፣ አይቆረቁርም? ስለማን የምን ንጥረ ነገር ይሆን ዬሚተነፈሰው? ውስጣችን ለእናታችን እንዲህ ሸካራማ፣ ኮረኮንችማ፣ አሜኬላ በቀል። ከእናት አገር ጠረን ዕለታዊ ሰብዕና በልጦብን ይሆን? #በር ። ኢትዮጵያ ከቅኔም፣ ከስዋሰውም አልፋ እና ንራ ኢትዮጵያ #ሰማያዊ #ምስባኽክ ናት።።።።።።።።።።።።። ቫወልም ናት። አናባቢ። ኮንሰነትም ናት ተነባቢ። #ቅምሻ ። ጎንደር ላይ ሲዘንብ የባጀው የዲን በረድ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ መጥቷል። በተለይ "ኢትዮ" ብላችሁ ምንም ተቋም የምትከፍቱ፣ የምትጀምሩ ወገኖቼ በልኳ ለመሆን እሰቡበት። ኢትዮጵያ ረቂቅ መንፈስ ናት። የራሷ ዬሆነ አንጡራ ማንነት ያላት የድንቅነሽ ድንቅ ናት። ዲስፕሊኑን የመጠሪያዋን ዬሚመጥን፣ የሞራል አቅም ይጠይቃል። የአውራ አገር መጠሪያ ነውና። ዬማይፋድስ፣ ዬማይነጥፍ ፏፏቴ ሥም ነው ያላት ኢትዮጵያ አገራችን። ይህን ብዬ ዬፃፍኩት በ2014 ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው ላይ ነበር። በፀጋዬ ራዲዮም በተደጋጋሚ አቅርቤዋለሁኝ። በቅርቡም ጹሐፋን በንባብ ዩቱብ ቻና...

ሌላው አዋሳ ላይ የአቤል ደም ይጮኃል ብለውን ነበር፣ የእሳቸው የደም ዘመንስ እዮርን አድነኝ አይል ይሆን? oct 20.2020

ምስል
  ሽሽት እና የሙት ዓመት። የትናንት የፓርላማ ውሎ ሽሽት በበዛ ሁኔታ፣ መውቲነት በፍፅምና አይቻለሁ። ኃላፊነትን ወስደው አያውቁም ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሽሽት ላይ ናቸው፣ እሳቸው የማይሸሹት ቢኖር ብልጭልጭታን ብቻ ነው። ለምን ብትሉ የገዳን ወረራ፣ የገዳን አስምሌሽን፣ የገዳን ዲስክርምኔሽን ስለሚጋርድላቸው። አፋር በ100 ቀኑ የሥራ ፕላናቸው የመጨረሻ የክልል ጉብኝታቸው ነበር። ደረግ የወደቀው ሰው በመግደሉ ነው ብለው ነበር። የአመክንዮ መፋለስ ወይንም የትንታኔውን ጮርቃነት በቀንበጥ ብሎጌ ሞግቻቸዋለሁ። አሁንስ ነው ጥያቄው በሰርክ ሰው እዬሞተ ነው። በመንግሥት ሎጅስቲክ በሚደገፍ ሽፍታ። እና የመንግስታቸው ስንብት እንደምን አልታያቸውም። በሳቸው ሎጅክ አማካኝነት። አገላለፁ የቀጣይነት ቃናም አለው። ሌላው አዋሳ ላይ የአቤል ደም ይጮኃል ብለውን ነበር፣ የእሳቸው የደም ዘመንስ እዮርን አድነኝ አይል ይሆን?     በዚህው በዓዋሳ ጉባኤ አንድ ተናጋሪ ባቀረቡት ነገረ የበርበሬ ገብያ አማካኝነት ምን ገብያው ብቻ ያልታመመ ማን አለ ብለው ነበር፣ እና ትናንት የጤናቸው ስለመሆኑ አንድ የፌስቡክ ጦማሪ አቶ ሻንቆ ካሳይ የጣፋትን አንብቤ ነበር። ግን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ያንግዜ የታማሚ ማህበርተኝነታቸውን ነግረውን ነበር እና ተሻላቸው ወይንስ ባሰባቸው ይሆን? በጥቅሉ በትናንቱ የሙልጭታ ጭለጣ መውቲነት አዬሁኝ። አምላኪዎቻቸው፣ በፍቅር እፍ ያሉት ሁሉ ምኑን አንስተው ምኑን ከምን እንደሚያደርጉት ያያቸው ሰው። ለዛቸው መጣጣ፣ ቃናቸው ሾጣጣ፣ አምክንዮቸው የተላመጠ አገዳ ነው የሆነው። የገረመኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ገበሬው የፖለቲካ ውክልና የሌለው መሆኑን ጥፌ ነበር። እስከ ትናንት ድረስ ማህበራዊ መሠረታቸው ዲታዎች ነበሩ፣ ት...

ገራገሯ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች።

ምስል
  ገራገሯ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች።     ገራገሯ የሰባዕዊ መብት ተሟጋቿን ወት አስምራ ሹምዬ አቶ ኦባንግ ሜቶ ሆነ ዶር ዳንኤል በቀለ ባሊህ ሊሏት ይገባል። ኑሯዋን በኪራይ ትኖርበት የነበረው ቤት ያሳያል ያች ቅን። ያቺ ከነተፈጥሮዋ ያለች ደግ ሸበላ የት እንዳደረሷት አይታወቀም። ቤተሰቦቿ ምን እንደ ገጠማቸው አይታወቅም። ባለቤት የሌለው ህዝብ በወዘተረፈው የገዳ ዘር የማፅዳት ዘመቻ ፍዳውን እያዬ ነው። ዋቢ የለውም ከፈጣሪ በስተቀር። ይህቺ ደግ ገራገር ህይወትሽ ስለምን ተረፈ ተብላ ነው ይህን ሁሉ ማዕት የምታዬው። በቁሙ የከሰለ የሴቶች የወጣቶች እና ህፃናት ሚር መ/ቤት ደግሞ አለ። ግዑዝ የሆነ ነገር። ወጣት አስምራ ሹምዬ የት ናት? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ኃራም ገዳ!    

ዳርቻው ምን ይሆን? …ኃራም ገዳ! oct 20.2020

ምስል
  ዳርቻው ምን ይሆን? የህይወትን ጣዕም ሳያውቁ፣ህይወት እንደናፈቃቸው፣ ወላጆቻቸው እንደሳሷቸው፣ ተስፋን እንደ ሰነቁ፣ በማያውቁት፣ ባልነበሩበት፣ በሌሉበት የፖለቲካ ትርምስ በማህበረ ኦነግ ዕምቅ በቀል ድራሻቸው ዕልም፣ ጥፍት ያለው የደንቢደሎ የአማራ እጩ ሊቃናት ሁኔታ ዳርቻው ምን ይሆን? በትናንቱ በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ የተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ ዲስኩር ውስጥ የተረዳሁት ቢኖር አማራን የማጥፋት፣ የማክሰል፣ የማሸማቀቅ ተግባር የተልዕኳቸው አውራ መሆኑን ተርድቻለሁ። እንዲህ ከምንሰቃ ኢትዮ 360 ሚዲያ አለኝ የሚለውን መረጃ ነግሮን ቁርጣችን ባወቅን። መረጃውን እንዳያወጣ የሰጋበት የጭካኔ አይነት ሰውነታችን ለምዶት የግፍ ሞት ሰርካዊ የህይወታችን አካል ሆኗል። መርዶስ ለካ ይናፍቃል። ይገርማል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie …ኃራም ገዳ!    

የሙጣጭ ኤሉሄ ህቅታ። oct 20.2020

  የሙጣጭ ኤሉሄ ህቅታ። በትናንትናው የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ የዲስኩር ውሎ እንጥፍጣፊ አልቦሽ የሆነ ግዙፍ አመክንዮ አስተዋልኩኝ። በግዜ ስለነበር የተኛሁት እኩሌሊት ነቃሁ። ሌሉትን ሁሉ አሰብኩት። አወጣሁት አወረድኩት። በልቦናቸው፣ በህሊናቸው፣ በመንፈሳቸው ውስጥ አማራ የሚባል ማህበረሰብ እርሾ አልቦሽ እንጥፍጣፊ ሙጣጭ ቤተኝነት አልነበረውም። ሳያኖሩን አመናቸው እናም አመከኑን። የክደታቸው፣ የውሸታቸው ቋት መሰረቱ መጪው መከራ አስፈርቶኛል። ግደሉ እያሉ ያሰማሯቸውን የቀኝ እና የግራ ክንፎቻቸው መንትዮሾቹ የቤንሻንጉል ጉምዝ እና የኦሮምያ መስተዳድር ቁንጮዎች ጆከሩን የአማራውን ካባ ሸላሚ እና አመስጋኝ ጨምሮ በጭካኔያቸው ይቀጥሉ ዘንድ ግፋበት ብለዋል። ትንሽ እንጥፍጣፊ አዘኔታ? ኦ! አምላኬ። በትናንቱ ውሎ ኦነግ ሸኔም ነፃ አውጥተውታል። በደሉን ሱዳንን ሄዳችሁ ጠይቁ ተብሏል። በትናንቱ ንግግራቸው በአማራ ላይ ንፁህ ዲስክርምኔሽን ፈፅመዋል። ከዚህ ቀደም አልፈፀሙም ማለቴ ግን አይደለም። የአማራ ደም ጅረት እና ውቅያኖስ ቢኖረው፣ ንግሥናቸውን ሥርዓት በዛ እዬዋኙ ይፈፁሙ ነበር። ሰባዕዊነት ቀርቶ ጨካኝ መሪ ሆነው አልታዩኝም። ጨልመው ታዩኝ። ትዕቢታቸው፣ ልግጫቸው፣ መስቃቸው የት ሊያደርሳቸው እንደሚችል እጬጌው ሂደት ይመስክረው። መጋቢት 18/2010 በማን ሙሉ ድምፅ ይህን የሚመኩበትን ቦታ እንዳገኙት ያውቃሉ። ዛሬ ያ ተረስቶ፣ ያ የጭንቅ ቀን ተክዶ ለዚህ መከረኛ ህዝብ ለሞቱ፣ ለጥያቄዎቹ ዕውቅና ለመስጠት ታበዩ። በጣም ተንጠራሩ። ከሳቸው በላይ ፈጣሪ ስላለ መጨረሻውን ይጠበቃል ችሎቱ። የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ፣ የአማራ ወዳጅ እንደ ወገን የትናንቱን ክህደት ከልብ በማድመጥ ለዚህ ቅን ህዝብ ከሄሮድስ አመራር የሚላቀቅበትን ብልኃት ፈጣሪ እንዲ...

የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ መሻት። oct 20.2020

  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን። "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፣ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። ምሳሌ 16/9" የነገህ ፀሎት። 1) የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ መሻት። 2) በወበራ ተመክሮበት በደንቢደሎ የአማራ የዩንበርስቲ ተማሪዎች እገታና ሰቆቃ መዳረሻውን ለማወቅ መጓጓት። 3) አንድም የአማራ ክልል ተማሪ ወደ ሌላ ክልል እንዳይመደቡ መሻት። ወስብኃት ለእግዚአብሄር። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

ህም። ግራሞት ቀጥሏልoct 20.2019

ህም። ግራሞት ቀጥሏል። የኦሮሙማ ጠሚር አብይ አህመድ ሌጋሲ ቀለሙ ድንገቴ ነው። ለዚህም ነው ህም ቅደም የተባለው። በትናንትና በዛሬው የኦሮሙማ ሠርግና መልስ የታዘብኩት ጠሚር አብይ አህመድ ራሳቸውን ማምለካቸውን ብቻ አይደለም። ይልቁንም እንደ አምላክ እንዲታዩ ያለባቸውን የውስጥ ግብግብ አይቻለሁ። ይህ ማለት ምን ማለት ነው " አምልኮ አብይ የማምለኪያ ሥፍራም፣ አብያውያንም በአብይ አምላክ ሲሉ፣ አብይ ይሙት ሲሉ፣ " የሚደመጥበት ጊዜ እንደናፈቃቸው ነው ያዬሁት። ከዚህ ጋር ተያይዞ " ይህ በመካከለኛ፣ በአጭር ሞገድ የሚተላለፈው የአብይ የራዲዮ ጣቢያ፣ የአብይ ሾው፣ የአብይ ቴልቪዥን" ፋታ ከሰጣቸው የተፎካካሪያቸው የጃዋር መንፈስ በቀጣይ አይቀሬ ይመስላል። እንዲያውም ዜጋው ሁሉ ከግንባሩ ላይ አብይ እያለ ቢወቀር ይሻሉ። ሌት እና ቀን መስማት የሚፈልጉት፣ ሙገሳ፣ ውዳሴ፣ ምስጋና ብቻ ነው። አይሰለችም? አድማጩ እራሱ አይሰለቸውም። 19 ወራት ሙሉ የፕሮሚውን ወይንም የቢአይፒውን፣ የአርቲስቱን፣ የአክቲቢስቱን፣ የሰባኪውን ቦታ ሁሉ አራጠው ይዘው በቃ መፈንደቅ ነው፣ ልጅ እያለን አዲስ ልብስ ሲገዛልን ለብሰነው ካላደርን እያልን ወላጆቻችን እንደምናስቸግረው። መዲናዋ አዲስ አበባ ግን አካባቢዋ ግን ይህን መስላ ነው የዋለችው። ለመክደኛም ይሁን እጬጌው ህም።

0ct 20.2020 የኦሮሙማ መጥምቀ ሞጋሳዊ መደመር

  የኦሮሙማ መጥምቀ ሞጋሳዊ መደመር መደመር መወረር። መደመር መመዝበር። መደመር መጎርጎር። መደመር መሰርሰር። መደመር መፈርፈር። መደመር መደፈር። መደመር መመንጠር። መደመር መቦርቦር።

LIVE 🔴 ኢትዮጵያውያኑ ከአሜሪካ ኮንግረስ ተወካዮች ጋራ ምን መከሩ?|| ልዩ ዝግጅት

ምስል

ጨካኝነት ለመሪነት ሊያበቃ አይችልም።

  Shared with Public ጨካኝነት ለመሪነት ሊያበቃ አይችልም። "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱) አይዟችሁ የነጠፈበት፤ ማጽናናት ድርቅ የመታው፤ በቀውስ በጀት የሚተዳደር፤ በቅጥፈት ቦይ የሚፈስ፤ ቀደምትነትን የሚጠዬፍ፤ ህዝብን የሚጠላ የሚያሳድድ - የሚያሳቅቅ - የሚያቃልል- የሚያናንቅ መንፈስ ለመሪነት ለዛውም ሁለመናዋ በስጦታ ለከበረው የኢትዮጵያ መሪነት የሚታሰብ አልነበረም። ግን ተያይዘን ባበድንበት ወቅት በፈቃድ ሆ! ብለን ተቀበልን። አሁንም ተመሳሳይ ግድፈት ተፈፅሞ አረንቋ ውስጥ ተስፋችን እንዳይዘፈቅ ብርቱ ጥንቃቄ፤ የፀሎት እና የድዋ ጥረት ይጠይቃል። ካሳለፍነው መከራ መጪው ይገዝፋል። ስለዚህም በሁሉም መስክ ህሊናን አብቅቶ ማሰናዳት ይጠይቃል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት እያንዳንዷ እርምጃችን ማስተዋልን ሊጠጣ ይገባዋል። ፈቃዱ ቢኖር አቅሙ፤ ዕውነቱ ቢኖር ተመክሮው፤ ጽናቱ ቢኖር ልምዱ ሁሉም በዬዘርፋ ሊፈተሽ ይገባል። መሪነት በመፈለግ እና በመሻት ብቻ ሳይሆን ቅባዕም ይጠይቃል። ቅባዕው ከሌለ አይሆንም። እያንዳንዱ እራሱን ለመሪነት የሚያጭ ፖለቲከኛ ሁሉ እራሱን ገምግሞ በራሱ ዳኝነት እንቅፋት እንዳይሆን እራሱን መግራት ይገባዋል። ሁሉም ኑሮ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ቅባው ከሌለ ተያይዞ መንኮት ይሆናል። ይህ ሁሉ ግብር እዬተገበረ ነገን የተሰናዳ ማድረግ እንዲቻል ሆኖ ካልተደራጄ ደግሞ መዛገጥ ይሆናል። ከሁሉም ልዩ ጥንቃቄ የሚሻው ጉዳይ በመፈቃቀድ ላይ የሚፈጠር ሥርዓት ለማቆም መስማማት መቻል ይሆናል። በመዘላለፍ፤ በመወራረፍ፤ በመዘነጣጠል የምናተርፈው አገርም ትውልድም አይኖርም። አክብሮ መነሳት። አክብሮ መሞገት። አክብሮ የተሻለ ሃሳብ ማፍለቅ። አክብሮ መነጋገ...
ምስል
  ዬኢትዮጵያ #የህልውና #መሠረታዊ #ችግር ጠሚር #አብይ #አህመድ ናቸው።     ምዕራፍ ፲፩ "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ? ደህና ሰነበታችሁልኝ? ፲ን የአብይዝም ለያዥ ለገራጅ ያስቸገረውን ዬ፭ ዓመታት ውጥንቅጥ የአገዛዝ ገፀ ባህሬ አስተውለን አሁን ወደ ፲፩ኛው ዛሬ እንሸጋገራለን። "ቂጥ ገሊቦ ራስ ተከናኒቦ" ስለሆነው የፋንታዚው ልዑል የጠሚ አብይ አህመድ ውቂ ደብልቂ እና ረግረግ። #በቅናት ፤ #በምቀኝነት ፤ #በማናንሼ #ድውይ ዕሳቤ ተነስተው ኢትዮጵያን እያመሷት የሚገኙት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ናቸው። ስለሆነም የኢትዮጵያ የህልውና ችግር ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ናቸው። 1) የኢትዮጵያ፤ 2) የስሜን ኢትዮጵያ፤ 3) የአፍሪካ ቀንድ፤ 4) የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ፤ 5) የአህጉራችን የአፍሪካ የችግር ምንጭ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እና ፈንታዚያቸው ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በልዕልና ልቅና ዬነበራትን የተፈሪነት፤ የከበሬታ፤ የግርማ ሞገስ ማህባ ቦታ አውርደው የጣሉበትን ቦታ ውስጣችን እዬቆሰለ እዬታዘብን ነው። በሁሉም ዘርፍ ዛሬ ኢትዮጵያ ከደረጃ በታች ናት። ከትንሿ ከጁቡቲ እንኳን ጋር ስትነጣጠር። የሆነ ሆኖ የአህጉሩ አብሪ ኮከብ እሆናለሁ #አንጋጠው ልፍጭ ብለው ባይፍጨረጨሩ እንደ ተለመደው ባይሰሙም እንመክራለን። አይዘብዝቡ። አይዝረክረኩ። ሁሉን ነስቷቸው ሁሉን የሚፈልጉ መሪ መሆናቸው ደግሞ ይገርመኛል። ቅኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ከወፈፌ ጋር መወፈፍ ልማድህ አይደለም እና አደብህን ጠጥተህ፤ በተደሞ ተከውነህ ምክክርህን ከፈጣሪህ ከአላህ ጋር ብቻ አድርግ አደራ። እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነውና ጨዋነትህን የሚመጥን ትጉህ፤ አዛኝ፤ አጽናኝ የአይዟችሁ ሙሴያዊ መሪ ይሰጥኃል። ጠብቀው...

እናታዊነት በቅንነት ለውስጥነት።

ምስል
  እናታዊነት በቅንነት ለውስጥነት። • ለኩላሊት ድክመት ትንሽ ብልስ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሐር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ጠብታ።             ባለፈው ሳምንት ስለ ኩላሊት ጠጠር ትንሽዬ አቅጣጫ ጠቁሜ ነበር። ምን ያህል እንዳዳመጣችሁት አላውቅም። ምን ያህል ሼር እንዳደረጋችሁት አላውቅም። ድውያኑ ማህበረ ግንቦታውያን ያው መኖራቸው ቀብር ስለሆነ ይህንንም ይገድቡት ያቅቡት ይሆናል። የሆነ ሆኖ መከታተላችሁን እያዬሁኝ ሚዛኑ ይለካል። በጣም የሚገርመኝ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ሰው መሆን የተሳነው ህዝብ ብዛቱ እጅግ ይገረምኛል። በቃ ልቡን አውልቆ፤ ህሊናውን አውልቆ እራሱን ተውሶ በውራጅ ማንነት የሚኖረው ህዝብ ብዛት ግርም ይለኛል። በራሱ የሚቆም የለም። እራሱን ሆኖ ተፈጥሮ ጨርቅ ቀዶ አልብሶ፤ መሃያ ከፍሎ ያላስተዳደረው ነፍስ እንዳሻው ይነዳዋል። ይገርመኛል። አቁም ሲል ያቆማል፤ ሂድ ሲል ይሄዳል። አድርግ ሲል ያደርጋል። አታድርግ ሲል አያደርግም። ሰው ራሱን ፈርቶ ከኖረ፤ ሰው እራሱን ወርጆ ከኖረ አልተፈጠረም ከምል አልተጸነሰም። ያልተጸነሰ ደግሞ ምንም ነው። {} • ኩላሊት ስለምን ይደክማል። • ሃኪም አይደለሁም። ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁኝ የባይወሎጂ እና የኬሚስተሪ ተማሪ ነኝ። አነባለሁኝም። እኔ እንደማስበው ግን የኩላሊት ድክመት ከሚያመጡ ውስጥ። (1) ኢንፌክሽን ወይንም ከዛ ጋር የተያያዙ በሽታወች ይመስሉኛል። በዚህ ዘርፍ ከቢቢሲ የ አማርኛው ክፍል እንዳነበብኩት ከሆነ ሽታ ያላቸውን ሳሙና ነክ ነገሮችን ለመታጠቢያ ነገር መጠቀም ለኢንፌክሽን እንደሚያጋልጥ አንብቢያለሁኝ። (2) ከዘር የሚተላላፍ ይህ ዕውነት የሆነ ነገር ነው። (3) የፉኛ ማነስ ይህም ዕውነት። አንዳንድ ኦርጋኖች ሲ...

መታቆር። oct 17.2020

  መታቆር። ህወሃት ሥልጣኑን ከለቀቀ ጀምሮ አቅም አባክኛ አላውቅም። ታግዬዋለሁ። ከሥልጣኑ ወርዷል። አሁን መታገል ያለብኝ ሰውን እዬገደለ ስለሰው አቀድኩ የሚለውን የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ነው። ዛሬ ግን ባዬሁት የሁለትተኩል ዓመታት ትዝብቴ ግርም የሚለኝን ላነሳ ወደድኩኝ። ህሊናቸው ውስጥ የታቆረ ዕምቅ ድንብልብል መከራ አለና። የተነሱበት ፀረ አማራ፣ ፀረ ተዋህዶ ነው። በዚህ በለስ ቀንቷቸው 27 ዓመታትን ቢገዙም ግን ወድቀውበታል። አወዳደቃቸውም እርሾ አልባ ነው። አይመልስህ ተብሎ። የሚገረመው ነገር ከሚዲያ አዘጋጆቻቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዛሬም ህወሃት ሲመሰረት ከነበረው ዕሳቤያቸው አንዲት ስትዝር ፈቅ የለም። እርግማን። ሌላው ቀርቶ ምዕቱ 21 ኛው ክ/ ዘመን ሥልጣኔውም ዲጂታል መሆኑን የሉበትም። አንድም የህወሃት ፖለቲከኛ የወደቀበትን እንኩሮ ሃሳብ ኮንኖ ለመዳን ሲተጋ አይታይም። የሰው ልጅ የወደቀበትን መንገድ እንደምን መዳኛው አድርጎ ያመልከዋል? የተገለበጠ ጉድ። ያሉበት ቦታ የክብር ነውን? የሥነ - ልቦና ቀውስ የለባቸውምን? አማራ እኮ ነው ደግፎ ያስገባቸው፣ ያኖራቸውም የግርባው ብአዴን ሙሉ ድጋፍ ነው። የጣላቸውም የዚህን ድምፅ ማጣታቸው ነው። ማንም ይሁን ማንም የአማራ ድጋፍ ከሌለው ገዢ የመሆን ተስፋው ቅዥት ነው። አሁንም አገር ለመምራት ያስባሉ ህወሃቶች። ግን በፀረ አማራ ኃይሎች ስብስብ የበላይነት። አይሰቡት። አይዳክሩም። አይደለም እነሱ ኦህዴድ ቀፎውን ነው ያሉት። ኦህዴድም ፀረ አማራ ኃይሎችን ክበቡኝ ብሎ ሲመክር፣ ሲዘክር ባጄ፣ የምድር እንቧዩን ብአዴንን በሞጋሳ ጥምቀት አስምጦ እንደ ደመቅን እንቀጥላለን ብሎም አሰበ። 50/60 ወጥቷል ትልሙ። አይደለም ለዛን ጊዜ አሁንም ያለው በቀውሱ የኦፕሬሽን ትንፋሽ ነው። በፋቲክ። ህወሃት ከራሱም ው...

ናርጋ ስላሴ ቤተክርስቲያን !

ምስል
ናርጋ ስላሴ ቤተክርስቲያን ! ናርጋ ስላሴ በጣና ሐይቅ አማካኝ ርቀት ላይ በሚገኝ ትልቁ ደሴት 'ደቅ' ደቡባዊ ጠርዝ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህን አብያተክርስቲያን ያሰሩት በጎንደር ዘመን ከነበሩት ትልቅ ሰው መካከል እቴጌ ምንትዋብ ናቸው፡፡ ናርጋ እቴጌዋን ጨምሮ ከበርካታ ነገስታትና የዕምነቱ አባቶች የተበረከቱ ፎቶው የሚተየውን ጨምሮ ንዋዮ ቅድሳት ይገኙበታል፡፡ ደቅ ደሴት ከጣና ደሴቶች ትልቁ ሲሆን በወስጡ 7 ያህል አብያተክርስቲያናትን የያዘ ነው፡፡ ከደሴቱ ምስራቅ ዳርቻ የጎንደር ነገስታት አስከሬን በክብር ያረፈበት ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ይገኛል፡፡ ናርጋ ስላሴ ከጣና ሐይቅ ደሴቶች በስፋቱ አንደኛ ከሆነው ደቅ ደሴት ላይ በምዕራባዊ ክፍሉ የሚገኝ ቤ/ክርስቲያን ነው።  

የአብይዝም ሸምቀቆ። oct 17.2019

የአብይዝም ሸምቀቆ። የአብይዝም ሸምቀቆ ከድንገቴው ሱናሜ ጋር ቀለበተኛ ነው። አሁን አንድ ህብረ ብሄር ሚኒሻ ማደራጀት ፈለገ። ሌት እና ቀን ጦር ማደራጀቱ እንዳይነቃበትም ዘያ።ዬደ። ቅምጡን አስነሳ እና አስፎከረ። ብቅ ብሎ ዲስኩር አደረገ። ዲስኩሩ በእንግሊዘኛም ተቀኝቷል። ለጀርባ አጥንቱ ለአቶ ኽርማን ኩኽን ነው ነገርዬው። ፋከራው አማራን እናስታጥቃለን። እቅዱ የአማራ ታጣቂ የሚባል የለም በጥላቻ የመገለውን መንፈስ አሰባስበን የራሳችን ጉዳይ እናስፈፅምበታለን ነው። እራሳቸው ጠቅላዩ አማራ የሚል ቃልም ህዝብም መስማት አይሹም። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና በአንድ ቀን ምጥጥ ብለን ብናድርላቸው ይሻሉ። አይወዱንም። ተዋህዶም የባዕለ ዕለቷን ከሚሰሙ ቢሞቱ ይመርጣሉ። ከራሳቸው ጋር እርቀሰላም ሳያወርዱ ነው አስታራቂ የሆኑት። ለዚህ ደግሞ ታጥቀው ተነስተው በሁሉም ዘርፍ ምንጠራውንም፣ ስረዛውትም ሁሉንም ዓይነት መከራ በጥድፊያ እያጣደፋት ነው። የልግጫው ልግጫ በዛ ሰሞን ሙሉ አቅም አለኝ ያለ መከላከያ ዛሬ የቤንሻንጉልን ሸፍጥ ከአቅሜ በላይ ነው ይላል። አሁንም የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና የውጭ ኃይል ቢወር ምን ሊኮን ነው። ለአንድ ጭንጋፍ የጫካ ሽፍታ ሌላ ሚሊሻ የሚደራጅለት? የግብፅ ሠራዊት ነውን? ለነገሩ ቀውሱ እንዲቀጥል ይፈለጋል። ያው ለዛ መተተኛ ምርጫ ሲባል አማራም ኦርቶዶክስም ይገበራሉ ለ10 ዓመት። ሁለት ተርም ነው ዕቅዱ። ሞት ንክች አያደርገውም ቤተ መንግሥቱን። ሌላም መፈንቅል አያሰጋውም። ደኃ የአማራ ገበሬ ግን ስጋቱ ነው። ለምን? ቁጥሩ፣ ክህሎቱ፣ የመቻል ጥበቡ፣ ጨዋነቱ፣ የሥነ - ልቦናው ልቅና ቦንብ ነው በበታችነት ለሚማስነው ዝክንትል ህሊና፣ ድሪቶ ልብ ሁሉ። እና ጠቅላዩ ብቅ ብለው የሸመቁትን ሸምቀቆ በሌላ በርዥን ይዘው ብቅ ብለዋል። ከሁሉ በላይ ግን ፈ...

እቴጌ መቀሌ 0k17.2019

ህም። ነው ዘንድሮ። እቴጌ መቀሌ ጦርነት አውጃ፣ ጁቡቲን ሱማሌ ላንድ ሌላ ጥቃት ሰንዝረው፣ ጎንደር ከተማ ዙሪያውን ቀውጢ ሆኖ፣ ድሬ እና ሀረር ጎረምሶች እዬመሯት፣ አጣዬ እና ኬሚሴ ሌላ ጦር ታውጆ፣ አዲስ አበባ በጭንቀት ተወጥራ፣ አዳማ፣ ደብረዘይት በጎረምሳ እዬታመሱ፣ የውህድ ፓርቲ ዘፈን ይደለቃል። መሬት እኮ ልትፈነዳ ተቃርባለች። እራሱ መከላከያ በዬዞጉ ጎድቯል ወይንስ ልቡ ከኖቤል ተሰክቶ ይሆን? ይህም አይታወቅም። ይህም አይደመጥም። ይህ ሁሉ ታምቆ ቤተ መንግሥት አንድ ጊዜ ከካቢኔው ሌላ ጊዜ ከኦዳ ዛፍ ጋር ፈንጠዝያ ላይ ነው። የዲፕሎማት ማህበረሰብም አንድ ነገር ቢፈጠር መውጫችን ብለው ያሰቡት ነገር የለም። ሌላም መገዳደል ይኖር እላለሁኝ የኦዳውን ዛፍ አስተውዬ በአርምሞ እያዬሁ። ይጨንቃል። ያስፈራል። ፀሎት።

ኦዳ እና አዲሱ የኦነግ ኦዴፓ የኃይል አሰላለፍ። 2019

ኦዳ እና አዲሱ የኦነግ ኦዴፓ የኃይል አሰላለፍ። ኦዳን ይሳለሙ ዘንድ ጠሚር አብይ አህመድ ቲም ጃዋርን የካደው የኦነግ ኦዴፓ የለሜ ቲም ምህረት ጠይቋል። ኦዳ ለአማላጅነት ቀርቧል። የራበው ልጅ ጡት ሲያጎርሱት እንደሚፍለቀለው በልጃዊ ባህሪ የሚታወቁት ጠቅሚር አብይ አህመድ ኦዳን ትኩር ብለው እያዩ ተፍለቅልቀዋል። ሌሎችም ክልሎች ድርጅታዊ ሥራ ተስጥቶ ይህን ይከውናሉ ብዬ አስባለሁ። ትግራይን አይጨምርም። የሚገርመው በጠቅሚሩ የሥልጣን ሹመት አፍንጫኽን ያሉት የኦሮምያ ከተሞች በፌስታል ፖለቲካ አራማጁ በአቶ አዲሱ አረጋ አሰተባባሪነት የኖቤል የድጋፍ ሰልፍ እጣ ነፍሳቸውን ወጥተዋል። ይህ የፖለቲካ ቁማር ትልቅ ፍሬ ነገር ይነግረናል። ከአምስት ተተርትሮ የነበረው ኦዴፓ ወደ አንድ ማጋደሉን። ኦዴፓ ውስጥ፣ የጃልማሮዊ፣ በቀላውያን፣ ጃዋርውያን፣ ለማውያን፣ አብያውያን፣ ዳውዳውያን ነበሩ። ግባቸው ኦሮሞን የአፍሪካ ገዢ አድርጎ ማውጣት ቢሆንም የቴክኒክ ጉዟቸው ግን ዥንጉርጉር ነበር። ይህም በመሆኑ ኦሮምያ ከፌድራሉ አፈንግጦ በራሱ ጊዜ ሉዕላዊ መንግሥት ሆኖ ቆይቷል። ኢትዮጵያም በዚህ የታበዬ መንፈስ ስትቀጠቀጥ ለ15 ወራት ባጅታለች። ኦነጋውያኑ፣ የኦሮሞ ሊሂቃን የጠሏት ኢትዮጵያ የኖቤል ተሸላሚ አድርጋለች። ለዚህም ነው ሥርጉትሻ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስተምህሮ የነበራት። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ነው በማለት ኢትዮጵያን ስትዘክር የኖረችው። የሆነ ሆኖ እጅ የሰጠው የለማ ኦዴፓ ቡድን የጃዋር ቡድን ከድቶ ኦዳን በወርቅ አሰርቶ ምህረት ጥዬቃ ላይ መሆኑን አይተናል። የሚገርመው የኦነግ ኦዴፓ ቲም ለማ ጃዋርን መክዳቱን በፕሮፖጋንዳ ግርዶሽ ለመከለል መሞከሩ ኢትዮጵያ ማስተዋል ያላቸው ልጆች የሏትም የማለት ቧልት ነው ለእኔ። የጃዋር ቲም ለለማ ቲ...