የአብይዝም ሸምቀቆ። oct 17.2019
የአብይዝም ሸምቀቆ።
የአብይዝም ሸምቀቆ ከድንገቴው ሱናሜ ጋር ቀለበተኛ ነው። አሁን አንድ ህብረ ብሄር ሚኒሻ ማደራጀት ፈለገ። ሌት እና ቀን ጦር ማደራጀቱ እንዳይነቃበትም ዘያ።ዬደ። ቅምጡን አስነሳ እና አስፎከረ።
ብቅ ብሎ ዲስኩር አደረገ። ዲስኩሩ በእንግሊዘኛም ተቀኝቷል። ለጀርባ አጥንቱ ለአቶ ኽርማን ኩኽን ነው ነገርዬው።
እራሳቸው ጠቅላዩ አማራ የሚል ቃልም ህዝብም መስማት አይሹም። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና በአንድ ቀን ምጥጥ ብለን ብናድርላቸው ይሻሉ። አይወዱንም።
ተዋህዶም የባዕለ ዕለቷን ከሚሰሙ ቢሞቱ ይመርጣሉ። ከራሳቸው ጋር እርቀሰላም ሳያወርዱ ነው አስታራቂ የሆኑት። ለዚህ ደግሞ ታጥቀው ተነስተው በሁሉም ዘርፍ ምንጠራውንም፣ ስረዛውትም ሁሉንም ዓይነት መከራ በጥድፊያ እያጣደፋት ነው።
የልግጫው ልግጫ በዛ ሰሞን ሙሉ አቅም አለኝ ያለ መከላከያ ዛሬ የቤንሻንጉልን ሸፍጥ ከአቅሜ በላይ ነው ይላል። አሁንም የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና የውጭ ኃይል ቢወር ምን ሊኮን ነው። ለአንድ ጭንጋፍ የጫካ ሽፍታ ሌላ ሚሊሻ የሚደራጅለት? የግብፅ ሠራዊት ነውን?
ለነገሩ ቀውሱ እንዲቀጥል ይፈለጋል። ያው ለዛ መተተኛ ምርጫ ሲባል አማራም ኦርቶዶክስም ይገበራሉ ለ10 ዓመት። ሁለት ተርም ነው ዕቅዱ። ሞት ንክች አያደርገውም ቤተ መንግሥቱን። ሌላም መፈንቅል አያሰጋውም።
ደኃ የአማራ ገበሬ ግን ስጋቱ ነው። ለምን? ቁጥሩ፣ ክህሎቱ፣ የመቻል ጥበቡ፣ ጨዋነቱ፣ የሥነ - ልቦናው ልቅና ቦንብ ነው በበታችነት ለሚማስነው ዝክንትል ህሊና፣ ድሪቶ ልብ ሁሉ።
እና ጠቅላዩ ብቅ ብለው የሸመቁትን ሸምቀቆ በሌላ በርዥን ይዘው ብቅ ብለዋል። ከሁሉ በላይ ግን ፈጣሪን ረስተዋል። ቅፅበት ታሪክን ይለውጣል።
ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ከፈጣሪ ቀን ጋር ሲገናኝ ያለው ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል። እንዲያውም ድሮ ዕውር ነበርን። ዛሬ ግን ኢትዮጵያን በሙሉ አቅም ሊመሩ የሚችሉ ብጡሎች እንዳሉን እያስተዋልን ነው።
ገዳይነት እና ክህደት ዱላው የራስ ህሊና ችሎት ነው። አቅሙ ካላቸው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ይቀጥሉት ጭካኔያቸውን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
እናስተውል።
ከግርግር የፖለቲካ ዕሳቤ እራሳችን እንታደግ።
እንጠንክር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ