የጃዋራዊው መንገድ 2019

 ይህን መረጃ ከልቤ ሆኜ መፈተሽ ፈልግሁኝ። ሦስት ሰዎች ለእጩ ምከ ከንቲባነት እንደቀረቡ። ሁሎቹም ኦነግ/ኦዴፓ ናቸው። ነገር ግን የኃይል አሰላለፋ ከኖቤል በፊት እና በኋላ ተብሎ መታዬት ይኖርበታል ባይ ነኝ። ከኖቤል ሽልማት በፊት ቲም ለማ፣ ቲም ጃዋር፣ ቲም አብይ ነበሩ። ቲም አብይ አማራን በመጫን ብቻ ያተኮረ ተግባር ነበረው። ብዙም በወጣበት ድርጅት ሚና ያልነበረው፣ ተፅዕኖ ማሳረፍ የማይችል። ሌላው ቲም ለማ ኦሮምያን ማዕከል አድርጎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦሮሞን የበላይነት ማስጠበቅ ላይ መሠረት ያለው ተግባር ሲከውን የቆዬ ጉልበታም መንፈስ የነበረው ነበር፣ ቲም ጃዋር ደግሞ ለኦሮሞ ፖለቲካ ልዕልና የሌሎቹን ሰላም በማወክ ለቲም ለማ አቅም ለፌድራል መንግሥቱ ምጥ ሲጥድ የባጀ ነው። በሌላ በኩል በጠሚር አብይ ሹመት ማግሥት ከቢቢኤን ጋር በነበረው ቆይታ የዶር አብይ ሰብዕና ስላቁን ለማሳካት ጅዋጅዊት እያጫወተ አይሆኑ አድርጎ ሰብዕናቸውን ውልቅልቁን አውጥቶታል። ቀድመን የሞገትንላቸው ሰዎች በልፍስፍሱ አቅማቸው ከውስጣችን ፍቀናቸዋል። ይህን የጃዋራዊው መንገድ አንድም ቀን አቶ ለማ መገርሳ ሲኮንኑት ተደምጠው አያውቁም። ሁሎቹም የሚመሳሰሉበት በፀረ አማራ ፍልስፍናቸው እና የኦሮሞን ተጠቃሚነት በሚመለከት ብቻ ነው። የኢትዮጵያ መዋለ መንፈስ እንዲውል የሚፈለገውም ለጋራ ግባቸው ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ በማድረግ ተልዕኮ ነው። አሁን ቲም ለማ ቲም አብይን ይቅርታ የጠዬቀበት ሁኔታ እዬታዬ ነው። የትናንቱ የኦዳ ዛፍ ሃብል እና የጥቅምት ሁለቱ የድጋፍ ሰልፍ የምህረት ጥዬቃ ብቻ ሳይሆን የኃይል አሰላለፋ መቀዬሩን ይነግረናል። ለዚህ ነው ዛሬ ቲም ለማ እና ቲም አብይ አብረው እንደ ነበሩ እዬተተረከልን ያለው። የቲም ለማ ሰብዕና አዲስ ግንባታ እዬተደመጠ የሚገኜው። ቲም ለማ ከስሜን አሜሪካው ጉዞ በኋላ ከቲም ጃዋር ጋር በአኃቲ ልቦና ተናቦ ሲሰራ የነበረ ነው። ቲም አብይ ደግሞ ኢንስቱሩሜንት። ቲም ለማ ስል እዛው ድርጅታቸው ኦዴፓ ሥር ያለውን የአቶ ለማ መገርሳ ቡድን ማለቴ ነው። አመቱን ሙሉ ጠሚሩ ድርጅታቸውን የመሰብሰብ አቅም አልነበራቸውም። ተንሳፋፊ ነበሩ። እሳቸው የሚፈለጉት ጡንቻ እንዲያቀርቡ ብቻ ነው። ከውጭ መንግሥታት ጋር በአገር ውስጥም በውጭም ከለማ መንፈስ ውጪ ምንም ዓይነት ጉዞ ማድረግ አይችሉም ነበር። እግት ነበሩ። አሁን ዕድሜ ለኢትዮጵያ ለኖቤል አብቅታለች። ኮራ ደልደል ብለው የኦዴፓን ዬድርጅታቸውን ምክር ቤትም ሆነ ሥ/አ/ ኮሜቴ አዳማ ላይ መሰብሰብ ይችላሉ። ምህረት ጠያቂዎቻቸውንም ጊዜ እዬጠበቁ በሚከተሉት የሥልጣን ተቀናቃኝ ፍልስፍና በሬ ሆይ ጊዜው እዬተጠበቀ ይከወናል። መነሻዬ አቶ ካሳሁን ጎፌ ናቸው። በዘመነ ለማወጃዋር የተገፋ ነበሩ። ፊት የተነሱ ቢሆኑም ጥቃት ያልደረሰባቸው ግን የኦሮሞ ደም ስላላቸው ብቻ ነው። ነገር ግን ከኦሮሞ ሊሂቃን ገና ከመነሻው ስለ ዶር አብይ በጎ እሳቤ የነበራቸው ናቸው አቶ ካሳሁን ጎፌ የመሰከሩም። ስለሆነም አቶ ካሳሁን ጎፌ የፕሬስ ሰክሬታርያት መሆን ሲችሉ ወደ ሌላ ቦታ ተመደቡ። እኔ በወቅቱ አውግዤ ሞግቼ ነበር። የዛሬን ባላውቅም ከኦሮሞ ሊሂቃን ረፕ ምህረቱ ሻንቆ እና አቶ ካሳሁን ጎፌ የራሳቸውን ዞግ ቢያቀርቡም ሰውኛ ጠረን ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ አቅምም አላቸው። ነገር ግን አቶ ካሳሁን እያሉ ለጠሚሩ ፕሴ ጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተሾሙ። ሰውዬው ጠሚሩ በሥማቸው ለመጥራት የሚፀየፋ ሆነው ግን ተሾሙ። እኛም ጉዲ ሰዲ አልን። አሁን ደግሞ አቶ ካሳሁን ጎፌ ለምክትል ከንቲባነት እጩ ሆነው ቀርበዋል እዬተባለ ነው። ቲም አብይ በኖቤል ሽልማት ምክንያት የኦዴፓን ገዢ መሬት ስለተቆጣጠረ ዕድሉ ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁ። ጠሚር አብይ አህመድ የካዷት ኢትዮጵያ ግዛታቸውን በድጋሚ አረጋግጥላቸው አለች። ሲቀናቀኗቸው የነበሯቸውን ሊሂቃን አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ በመዳፋቸው ሥር አድርጋላቸው አለች ልዕልት ኢትዮጵያ። አብረው ነበሩ እያላችሁ የምትሉት ግን የአቶ ለማ መገርሳ ፕሮፖጋንዲስት ከመሆን በስተቀር የፖለቲካ ፍልስፍናው ፍሬነገር የለውም። ጠሚሩ ሥልጣን አምላኪ ስለሆኑ የተሰጣቸውን አጀንዳ ከመፈፀም ውጪ አቅም አልነበራቸውም። ጠሚሩ አቶ ለማ መገርሳ ናቸው የነበሩት፣ በሥውር አቶ አባ ዱላ ገመዳም አሉበት። ለመሆኑ የሰኔ 16ቱን፣ ሆነ የአውሮፕላን ውስጥ የመጠጥ ብክለት በማን ተከናወነ? ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ የጠሚሩ ተግባር አቅማቸው አማራን ማስገበር ብቻ ነበር። አማራን ማጨድ እና ለሞጋሳ ሥርዐት ህዝብን ማማለል። በዚህም ለማወጃዋር አማራ አንቅሮ እንዲተፋቸው የማድረግ ፕሮጀክታቸውን አሳክተዋል። አሁን ባለው የኃይል አሰላለፍ የለማው ኦዴፓ ምህረት ጠይቆ ከአብይ ጋር ስለሆነ የጃዋር ኦዴፓ ከለማው ኦዴፓ ጋር ይፋታል ማለት ነው። ወደፊትም በተናጠል የጃዋር ኦዴፓ እዬተመታ የመሄድ ዕጣ ይገጥመዋል የጀርባ አጥንቱ የለማ ኦዴፓ ስለከዳው። ስለዚህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከፕሬስ ሰክሬታርያቱ ጀምሮ አዲስ የኃይል አሰላለፍ ይኖራል። ልንዘናጋባት የማይገባው ጉዳይ ግን ለማ ለማ ነው የናዚ ፍልስፍና አራማጅ አብይም አብይ የበሬ ሆይ እሳሩን አይተህ ፖለቲካ አራማጅ። በዚህ መሃል ከቀረቡት ሦስት እጩዎች ካልተለወጡ አቶ ካሳሁን ጎፌ ከሆኑ አንፃራዊ የፖለቲካ ስክነት አዲስ አበባ ላይ ይኖራል ብዬ አስባለሁ። ለሳቸው ያለኝ አክብሮትም እስካሁን አልተቀነሰም፣ ገዳም ገብተው ስለነበር። በነበረው አቅማቸው፣ ሰውኛ ሰብዕናቸው አቶ ካሳሁን ጎፌ ይመጥናሉ ባይ ነኝ። ወሮ አዳነች አቤቤ መጀመሪያ ከእናትነት ፀጋቸው ጋር ይታረቁ። ራሱ መንፈሳቸው ሲኦል ስለሆነ ፌድራል ላይ ለእኔ አይመጥኑም። በሌላ በኩል የአቶ ታከለ ኡማ ከሥልጣን መነሳት ለእኔ ሳቢያ ሳይሆን ምክንያታዊ ነው። በኖቤል ሽልማት ምክንያት ያፈነገጠው የጃዋርም፣ የለማም ኦዴፓ ሙት መሬት ላይ ስላለ። ጠሚር አብይ ኦዴፓን የመሩት ለ100 ቀናት ብቻ ነበር። ከዚህ ላይ ላነሳ የምሻው ጉዳይ ለአዲስ አበባ ኦዴፓ ብቻ ለሚሉ እርክክቡ ተፈፅሟል። የእኛ ናት ብለው አውጀዋል። ይሄው ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።