ኦዳ እና አዲሱ የኦነግ ኦዴፓ የኃይል አሰላለፍ። 2019

ኦዳ እና አዲሱ የኦነግ ኦዴፓ የኃይል አሰላለፍ። ኦዳን ይሳለሙ ዘንድ ጠሚር አብይ አህመድ ቲም ጃዋርን የካደው የኦነግ ኦዴፓ የለሜ ቲም ምህረት ጠይቋል። ኦዳ ለአማላጅነት ቀርቧል። የራበው ልጅ ጡት ሲያጎርሱት እንደሚፍለቀለው በልጃዊ ባህሪ የሚታወቁት ጠቅሚር አብይ አህመድ ኦዳን ትኩር ብለው እያዩ ተፍለቅልቀዋል። ሌሎችም ክልሎች ድርጅታዊ ሥራ ተስጥቶ ይህን ይከውናሉ ብዬ አስባለሁ። ትግራይን አይጨምርም። የሚገርመው በጠቅሚሩ የሥልጣን ሹመት አፍንጫኽን ያሉት የኦሮምያ ከተሞች በፌስታል ፖለቲካ አራማጁ በአቶ አዲሱ አረጋ አሰተባባሪነት የኖቤል የድጋፍ ሰልፍ እጣ ነፍሳቸውን ወጥተዋል። ይህ የፖለቲካ ቁማር ትልቅ ፍሬ ነገር ይነግረናል። ከአምስት ተተርትሮ የነበረው ኦዴፓ ወደ አንድ ማጋደሉን። ኦዴፓ ውስጥ፣ የጃልማሮዊ፣ በቀላውያን፣ ጃዋርውያን፣ ለማውያን፣ አብያውያን፣ ዳውዳውያን ነበሩ። ግባቸው ኦሮሞን የአፍሪካ ገዢ አድርጎ ማውጣት ቢሆንም የቴክኒክ ጉዟቸው ግን ዥንጉርጉር ነበር። ይህም በመሆኑ ኦሮምያ ከፌድራሉ አፈንግጦ በራሱ ጊዜ ሉዕላዊ መንግሥት ሆኖ ቆይቷል። ኢትዮጵያም በዚህ የታበዬ መንፈስ ስትቀጠቀጥ ለ15 ወራት ባጅታለች። ኦነጋውያኑ፣ የኦሮሞ ሊሂቃን የጠሏት ኢትዮጵያ የኖቤል ተሸላሚ አድርጋለች። ለዚህም ነው ሥርጉትሻ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስተምህሮ የነበራት። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ነው በማለት ኢትዮጵያን ስትዘክር የኖረችው። የሆነ ሆኖ እጅ የሰጠው የለማ ኦዴፓ ቡድን የጃዋር ቡድን ከድቶ ኦዳን በወርቅ አሰርቶ ምህረት ጥዬቃ ላይ መሆኑን አይተናል። የሚገርመው የኦነግ ኦዴፓ ቲም ለማ ጃዋርን መክዳቱን በፕሮፖጋንዳ ግርዶሽ ለመከለል መሞከሩ ኢትዮጵያ ማስተዋል ያላቸው ልጆች የሏትም የማለት ቧልት ነው ለእኔ። የጃዋር ቲም ለለማ ቲም እስትንፋሱ ነበር። የለማ ቲምም ለጃዋር የቀውስ ውርዴ ሆኑ የጠሚሩ ሰብዕና ዕርቃን በማስቀረት ህሊናው ነበር። የሁለቱ ጥምረት የጠሚሩ የተቀባይነት አቅም መለመውን እንዲቆም የተሳካ የፖለቲካ ትርፍ ተገኝቶበታል። አቶ ለማ መገርሳ በጠሚሩ ገደብ ያልነበረው ተቀባይነት አልቀኑም ማለት አይቻልም። ይህም ሰውኛ ነው። ጃዋርውያኑ ደግሞ ከሳት የገባ ፕላስቲክ ነበሩ በጤነኛው የ100 ቀን ጉዞ። በሌላ በኩል ጠሚሩ የዋጡትን ውጠው ሰብዕናቸውን እንዳሻው ሸቅጠው እና መቅጠው የጃዋርወለማ ፍላጎት ሲያስፈፅሙ ባጅተዋል። የኦነግንም እንዲሁ። እንደ አክቲቢስትም እንደካድሬም ሲያደርጋቸው ባጅቷል። ኢትዮጵያን ከድተዋታል። መታመን ቃሬዛ ሸልመውታል። አማራን ሊሂቃኑን በመጨፍጨፍ፣ በማሰር፣ በማሳደድ በዐለም እንዲወገዝ በማድረግ፣ ብሄራዊ ሰንደቃችን ክብሩ እንዲጣስ በማድረግ፣ የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ስላከበረች ስትነድ ስትንገላታ ፍፁም ተባባሪ በመሆን ዘመንም ትውልድም የማይረሳው በደል ፈፅመዋል። የአዲስ አበባ ህፃናት በፅንሳቸው የመከራ ቀንበር እንዲጫናቸው፣ መኖርን እንዳይናፍቁት ረቂቅ ዲስክሪምኔሽን ተከናውኗል፣ የኢትዮጵያ ተምሳሌት የነበረውን ደቡብን በትነዋል። ለማን ሲባል? ለሥልጣናቸው ሲባል የቲም ለማን ፍላጎት ቀጥ ብለው ሲፈፅሙ ባጅተዋል። አሁን በአደባባይ የከዱት ኢትዮጵያዊነት አዲስ ዕድል ሰጥቷቸዋል። የኖቤል ተሸላሚ ሆነዋል። ይህም በመሆኑ በአቅም፣ በክህሎትም የሚመጥኗቸውን አቶ ለማ መገርሳ ፈንጋጭ መንፈስ አንበርኮኮላቸዋ። በፅኑ የሚፀዬፋቸውን የጃዋርዊውን መንፈስም ተግ ያደርግላቸዋል ብዬ አስባለሁ። ስለሆነም ቀጣዩ የኦነግ ኦዴፓ የኃይል አሰላለፋ ይቀዬራል።



 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።