ምዕራፍ ፲፩
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
፲ን የአብይዝም ለያዥ ለገራጅ ያስቸገረውን ዬ፭ ዓመታት ውጥንቅጥ የአገዛዝ ገፀ ባህሬ አስተውለን አሁን ወደ ፲፩ኛው ዛሬ እንሸጋገራለን። "ቂጥ ገሊቦ ራስ ተከናኒቦ" ስለሆነው የፋንታዚው ልዑል የጠሚ አብይ አህመድ ውቂ ደብልቂ እና ረግረግ።
1) የኢትዮጵያ፤
2) የስሜን ኢትዮጵያ፤
3) የአፍሪካ ቀንድ፤
4) የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ፤
5) የአህጉራችን የአፍሪካ የችግር ምንጭ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እና ፈንታዚያቸው ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ በልዕልና ልቅና ዬነበራትን የተፈሪነት፤ የከበሬታ፤ የግርማ ሞገስ ማህባ ቦታ አውርደው የጣሉበትን ቦታ ውስጣችን እዬቆሰለ እዬታዘብን ነው። በሁሉም ዘርፍ ዛሬ ኢትዮጵያ ከደረጃ በታች ናት። ከትንሿ ከጁቡቲ እንኳን ጋር ስትነጣጠር። የሆነ ሆኖ የአህጉሩ አብሪ ኮከብ እሆናለሁ #አንጋጠው ልፍጭ ብለው ባይፍጨረጨሩ እንደ ተለመደው ባይሰሙም እንመክራለን። አይዘብዝቡ። አይዝረክረኩ። ሁሉን ነስቷቸው ሁሉን የሚፈልጉ መሪ መሆናቸው ደግሞ ይገርመኛል።
ቅኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ከወፈፌ ጋር መወፈፍ ልማድህ አይደለም እና አደብህን ጠጥተህ፤ በተደሞ ተከውነህ ምክክርህን ከፈጣሪህ ከአላህ ጋር ብቻ አድርግ አደራ። እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነውና ጨዋነትህን የሚመጥን ትጉህ፤ አዛኝ፤ አጽናኝ የአይዟችሁ ሙሴያዊ መሪ ይሰጥኃል። ጠብቀው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/10/2023
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅር ሲያልቅም ትዕግሥት ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ