መታቆር። oct 17.2020
መታቆር።
ህወሃት ሥልጣኑን ከለቀቀ ጀምሮ አቅም አባክኛ አላውቅም። ታግዬዋለሁ። ከሥልጣኑ ወርዷል። አሁን መታገል ያለብኝ ሰውን እዬገደለ ስለሰው አቀድኩ የሚለውን የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ነው።
ዛሬ ግን ባዬሁት የሁለትተኩል ዓመታት ትዝብቴ ግርም የሚለኝን ላነሳ ወደድኩኝ። ህሊናቸው ውስጥ የታቆረ ዕምቅ ድንብልብል መከራ አለና። የተነሱበት ፀረ አማራ፣ ፀረ ተዋህዶ ነው።
የሚገረመው ነገር ከሚዲያ አዘጋጆቻቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዛሬም ህወሃት ሲመሰረት ከነበረው ዕሳቤያቸው አንዲት ስትዝር ፈቅ የለም። እርግማን።
ሌላው ቀርቶ ምዕቱ 21 ኛው ክ/ ዘመን ሥልጣኔውም ዲጂታል መሆኑን የሉበትም። አንድም የህወሃት ፖለቲከኛ የወደቀበትን እንኩሮ ሃሳብ ኮንኖ ለመዳን ሲተጋ አይታይም።
የሰው ልጅ የወደቀበትን መንገድ እንደምን መዳኛው አድርጎ ያመልከዋል? የተገለበጠ ጉድ። ያሉበት ቦታ የክብር ነውን? የሥነ - ልቦና ቀውስ የለባቸውምን?
አማራ እኮ ነው ደግፎ ያስገባቸው፣ ያኖራቸውም የግርባው ብአዴን ሙሉ ድጋፍ ነው። የጣላቸውም የዚህን ድምፅ ማጣታቸው ነው። ማንም ይሁን ማንም የአማራ ድጋፍ ከሌለው ገዢ የመሆን ተስፋው ቅዥት ነው።
አሁንም አገር ለመምራት ያስባሉ ህወሃቶች። ግን በፀረ አማራ ኃይሎች ስብስብ የበላይነት። አይሰቡት። አይዳክሩም። አይደለም እነሱ ኦህዴድ ቀፎውን ነው ያሉት።
ኦህዴድም ፀረ አማራ ኃይሎችን ክበቡኝ ብሎ ሲመክር፣ ሲዘክር ባጄ፣ የምድር እንቧዩን ብአዴንን በሞጋሳ ጥምቀት አስምጦ እንደ ደመቅን እንቀጥላለን ብሎም አሰበ። 50/60 ወጥቷል ትልሙ። አይደለም ለዛን ጊዜ አሁንም ያለው በቀውሱ የኦፕሬሽን ትንፋሽ ነው። በፋቲክ።
ህወሃት ከራሱም ውድቀት መማር አልቻለም። ከኦህዴድ ከሄሮ ወደ ዜሮ መ
ማቆልቆሉም አያስተምራቸውም። ይህ ሁሉ ህዝብ እዬተፈናቀለ፣ እዬታረደ ጉዳያቸው አይደለም። ከአንጀታቸው ጠብ አይልም ሃዘኑ። ስለ ኢትዮጵያም አያስቡም።
አገረ የሚባለው ለእነሱ ድንጋዩ ይሆን? ብጣቂ ሰብዕና እንዴት ይጠፋል? በዚህ ልሙጥነት በቀደመው የጭካኔ፣ የዘረፋ ክርፋት እንደምን ህዝብ ይቅር ብሎን ዕድሉን ይሰጠናል ተብሎ ይታሰባል?
ማንም ይሁን ማንም ካለ አማራ ሙሉ የመንፈስ ድጋፍ ቆሞም አያውቅም። ወደፊትም አይቆምም።
በሌላ በኩል ግን የአማራ ልጅ የሚገነባው ሰብዕናም፣ የሚያደራጀው ተቋምም የሌላ ሲሳይ ነው። ስለ እራሱ ቋሚ አጀንዳ የሌለው ማህበረሰብ ቢኖር አማራ ብቻ ነው።
የሆነ ሆኖ ፀፀትም፣ ይሉኝታም ያልሰራለት ህወኃት የተከለውን እሾህ ነቅዬ እኔ እጠቀልላሁ ሃሳቡን ጋራጅ ለቆ እሱ የህሊና ቡርሽ ቤት ይግባ። ትናንት ዛሬ አይደለም። ነገም ዛሬ ሊሆን አይችልም።
አንድ ተቋም ወይንም ድርጅት የወደቀበትን፣ የከሰረበትን፣ ተዋርዶ እንኩትኩት ያለበትን መንገድ እንደምን የሙጥኝ ይላል?
ጭካኔውም አረመኔነቱም እራሱን ጣለው። ያን ተሸክሞ ዛሬም መሪ ድርጅት እሆናለሁ ብሎ ማሰብ ጅልነት ብቻ ሳይሆን እብደትም ነው።
የሰው ልጅ ሰውን ማዕከል አድርጎ የተነሳበትን፣ የወደቀበትን አመክንዮ፣ ማህበራዊ ንቃተ ህሊናውን ገምግሞ መዳኛውን መቀዬስ ሲገባ ውሃ ወቀጣ።
የተተከለ ድንጋይ ሆነው ቁጭ አሉ። አማራን በቅንነት፣ በተቆርቋሪነት፣ በቤተሰብነት ማንሳት ጣራቸው ነው ለህወሃቶችም ለኦህዴዶችም። የበደሉት በደል፣ የሠሩት ግፍ አይፀፅታቸውም። አይጎረብጣቸውም። አለመታደል።
የሰውነት ጠረን ሳይኖር ሰውን የመምራት አማራጭነት አይገኝም። ልብ ይስጣችሁ። ለነገሩ ፀረ አማራነት እና ፀረ ኦርቶዶክስነት ከተነሳ ህወሃትም ኦህዴድም ኦነግም ህልውናችሁ ያከትማል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
… ፈጣሪ ሆይ ሰውኛ ጠረን ያለው መሪ ስጠን። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ