እናታዊነት በቅንነት ለውስጥነት።

 

እናታዊነት በቅንነት ለውስጥነት።
• ለኩላሊት ድክመት ትንሽ ብልስ።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሐር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
ጠብታ።
 
 No photo description available.
 
 
 
 
ባለፈው ሳምንት ስለ ኩላሊት ጠጠር ትንሽዬ አቅጣጫ ጠቁሜ ነበር። ምን ያህል እንዳዳመጣችሁት አላውቅም። ምን ያህል ሼር እንዳደረጋችሁት አላውቅም። ድውያኑ ማህበረ ግንቦታውያን ያው መኖራቸው ቀብር ስለሆነ ይህንንም ይገድቡት ያቅቡት ይሆናል። የሆነ ሆኖ መከታተላችሁን እያዬሁኝ ሚዛኑ ይለካል።
በጣም የሚገርመኝ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ሰው መሆን የተሳነው ህዝብ ብዛቱ እጅግ ይገረምኛል። በቃ ልቡን አውልቆ፤ ህሊናውን አውልቆ እራሱን ተውሶ በውራጅ ማንነት የሚኖረው ህዝብ ብዛት ግርም ይለኛል። በራሱ የሚቆም የለም። እራሱን ሆኖ ተፈጥሮ ጨርቅ ቀዶ አልብሶ፤ መሃያ ከፍሎ ያላስተዳደረው ነፍስ እንዳሻው ይነዳዋል። ይገርመኛል።
አቁም ሲል ያቆማል፤ ሂድ ሲል ይሄዳል። አድርግ ሲል ያደርጋል። አታድርግ ሲል አያደርግም። ሰው ራሱን ፈርቶ ከኖረ፤ ሰው እራሱን ወርጆ ከኖረ አልተፈጠረም ከምል አልተጸነሰም። ያልተጸነሰ ደግሞ ምንም ነው። {}
• ኩላሊት ስለምን ይደክማል።
• ሃኪም አይደለሁም። ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁኝ የባይወሎጂ እና የኬሚስተሪ ተማሪ ነኝ። አነባለሁኝም። እኔ እንደማስበው ግን የኩላሊት ድክመት ከሚያመጡ ውስጥ።
(1) ኢንፌክሽን ወይንም ከዛ ጋር የተያያዙ በሽታወች ይመስሉኛል። በዚህ ዘርፍ ከቢቢሲ የ አማርኛው ክፍል እንዳነበብኩት ከሆነ ሽታ ያላቸውን ሳሙና ነክ ነገሮችን ለመታጠቢያ ነገር መጠቀም ለኢንፌክሽን እንደሚያጋልጥ አንብቢያለሁኝ።
(2) ከዘር የሚተላላፍ ይህ ዕውነት የሆነ ነገር ነው።
(3) የፉኛ ማነስ ይህም ዕውነት። አንዳንድ ኦርጋኖች ሲፈጠሩ አንሰው ይፈጠራሉ። ለምሳሌ ልብ። እና ፉኛ ትንሽ ከሆነ በኩላሊት ላይ ጫና ይፈጥራል። ልብ ካነሰ ደግሞ የልብ ትርታ ፈጣን ሊሆን ይችላል።
(4) ውሃ በብዛት አለመጠጣት።
ይህ የሥርጉትሻ ለምን ጥያቄ እንጂ ተምራ ተመራምራ ያገኜችው አይደለም። የስሜን ጎንደር ልጅ የኢትዮጵያን ግማድ ተሸክመን በዬት አልፈን እንማረዋለን። እንዲህ ተዳፍነን አገር ስንል ይኸው ተቀብሮ መኖር።
የሆነ ሆኖ የአብሽ ሻይ ይረዳል። ስኳር የሌለው©የአብሽ ሻይ ኩላሊትን ያጠራል።
እንደ ገናም ተፈጥሯወ ዲያሊስስ ይሰራል። ሞክሬሩት። እኔ ሰነፍ ነኝ።
ይህ መጫር ሳለ ራሴን እማስታውስበት ጊዜ የለኝም። ቀድሞ ነገር ከልጅነት እሰከ ዕወቅት እኔ አጀንዳው ሆኜ አላውቅም። አሁን ልብ የምገዛ ይመሰለኛል። ያ የመሰከርኩለት ህዝብ ሁሉ እንዲህ ውሃ የበላው ቅል ሲሆን። አሁንም ጥረት የማደርግለት ነፍስ ማድመት ከተሳነው። በቃ ማረፍ አማራጭ ነው።
እኔ ሳርፍ እህቶቼ ቢያንስ ስለ እኔ ማሰብ አቁመው የራሳቸውን ኑሮ መጀመር ይችላሉ። እነሱንም ሰላማቸውን አውኬያቸዋለሁኝ። በዕድሚያቸው ኃላፊነት ሳይሰማኝ ኑሪያለሁኝ። ፍቅር ነፍጌያቸዋለሁኝ። አትኩሮት ነስቻቸዋለሁኝ። እንዲህ ፈሶ ለሚቀር ተጋድሎ።
ለዛውም በገባሁ በወጣሁ ቁጥር በሰራሁ በደከምኩ ቁጥር በተነፈስ ቁጥር ሰብሌን ይዘርፋሉ ሥሜን ያጠቁራሉ። ሥሜን ይታገላሉ። ዘመነ ጥቁር ቀኖች። የዘመን ቀንበሮች።
ግንቦት 7 የሚባል ድርጅት ወደ ትቢያ የተቀዬረ ዕለት ያን ጊዜ የኢትዮጵያ ልጆች አቅም ዳግሚያ ትንሳኤ፤ ዳግሚያ መወለድ ይሆናል። እነሱ እያሉ ግን ኢትዮጵያ ማድያት እንደዋጣት ትቀጥላለች። ማፍረስ፤ መንቀል፤ ማጠንዘል፤ ማወዬብ፤ መሰንጠቅ፤ መተርተር። ማጠውለግ። ማወክ። ቤርሙዳ ትርያንግል።
በሉ ከኬሚስትሪ ውጤት ጋር ከምትላፉ አገር ቤት በኪሎ አስመጥታችሁ የ አብሽ ሻይ እያፈላችሁ ኮምኩሙ። ከዛ ውጤቱን ታያላችሁ። ይህን ዝግጅት እምቀጥለው። ምን ያህል ሼር እንዳደረጋችሁ ከዬሁኝ በኋላ ነው። በስተቀር አቆመዋለሁኝ። የነፃ ነገር ከ እንግዲህ ለማንም አይሰጥም። በፖለቲካውም ዘርፍ እንዲሁ። ዝም ነው። በቃ ዝም ብሎ ማዬት ማድመጥ።
አቤቱ አብይዝም ስለ ጠሎት እኔ ስናገር አንድ ቀን የካቢኔ ምደባውን አራዝሞ ሩጫ ሆኖ የጠሎት ቀን ለማወጅ። ተዋህዶ ተገለለች። ሁለት ብጽዓን ፓትርያርክ የት አሉ ብዬ ጠዬቅኩኝ። ትቅማጥ እንደያዘው ሰው ሩጫ ሆነ። ማንም ይህችን ያዬ ያስተዋለ የለም።
ከዛ ወንድም ታሜ ነገሬ መጣ እና ጠሎት ለ አዲሱ መንግሥት ተደረገለት ብሎ ነገረን፤ ትናንት ደግሞ የግብርና ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለሙኝ ሲል ነበር።
የሆነ ሆኖ ማፈሰስ ከእንግዲህ የለም። ማገናዘቢያወችን እያቀረቡ ማሳዬቱ ግን ይቀጥላል። ትናንት ምን ዛሬ ምን? በህሊናው የሚኖር ሰው ነው አማላካችን ሰው አድርጎ የፈጠረው። ሰው ነኝ ካልክ እንደተፈጠርክበት አሻራ ሰው እንጂ ሐረግ አትሁን፤ ዝልፍልፍ አትበል።
ለፈለጋችሁ የ14.10.2021 ግሎባል፤ ፓን አፍሪካዊው የጸጋዬ ራዲዮ መሰናዶ ይህን ይመሰል ነበር። ላይፍ ላይ ያልተከታተላችሁ።
"Ethiopia is the Mother of Africa's Independence." (Excellency, Uhuru Kenyatta President of Kenya) ያለውን ሥርዓት መታገል ማለት እናትን መታገል ማለት አይደለም። ይህ ሊታወቅ ይገባል። እናት አገር የመፈጠር ሚስጢር ናት። ለዛውም ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያ የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ቀጥሮ የሚያስተዳድራት ረዱ አገር አይደለችም። በጣም ይዳፈሯታል።
እሱ ከመፈጠሩ ሺህ ዘመን በፊት የነበረች አገር ናት። የሆነ ሆኖ የዘመናችን ታላቁ ንግግር የኬኒያው ፕሬዚዳነት ትንግርት አለበት። ታደሙበት። የሴኒጋሉም ፕሬዚዳንት በፈረንሳይኛ አዲስ አበባ የአፍሪካ ዋና ከተማ ይሏችኋል። ሲዊዝ አንዱ ቋንቋዋ ፈነንሳኛም ነው። የኦነግን አከርካሪ እንኩቶ አድርገውልኛል።
„አፍሪካ ለአፍሪካውያን“ የጃንሆይ ቅኔም በተክሊል ተቃኝቶበታል። ሳቢ ማራኪ ቀን ነበር። ቅዱስ ጥሩ ቀን ነበር። ልደትም ትንሳኤም። ተመስገን። መኖር ይህን ይሰጣል። ተመሰግን። ያን ሁሉ የግንቦት 7 አቧራዊ ወጀብ ብቻውን ያሳለፈ የጸጋዬ ራዲዮ ከዚህ ደረሰ። ተመሰገን። የዓለም ድምጽ በአኃቲ ተሰተናገደበት። ይደንቃል።
መልካም ሰንበት። የእኔ አሜኖች ቅኖቹ እባካችሁ እምጽፈውን አንብቡ።
• ፎቶው ያለሁበት ከተማ ቪንተርቱር የኢንተግሬሽን ቤተመጻህፍቱን 10ኛ ዓመቱን ሲያከብር ጋብዞኝ 5 ዝግጅት ነበረኝ። አንዱ ነው ይህ። በዕለቱ የረዳኛን ኤርትራዊን ቅኑን ወንድሜን አመሰግናለሁኝ።
ጤና ይቅደም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17.10.2021


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።