ቅኔው ጎጃም የትህትናው ውሃ ልክ በትሁቱ ሃብታሙ ይሄነው መስፈር ይቻላል። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።" ሃብትሽን የመሰለ ወጣት ማዬቴን እግዚአብሄርን አመሰግንኃለሁ ብል የተገባ ነው። እኔ የሚጨንቀኝ የትውልዱ ጉዳይ ነው። ዓለም እራሷ ታስፈራኛለች። ምክንያቴ አሉታዊ ነገሮች ጉልበት ስለሚያገኙ። የሆነ ሆኖ ሃብትሽ የጋራጅ ሰራተኛ ነው። እንደ ዋዛ ፋና ላምሮት ተወዳደረ። እናማ አራተኛ ወጥቶ ተሸለመ። አሁን ፋና ላምሮት የ፲፫ኛ፦ ዬ ፲፬ኛ፦ የ ፲፭ኛ ዙር አሸናፊወችን እና በዩዙሩ ብቃት አሳይተው ግን በዕለት ፐርፎርማንስ ዕድል ያልቀናቸውን አክሎ ለአሸናፊወች አሸናፊ እያወዳደረ ነው። እኔ ከቀን አንድ ጀምሮ ሃብትሽን ሳዬው ትህትናው መሰጠኝ። ስለሆነም ተግቼ እከታተለዋለሁኝ። ዕውነት ለመናገር መከታተል ከጀመርኩ ጀምሮ በማያቸው ተወዳዳሪወች የሙዚቃ ብቃት ሳይሆን በሰብዕና ውቅራቸው ላይ በአትኩሮት እከታተላለሁኝ። እናም እረካለሁኝ። አሁን የዙር ፲፭ አሸናፊ ሄኖክ ብርሃኑ እርጋታው ይመስጠኛል። ፋክት ፈላጊነቱም ይደንቀኛል። መሰናዶው ፋክት ፍለጋ ላይ ነውና። የወደፊት የፋክት ሙዚቀኛ መሠረት ጣይም ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ዛሬ እምጽፈው ስለ ሃብትሽ ምክንያቴ በወጣት ጉዳይ ላይ ማስታወቂያ የሚሠሩ፤ በፊልም ፕሮዳክሽን ውስጥ የምስጉን ወጣት ካራክተር ላላቸው ወገኖቼ ሃብትሽ ትክክለኛ ወጣት መሆኑን ዘለግ አድርጌ በትሁት መንፈስ ለማሳሰብ ነው። ቅኔው ጎጃም ሁሉንም የሰጠው ነውና ለትህትናም ይህን የመሰለ ብሩህ ተስፋ ወጣትንም ያፈራል። መመካት ተገቢ ባይሆንም ተስፋዬ ግን ፋፍቷል። ይህ ወጣት እኔ እንደማስበው በሥራ አካባቢው፤ ለጓደኞቹም ትህትናን በገፍ እንደሚመግብ ተስፋዬ ሙሉዑ ነው። የፋ...