ልጥፎች

ስትል

  ጥበብን ስፍ ብዬ የምወዳት #የልብን ስለምታናግር፤ ስለምታደፋፍርም ነው። ጥበብዬ #ስታጽናና #ከህሊናዋ ነው። #አይዞሽ ስትል እኮ ቁልምጫዋ #በገፍ #ማዕዱን አቅርባ ነው። ሥርጉትሻ 2024/06/15

#አንጎል #ድንቢጥም አላት

  #አንጎል #ድንቢጥም አላት። እኛ የምንለዬው #ህሊና ስላለን ነው። ህሊናችን ደግሞ #ለተፈጥሯዊነት እና #ለሰባዕዊነት #ብቻ ነው የተፈጠረው። #ዕብንነት መፍቀድ #አንጎል ብቻ ይኑረኝ ማለት ነው። ሥርጉትሻ2024/06/15

ሐሤቴ

  ከዘለለው ጋር #አለመዛለሌ ። ከጎረፈው ጋር #አለመጉረፌ ። ሥርጉትሻ 2024/06/15

በተከፋች

  በተከፋች አገር ውስጥ የሚያድጉ ወጣቶች ሁለመናቸውን #ተዘርፈው ያድጋሉ። ወጣትነታቸውንም ይዘረፋሉ ከሞት ከተረፋ። ይህ ማለት ለምን #ተፈጠራችሁም ነው። ሥርጉትሻ 2024/06/15

Traumhaft. ቅኒት ሆይ! እንኳን ቀናሽ። ተመስገን።

ምስል
  Traumhaft. ቅኒት ሆይ! እንኳን ቀናሽ። ተመስገን።   ሲዊዝ እና ኡንጋር ጨዋታቸውን አሁን አጠናቀቁ። የሲዊዝ እግር ኳስ ብቃት ልዩ ነበር። ሲዊዞች በመከላከል ላይ የሚያተኩሩ ጨዋታቸው ፍፁም ሰላማዊ ነበር። ዛሬ አራት ደቂቃ ላይ ነው ባለ ቢጫ ነበር የሆኑት። ጨዋታቸው በተለይ የመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አግሬሲብ ነበር። የቲም ወርኩ፤ ቅንጅቱ የተሟላ ነበር። በመከላከል ሳይሆን ማጥቃት ተኮር ነበር። ከትናንቱ የስኮትሽ እና የጀርመን የመክፈቻ ጨዋት ይልቅ ዛሬ ሞቅ ያለ ጥሩ ፋክክር ነበረው። አርቱም ሳቢ ሆኖ ነው አገኜሁት። የሲዊዝ አንከር ተጫዋች ጭምቱ እና ተወዳጁ አንድ ሚሊዮን የፌቡ ተከታይ ያለው #ሸኪራ ባይኖርም ንቁው #ሻካ ነበር። #በጠይም #ዕንቁ #ህብርነት በአዲስ አሰልጣኝ፦ በልዩ የጨዋታ ቴክኒክ ያዬሁት የቅድስት አገር የሲዊዝ ጨዋታ ለእኔ ልዩ ነበር። የተነቃቃ የውስጥ የሆነ ነበር። በጨዋታው አራት (4) ቢጫ፥ ለበርካታ ጊዜ የማዕዘን ምት ሲዊዞች አግኝተው ነበር። በነገራችን ላይ የሲዊዝ ጎል ጠባቂም #ምስጉን የተረጋጋ እና ጠንካራ ከሚባሉት ውስጥ ነው። ዛሬ። ፈጽሞ ያልጠበቅኩት የጨዋታ ትዕይንት ከሲዊዝሻ ቲም አዬሁ። ስለሆነም ቀጣይ ተስፋውን #ስሰፍረው #ቲፍ ። #ሲዊዝ 3 ለአንድ ኡንጋርን ረታለች። የሚገርመው ሦስተኛው ጎል በተስተጓጎለ የጨዋታ ጊዜ የተገኜ በተጨማሪ ጊዜ የተገኜ #ታካይ ድል ነበር። ቦነስ ይባል። ሌላው ደጋፊም የሲዊዝ በበቂ ሁኔታ መኖሩ ብቻ ሳይሆን #አትኩሮቱም ተሳትፎውም #ልዩ ነበር። አዬ ድንቡልቡልዬ ሚሊዮንን በፍቅር ልትነጂ የተፈጠርሽ። ታድለሽ! ድለቃው ፌስታሽ ኢቬንትሽ። ምሩቅ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15/06/2024 #ኳስዬ የማቱሳላን ዕድሜ!

ዶ/ር አብረሃም አመሓ ሜታ ፊዚክስ 5% Vs 95%

ምስል

Live:ሜታ ፊዚክስ ሃሳቦች ዙሪያ አቅራቢ: ዶክተር አብረሃም አምሃ

ምስል

በስደት ተሳትፎዬ በፎቶ የተደገፈ ፌቡ ላይ አለ ማየት ትችላላችሁ።

  Facebook https://www.facebook.com › sergute.selassie

የሞዴል፤ ሞድሬተር ዳኛ እና የአዲስ ሃሳብ አፍላቂ የልዕልት ዬሃይዲ ዓለም እና ለአዲስ ትውልድ ግንባታ ያላት ልቅና።

ምስል
  የሞዴል፤ ሞድሬተር ዳኛ እና የአዲስ ሃሳብ አፍላቂ የልዕልት ዬሃይዲ ዓለም እና ለአዲስ ትውልድ ግንባታ ያላት ልቅና። " የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፦ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱) ጤና ይስጥልኝ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁ? ደህና ናችሁ ወይ። ትናንት 19ኛ ዓመቱን ያከበረው የጀርመን ምርጥ ሞዴሎች ውድድር የመጨረሻ ቀን ነበር። ብዙ የተማርኩበት፤ ሁለቱ መፃህፍቶቼ የተፃፋበት መሠረታዊ የመነሻ ሃሳብ ትውልድን ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር፤ መክሊቱ፤ ጥሪው ሜሴጁ ሳያልፍበት በጥዋቱ እንዴት ይገነባል የሚል ፍለጋዬ ዓለም ዓቀፍ የመክሊት ውድድሮችን እንድከታተል አስችሎኛል። 1) 6ኛ መጸሐፌ "የተስፋ በር" ልጆች እና ወላጆችን፤ ልጆቻችን እና ማህበረሰቡ፤ ልጆች እና ግሎባላይዜሽን፤ ልጆች እና መምህራን የመነሻ ሃሳብ የተካተተበት ነው። 2) 7ኛ መጽሐፌ "ርግብ በር" ማህበረሰብ እና ትዳር በትውልድ ግንባታ ላይ ምን ድርሻ አላቸው? ድርሻቸውን እንዲወጡ ዕድሎች እንዴት ማኔጅ ሊደረጉ ይገባል የሚል የመነሻ ሃሳብ ነው። ሁለቱም ጀርመን አገር በታለንት፤ በሞድ፤ በሙዚቃ ውድድር ከማያቸው ክፍተቶች በአገሬ በኢትዮጵያ በማህበረሰብ አደራጅነቴ አያቸው በነበሩ ጥንካሬ እና ድክመቶች፤ እኔ አባቴ አበይ በጥዋቱ ወደ ጥበብ ያስገባኝ ሁኔታ፤ የእናቴ የእብዬ ክትትል በሞድ ዙሪያ ልምዴን ያጋራሁበትም ነው። ሌላው ቁጥቧ ሲዊዝስ በዚህ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ አክያበታለሁ። ብዙውን የተስፋ ጎዳና ዳሜጅ በሚያደርገው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ህሊናን ላለማከራዬት በወሰድኩት እርምጃ ስቶር ያሞቃሉ። እና ለእኔ የኦስትራሽ በስሱ፤ የጀርመን በጉልሁ፤ የሲዊዝ በመጠኑ በዘርፋ የሚካሄዱ ውድድሮች አቅጄ የምከታተላቸው ናቸው።...

የተፃፈው ሁሉ እየሆነ ነው || ዶ/ር አብርሃም አምሃ

ምስል
ፈቃዱ ዛሬ ነበር። ቤቴ ውስጥ የተከወነውን ልክደነው። ዊዝደም ለናፈቃችሁ የዕውቀትም የርጋታም የኔታን እንሆ። መጨረሻ ላይ አለቀስኩ። ስለእኛም ስለኢትዮጵያም። በርቀት ስለ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራም አሰብኩ። ሥርጉትሻ ደህና እደሩልኝ። ሰላም ካደርኩ ነገ አገኛችሁአለሁ። 11.06.024

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶር ዳንኤል በቀለ፦ ይድረስ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋች ክቡር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፦

ምስል
  ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶር ዳንኤል በቀለ፦ አዲስ አበባ። ይድረስ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋች ክቡር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፦ ካሉበት። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     ጉዳዩ፦ የሰማዕቱ ኢሳያስ በላይ ቤተሰቦችን እና አብረው እስረኛ ስለሆኑ ጓዶቻቸው #ቀጣይ #ሕይወት ይመለከታል። አሁን በመረጃ አቀራረብ ጥራቱ እና ቅልጥፍናውም፦ በሚዛናዊነት አቅሙም ተስፋ ከማደርግበት ሚዲያ አንዱ ኢትዮ ኒዊስ ነው። ከደማችን ጋር እንዲዋህድ በተገደድነው #ዘወትራዊ " #ሰበር " #አስደንጋጭ ዜና እንደ ተለመደው በዛሬ ኢትዮ ኒዊስ ረፋድ ዜና ደነገጥኩኝ። ሰውነቴም #ተንዘፈዘፈ ። መቀመጥ ተስኖኝ ጋደም ብዬ ነው የምጽፈው።   ሰማዕቱ ሟች አቶ እያሱ በላይ አሰቃቂ በሆነ ድብደባ እና ዘለፋ በታከለበት ሁኔታ ህይወታቸው ማለፋን የእሥር ቤት ጓዶቹ መሠከሩ ይላል ዘዬዘገባው ዕድምታ። #አስፈሪው ጉዳይ ተረኞች ሊኖሩ እንደሚችሉም #ዛቻ እንደሚደርስባቸው የእስር ጓዶቻቸው ገልፀዋል ይላል ኢትዮ ኒውስ በስደት ባለበት አገር አሁን በሰማሁት ዘገባ።   #ህም ! #አማጥኩኝ ።   1) እነኝህ ዛቻ ስንቃቸው እንዲሆን የተገደዱት እስረኞች ለቀጣይ ህይወታቸው ማን ዋስትና ይስጥ? እንዴትስ ማፍትሄ ማግኜት ይቻል ይሆን? 2) ቁጥራቸው በውል ለማይታወቀው የአማራ ህዝብ ሊቃናት እና ሊሂቃን እስረኞች በቀጣይ እንደምን ጥበቃ ሊደርግላቸው ይችል ይሆን? ስጋቴ አይሏል። 3) በሻለቃ ናሆሰናይ ጉዳይ የታሰሩት ባለፈው አጭር ዘገባ በመንግሥት የተሠራባቸው ወገኖች እና እስሩም በዚህ ዙሪያ ከቀጠለ ልቁን ጭካኔ ማን ሊገድበው ይችል ይሆን?   4) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቁ ሆነ መቀጠሉ መቼ ነው ይፋዊ መግለጫ በጠሚር አብይ ...