የbbc የአማርኛው ዘገባ። «ከ30 ዓመታት በላይ ሕይወቱን ለኪነጥበብ የሰጠው ኩራባቸው ደነቀ በወዳጆቹ እንዴት ይታወሳል?»
የbbc የአማርኛው ዘገባ። «ከ 30 ዓመታት በላይ ሕይወቱን ለኪነጥበብ የሰጠው ኩራባቸው ደነቀ በወዳጆቹ እንዴት ይታወሳል ?» https://www.bbc.com/amharic/articles/c62830d5kymo «ከ 1980 ዎቹ መጀመርያ ጀምሮ በተለያዩ ቴአትር ቤቶች በትወና እና በአዘጋጅነት ሰርቷል። በአዲስ አበባ በሚገኙት አራቱ ቴአትር ቤቶች በትወና፣ በዝግጅት፣ አንዲሁም በአመራርነት እውቀቱን አካፍሏል። የሙያ ባልደረቦቹ ኩራባቸው ከማለት ይልቅ “ ኩራ ” እያሉ መጥራትን ይመርጣሉ። ሁሉም በአንድ ቃል ለሙያው ካለው ፍቅር ባሻገር “ ጨዋታ ወዳድ፣ ወግ አዋቂ ” መሆኑንም ይመሰክራሉ። “ መካሪ፣ መንገድ መሪ ” ሲሉ የሚገልጹትም አሉ። ለሦስት አስርታት በላይ በኢትዮጵያ የኪነጥበብ አድማስ ደምቆ የኖረው ኩራባቸው ደነቀ የተወለደው በ 1957 ዓ . ም . በሐረር ነበር። ኩራባቸው የመጀመርያ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በጭሮ ከተማ ነው የተከታተለው። በ 1979 ዓ . ም . ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቴአትር ጥበባት የትምህርት ክፍል የተመረቀው ኩራባቸው፤ በ 1980 ዓ . ም . ጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር አርባ ምንጭ በጀማሪ የቴአትር ኤክስፐርትነት ተመድቦ ሥራ ጀመረ። በአርባ ምንጭ ቆይታው ለኪነጥበብ ዝንባሌ ያላቸውን ወጣቶች በተለያየ መልኩ ይደግፍ እና ያበረታታ እንደነበር የሚነገርለት ኩራባቸውን በተመለከተ ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ የራሱን ገጠመኝ በማንሳት ". . . እንደ መኪና ሮዴታ ከነበርኩበት ግራ መጋ...