"52 አመት በሀኪምነት አገልግያለው" - ኘ/ር ማለደ ማሩ | Prof. Malede Maru | Season 2 Epis...የተግባር #ሐዋርያው #የኔታ ፕሮፌሰር ዶር ማለደ ማሩ ሽልማቴ ናቸው።
የተግባር #ሐዋርያው #የኔታ ፕሮፌሰር ዶር ማለደ ማሩ ሽልማቴ ናቸው። እቴጌ ጎንደርስ ሊቀ - ሊቃውንትሽን አክብረሽ #መለዮሽ የምታደርጊያቸው መቼ ይሆን??? ከዬት ልጀምር እንደምችል ሳላውቅ ወጠንኩት። እርእስ ለመስጠት ገና አቅሙን አላገኜሁም። እርእሱ እራሱን እስጊገልጥ ድረስ ልሰጥስጠው። እንዲህ …… እንዴት ሰነበታችሁ ውዶቼ - ክብረቶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ጫ ባለችው ደጓ ቪንተርቱር ከተማ በበዛ ጭመታ ላይ የሰነባበተችው እቴጌ ብዕሬ መጣች። ክረምት እና እኔ በፍልሚያ ነው። ጉንፋን ከመደበኛው በሽታ በላይ ነው። ለነገሩ አጤ ኮሮና አለምን ስንት እንዳስደገደገ እናውቃለን። ጉንፋን አይለቀኝም። ሲያሸኝ ኑሮ፤ ስንብቴም በዚህው ይሆን እንደሆን አላውቅም። "የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) #እፍታ በምልሰት - እንደ መግቢያ። ባለፈው ሳምንት ይህን የተከበሩ #የዬኔታን ፕሮፌሰር ዶር ማለደ ማሩን ከሃኪም ዩቱብ ቻናል ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አገኜሁት። ያዳመጥኩት በሲቃ ነበር። እኔ ፈሪ ስለሆንኩኝ ከምነገረው በስተቀር እከሌ፤ እከሊት ደህና ናቸው ወይ ብዬ ጠይቄ አላውቅም። በሥርዓትም መርዶ ተነግሮኝ አያውቅም። ትልቁ የህይወቴ ድክመት ተሎ መጽናናት አለመቻሌም ነው። እፈራለሁኝ። አይደለም ለሰው ልጅ ወፍ መንገድ ላይ ሞቶ ካገኜሁኝ አንስቼ ቀብሬ ነው የምሄደው። ሃዘን ከቤተሰብ ከኖረ እነ ታላቁ መምህር በላይ ሁሉ ውግዘት የጣሉብኝጊዜ ሁሉ ነበር። በሥጋው ለተለዬው ሳይሆን የሚታሰበው ለእኔ ነው። መገናኜቱ ላይ ቁጥብ እምሆነውም፦ መለዬትን ስለምፈራም ነው። ሃዘኔ ጥልቅ፤ ሳስተናግደውም በማምረር ነው። እንደዚህ ባልሆን በወደድኩኝ። ስለሆነም የኔታ ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ በህይ