ልጥፎች

#ሰላምን የሚገልጽ #ቃል #አልተፈጠረም።

ምስል
  #ሰላምን የሚገልጽ #ቃል #አልተፈጠረም ።      በዚህ አፍላ የሽግግር ጊዜ #የጋዛ እና #የእስራኤል #ተኩስ #አቁም ፣ #የእስረኛ እና #የታገቱ መከረኞች #ንጹህ #አየር #መተንፈስ እጅግ #ተስፋ #ሰጪ ጅምር ነው።    #ተመስገን ። መጨረሻውን ያሳምረው። #የጦርነት #መጨረሻም ፈጣሪ አምላክ፤ አላህ ያድርገው። አሜን።   «የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን መንገዱን ያዘጋጃል።»   (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) Sergute©Selassie 20.01.2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

መልካም #የእረፍት ጊዜ። አሜን።

ምስል
  መልካም #የእረፍት ጊዜ። አሜን።    «የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን መንገዱን ያዘጋጃል።» (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)     ለተከበሩት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለነበሩት ለክቡር ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ለቲማቸው #መልካሙን ሁሉ ይገጥማቸው ዘንድ እመኛለሁኝ። የአሜሪካ መንፈስ #ከግሎባል ዜጎች ጋር በአመዛኙ #የተሳሰረ ነው። ነገረ አሜሪካ #አያገባኝም ማለት የሚቻል አይመስለኝም።    #የሰብዕዊ #መብት #ረገጣ ፥ ወይንም #የሚዛን #መዛባት ሲገጥም #ሲከፋን #አቤት የምንለው ወደ እነሱ ነው። #ታላቅ #ታናሽ ሳይለዩ #በራቸው #ለሁላችንም #እኩል ክፍት ነው። ቲማቸውም #የከበሩ የሰውን ልጅን #የሚያከብሩ ነበሩ። #ያደምጣሉም ። ይህ መቼም #መሰጠት ፤ #መቀባትም ነው። እግዚአብሄር ጨምሮ #ይባርካቸው ። አሜን። #እግዚአብሄር #ይስጥልኝ ። #አመሰግናችኋለሁም ። #ብዕሬ #ሳትደመጥ ቀርታ #አታውቅም እና!    Sergute©Selassie 20.01.2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

ከአሜሪካ #ፈርስት በሚደንቅ ሁኔታ እግዚአብሄር #ይቅደም!

ምስል
  #የምዕት #ዕንቁ መሪ ፍፁም #ቅዱስ #ቃል ። #የፀደቀም ተነበበ።        ከአሜሪካ #ፈርስት በሚደንቅ ሁኔታ እግዚአብሄር #ይቅደም ! " #አሜሪካን ዳግም #ታላቅ ለማድረግ፦ በአሜሪካ #ህይወት ውስጥ፦ መልሰን የምናስገባው #ታላቁ ነገር፤ #እግዚአብሄር ነው።" (አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶናል ትራንፕ።)     ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ። ይህ #የምዕት መሪ ቃል ፍፁም ቅዱስ፤ #የፀደቀም ቃለ ህይወት ነው - ለእኔ። የተባረከ የመሪነት መርህም፤ ቀናም ጎዳና ነው። ቃሉ ኪዳኑ ከፈጣሪ ጋር ነውና አቅሙን የአለም ንጉሥ ክርስቶስ ይስጥ። አሜን።   ለክቡርነታቸው ይህን ዕውን የሚያደርጉበት የህይወት ዘመን ይስጣቸው። አሜን። ይህ መሪ ቃል ከሞት በተደጋጋሚ ያተረፈ፤ ፈቅዶ እና ወዶ ለመረጠ ለቀባ ተደጋጋሚ የዕድል በር ለሰጠ አምላክ የቀረበ #የምስጋና #ስጦታ ነው። የመፈፀም አቅሙን፦ ክህሎቱን መዳህኒዓለም ይሰጥወት ዘንድ እንደ አንድ የግሎባሉ #ባተሌ ዜጋ በፍፁም ልቤ እመኛለሁ። ከቂም፤ ከበቀል የፀዳ መንፈሰ ደርጅቶ፦ መስመሩን አጥርቶ ፈጣሪ ይመራወትም ዘንድ እመኛለሁኝ።   ለእኔ እንደ ቃለ ምህዳን ነው ያዬሁት። ፍፃሜውን ያሳምረው ፈጣሪ። አሜን። በአንድም በሌላ የአለም አገሮች ሆኑ ዜጎች ከአሜሪካ ጋር ትስስር አላቸው እና። ስጋት፤ ጭንቀት፤ ፍርሃት የሰውን ልጅ በቁሙ ይፈትነዋል። በዚህ የአመራር ሽግግር ደስ ያላቸው እንደአሉ ሁሉ የፈሩም፦ የሰጉም ዜጎችም አገሮችም ይኖራሉና።   መሪነት #አጽናኝነት እንዲሆን ፈጣሪ ይርዳ። መሪነት #አረጋጊነት ይሆን ዘንድም አማኑኤል ይርዳ። አሜን። መሪነት ሰባዕዊነት እና ተፈጥሯዊነቴ ይሆን ዘንድ ከሞት ያተረፈ አምላክ ይ...

ከፈጣሪ አምላክ ጋር #እርቀ #ሰላም ማውረድ ለሁሉም ይበጃል። #ለፋኖይዝምም ሆነ #ለአብይዝምም።

ምስል
  ከፈጣሪ አምላክ ጋር #እርቀ #ሰላም ማውረድ ለሁሉም ይበጃል። #ለፋኖይዝምም ሆነ #ለአብይዝምም ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   እንዴት ሰነበታችሁልኝ ማህበረ ክብር። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ዘመነ ብርሃነ ልደት፤ ዘመነ አስተርዬ በአማራ ክልል በትላልቅ ከተሞች በሰላም መጠናቀቁን ሰማሁኝ። የአፍሪካ፤ የአለም፤ የኢትዮጵያም ርዕሰ መዲና በሆነችውበአዲስዬሜ እንዲሁ። በውነቱ ደስም ብሎኛል።    በኦሮምያ ክልል ክልትምትም የሚለው የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ዓውደ ዓመታት አሁን ከሆነ በአማራ ክልልም መፈጠሩ፦ #መስተጓጎሉ በብዙ አዝንበት የነበረ በኽረ ጉዳይ ነበር። ሰሞናቱ ተመስገን ነው።   እርግጥ ነው በፈታ ደይሊ ዜና እንዳዳመጥኩት አልፎ አልፎ #ጠሽ #ጧ እንደነበር አዳምጫለሁኝ። የሆነ ሆኖ ግን በመላ የአማራ ክልል እና በሌሎችም ክልሎች እግዚአብሄርን ያስከፋ መስተጓጎል ባለመድረሱ ተመስገን ነው።   ጎንደር #የሎዛ #ማርያም ቀጣይ ክብረ በዓል በ21 አለና ከበዓለ እመቤታችን በዓላት ጋርም ግብ ግብ እንዳይኖር፦ በአጽህኖት ለሚመለከታቸው #ለፋኖይዝም አለቆች እና #ለአብይዝም የመንግሥት ሠራዊት አባላት አሳስባለሁኝ።    ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ግብግብ ትርፋ መትነን ነው። ለማንም አይጠቅም። በውነቱ #መባረክን ፤ #መቀደስን ፤ #መመረቅን መፃረር የጤና አይመስለኝም። የሆነ ሆኖ በ ዕዓላቱ በአንፃራዊ ሰላም መጠናቀቃቸው፤ መልካም ነገር ነው። ደንግጬ ነበር በጦር ድሮን #ጥበቃ ይደረጋል፤ #እርምጃም ይወሰዳል ሲባል። ሦስቱም አካላት #ፋኖይዝም ፤ #አብይዝም ፤ #ሽመልዚም ትእግስቱን ሰጥቷቸው በዕላቱ ካለ ህውከት መጠናቀቃቸው መልካም ነው። የፈጣሪ አም...

Anchor ''መከላከያ ሰራዊቱ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ነው። በፖለቲከኞች የሚፈታውን ችግር እፈታዋለሁ ብሎ ከንቱ መ...

ምስል
እግዚአብሄር የሚመሰገነው ይህን የመሰለ፣ ሚዛናዊ፣ የጨመተ፣ የሰከነ ሰብዕና ኢትዮጵያን ስላልነሳት ነው። ሁልጊዜ ባደምጣቸው እማልጠግባቸው ብቁ። ምራቁን የዋጠ ሰብዕና የኢትዮጵያ ኦርጋኒክ ተፈጥሮ አይከብደውም። ለዚህም ነው ከእናታቸው በላይ ማንም እና ምንም በልጦባቸው ትልልፍ የማይታይባቸው። ቁጥብ የታረመ ዕይታቸው ይመስጠኛል። ሼርም አደርገዋለሁኝ። ይኑሩልን። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።

እምወድሽ ጎንደር /Emwedshi Gonder/Nuradiss Seid/Bamlak Getnet/Tewodros Samual/...

ምስል

Yabek Molla - Gondere Bezina (Ethiopian Music) - official release

ምስል

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ | Amoraw Kamora | Aschalew Fetene - ነገ ማታ

ምስል

የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ። በድጋሚ በ17.01.2025 የታተመ

ምስል
  እንኳን ወደ ቀንበጠ ብሎግ በሰላም መጡ። „ድሆች ግን ዳግመኛ በመኝታቸው ያስባሉ፣ ባለ ጠጎች ባይቀበሏቸው ግን ልምላሜ እንደሌለው እንደ ደረቅ እንጨት ይሆናሉ፤ ርጥበትም ከሌለ ዘንድ ሥር አይለመልምም፤ ሥርም ከሌለ ቅጠሉ አይለመልምም።“(መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ 26 ቁጥር 1) የ ዴሞክራሲ ጽ ንሰት ው ርጃ። ከሥርጉተ©ሥላሴ Seregute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 29.12.2019 ·          መ ቅድም። አምላክ አለቀሰ መርኽ አለቀሰ የቃልኪዳን ሰነድ ሰለተቦደሰ የህሊና ልኩ ስለተቀደደ። ·          እ ፍታ። በዚህ ጹሑፍ የፖለቲካ ድርጅት አፈጣጠርን የሥርዓት ግሽበትን እንመለከታለን። መግቢያ ላይ ያለው ቃለ ወንጌልም ያመሳጥረዋል። ጉዳዬ ሥር ከሌለው ፍሬ ሰብል ጥበቃ ተስፋው ሩቅ ስለመሆኑ ያስተረጉማል። ተስፋ መውደቅ ሲያምረው እንዲህም ይፈተናል። የምርጫ ቦርድ አዲሱን የብልጽግና (ፓርቲ?) ህጋዊ ዕውቅና እንደ ሰጠ፤ በቱማታ እንደ መዘገበው ከሰሞናቱ ጠቅሷል። በዚህ አያያዝ የዴሞክራሲ ችግኝ ማብቀያ ተብሎ የታሰበው  የመጀመሪያ የጽንስ ውርጃውን አሳይቶናል። በአብን ላይ ያለው እምቅ ጫናን ቆዬን ብለን ማለት ነው። እሱ እራሱን የቻለ የታመለ የአምክንዮ ሽፍጥ ስላለበት።   ግን የአገሬ ቅኔዎች እንዴት ናችሁ? ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ይህን የብልጽግና(ፓርቲ?) አመሰራረት የግድፈት አካሄድ በሚመለከት በፌስቡኬ ላይ አጫጭር ጹሑፎችን ሳቀርብ ሰነባብቻለሁኝ። አሁን ጫን ያለ የመርኽ ይፋዊ የ...