የካቲት 25/2006 ሲጠዬቅ ስለ #ባለድርብ #ህሊና ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን።
የካቲት 25/2006 ሲጠዬቅ ስለ #ባለድርብ #ህሊና ። #አገር እና የአገር ሕይወት ጌታ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን። ነገረ ጸጋዬ #ሚዛኔ ነው። ነገረ ጸጋዬ ተግባሩ እራሱ #የፊደል #ገበታ ነው። "አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድድሃለሁ።" (መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፩) ዛሬን በነጮቹ የካቲት 25ትን ዕለቱን ከመንበሩ ጉብ ብሎ ተደላድሎ ስናገኜው እምንጠይቀው ቁልፍ ጥያቄ አገርም- አህጉርም፤ ዜግነትም - እኛነትም፤ ዕውነትም - መኖርንም፤ ሃይማኖትን - ታሪክን፤ ትውፊትን - ትሩፋትን፤ ወግ - ባህል - ልማድን፤ ሥልጣኔን ያናገረ - ያወያዬ - #ያስጠሞነ - ያመሳጠረ፥ በእነሱ ልዩ እርካታ ከፍታም የመረመረ - #የተፈላሰመ ፤ ወቅትን ከትናንት እስከ ነገ የተረጎመ - የተነበዬ ያን ታላቅ #ቁምነገር ፤ የተግባር #አንቱ ፤ #ዓራት #ዓይናማ ሊቀ - ሊቃውንት ባለ ድርብ ህሊና ኢትዮጵያዊ ስለምን አሳጣህን ተብሎ ነው? ዕለቱን ሳስበው እንደ አገር አውራ - ታቦት የማዬውን የሁለመናዬን ቅኝት፤ የትውልድ የቤት ሥራዬን በማሰብ - በማስላትም ነው። መኖሬን ሳስበው መንፈሴ ያን ታላቅ ሰው እዘክረው ዘንድ በሕይወት እያለሁኝ በስደት አገሬ በኳሽ አይሏ በእምዬ ሲዊዘርላንድ ስለ ሥሙ፤ ስለተግባሩ፤ ስለ ሊቀ ሊቃውንትነቱ እናገር - እጽፍ - እመሰክር - #አውጅ ዘንድ አምላኬ ስለፈቀደልኝም በማመስገን ነው። በተለይ የጸጋዬ ድህረ ገጽ ስወጥን፤ ስጀምር ላገዙኝ ለተባበሩኝ ማህበረ ቅንነት እጅግ ከፍ ያለም ምስጋና አቀርባለሁኝ። ለምንጊዜውም አከብራቸዋለሁኝ። ቅንነታቸው ቁሞ አስተምሮኛል እና። ያ ጥንካሬዬ ጸሐዬ ሆኖ ነው የጸጋዬ ራዲዮን የጀመርኩት። ብርታቶቼ ግሉኮሶቼ ከሲዊዝ፤ ከአውስትራልያ እና ከአገረ አሜሪካ ...