ልጥፎች

የእቴጌ ጎንደር #ትናንት ይጠራ! ናልኝ አጤ ትናንት የእኔ ሸበላ በመሸቢያ! Bitte kommen Sie in da...

ምስል

ራህብን ማስደንገጥ፤ ራህብ ዞግ የለውም። ለራህብ ካቴና መለገስ አይገባም።

  ራህብን ማስደንገጥ፤ ራህብ ዞግ የለውም። ለራህብ ካቴና መለገስ አይገባም።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የሃኪሞችን ጥያቄ ይሁን ማናቸውም ፍትኃዊ የህዝብ ጥያቄወችን የአብይዝም መንግሥት በጥንቃቄ፤ በእርጋታ እና በስክነት ሊይዘው የሚገባ ክስተት ነው። ሃኪሞች ጥያቄያቸው #ንጹሁ ነው። የተፎካካሪው ወይንም የተቃዋሚው ፖለቲካ የተግባር ራህብ ላይ ሲሆን የትኛውንም ጥያቄ ወደ ራሱ አስጠግቶ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ሃሳቡን ማንሸራሸሩ የማይቀር ነው። ታስታውሱ እንድሆነ የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴን እንደምን የተቃዋሚ ኃይሉ በዘመነ ህወሃት ሃንድል እንዳደረገው ይታወቃል። ከኦሮማራ ንቅናቄ በኋላ የድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ ረብ አለ፤ ከአብይዝም አገዛዝ በኋላ ጸጥ ረጭም አለ።   የሆነ ሆኖ ጥያቄ ያላቸው ወገኖች በችግራቸው ገፊነት አደባባይ ሲወጡ የአቅም ሻሞ አያስፈልግም። በመሃል የሚጎዱት #የተጎዱት ይሆናሉ። የሚጎዱት እንዳይጎዱ ደግሞ ሁሉም ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን አመጣጥኖ መከወን ይኖርበታል። አንድ ሃኪም #የሚሊዮኖች እስትንፋስ ነው። አንድ ሃኪም የሚሊዮኖች ቀጣይ ትውልድ #ሮልሞዴል ነው። አንድ ሃኪም የግሎባሉ ዓለም #ዜጋ ነው። አንድ ሃኪም #እናትም #ቤተሰብም አለው።   በሌላ በኩል አገር የሚመራ፤ አገር የሚያስተዳድር መንግስት ኮሽ ባለ ቁጥር ከመደንገጥ ጥያቄውን መርምሮ በአቅሙ ልክ መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል። የኢትዮጵያ ቅን እና ትጉህ ሃኪሞች መኖራቸው ችግር ውስጥ ስለመግባቱ ማመልከታቸው #ቂም ሊያዝባቸው፤ ከደረጃ #ሊይስተጓጎሉ ፤ ከቀጣይ የትምህርት ዕድል እስኮላር ሊታገዱ አይገባም። ቀጣዩ ይህ ሊሆን እንደሚችል ስለማስብ ነው ይህን የምጽፈው። በዞጋቸው እዬተነጠሉ የበቀል እርምጃ ሊወሰድባቸው አይገባም።   ተ...

ሳይንስ፤ ቴክኖሎጂ፤ ሥልጣኔ ናቸው። ሥልጣኔያቸው መሠረቱ ዕውነት እና ፋክት ነው። የሁለቱ ጋብቻ መኖርን ያቀላሉ።

ምስል
  ሳይንስ፤ ቴክኖሎጂ፤ ሥልጣኔ ናቸው። ሥልጣኔያቸው መሠረቱ ዕውነት እና ፋክት ነው። የሁለቱ ጋብቻ መኖርን ያቀላሉ።    "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እኔ እና እናንተ የምንገናኜው፤ ወደ ተሰደድንበት አገር የተጓጓዝነው ዘመኑ በፈቀደው የቴክኖሎጂ ሥጦታ ነው። አንድ አገር የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ፤ የትምህርት ተቋማትን የሚመሩ ማዕከላዊ ተቋማት መፍጠር፤ #ማሰልጠን ፤ የትውልድ ኃላፊነትን መወጣት ነው።   ዘመኑ በሚፈቅደው ልክ አጀንዳውን የእኔ ብሎ አትኩሮት መስጠትም ከሌሎች የመኖር ጉዳዮች በስተኋላ ቆዬኝ እስኪ ሳይሆን #በአቻነት እንዲጓዝ በመርህ ደረጃ መቀበል እና ወደ ተግባር ለመቀዬር የሚችሉትን ያህል መጣር #የሚጣጣል ፤ #የሚቃለል ፤ የሚወገዝ ሊሆን አይገባም።    ቀደምት አገር ግን በብዙ ነገር ኢትዮጵያ ኋላቀር ናት። ቢያንስ ዘመኑ በሰጠው ሥልጣኔ ጋር ተጣጥሞ ለመቀጠል መጣር የተገባ እርምጃ ነው። "ትምህርት ከድል በኋላ" በእኔ ዘመን የነበረ መፈክር ነው። ያ አልጠቀመም። 50 ዓመት በጨለማ ተዋጡ ነበር። የተሰደደው ትውልድ ግን ተምሮ እንሆ የትምህርት ሚር ለመሆን የበቃው በመማሩ ነው።   የዛን ጊዜው " #አትማሩ !" ብዙ ተስፋን አቀጭጮ እና ብዙ ዕድሎችን ለሙጦ ያለፈ ጎጂ ጉዳይ ነው። ዛሬም መደገሙ ያሳዝነኛል። ዛሬ ብዙ ሰው የከተማው ጉሮሮውን አርጥቦ የሚያድረው ማህበራዊ ሚዲያ በፈጠረለት #ትሩፋት ነው። ሥልጣኔ ሊገፋ አይገባም። ሥልጣኔን መፍቀድ እንደ ነውር ሊታይ አይገባም።    ልቅና እና በልዕልና የሚገኜው #በዕውቀት ነው። በመማር ነው። መሰልጠን በድካም ሳይሰለቹ በመትጋት የሚገኝ ትሩፋት ነው። በአብይዝም የመንግሥት ሥርዓት አፈፃ...

«የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ» BBC እንደ ዘገበው።

ምስል
  «የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ» BBC እንደ ዘገበው። በአብይዝም ይቅርታ ተጠይቆ ቢፈቱ ይሻለል። እርምጃው ብልህነት ያረጠበት ነው።   • https://www.bbc.com/amharic/articles/ckgqdkx3q32o «የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ»   ዶ/ር በርናባስ ሳሙኤል፣ ዮናታን ዳኛው፣ ዶ/ር ሀብታሙ ጌታቸው እና ዶ/ር መላኩ አልማው «የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው እንዲሁም ሦስት የአርባ ምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክተሮች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።   በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በአማራ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በቀናት ልዩነት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር አምስት ደርሷል። በአዲስ አበባ ከተማ ሌሎች አምስት የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ከሁለት ቀን እስር በኋላ ተለቅቀዋል።   የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ ድጋፉን የገለጸው የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዮናታን የታሰሩት ትናንት እሁድ ግንቦት 3/2017 ዓ.ም. እንደሆነ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መለስ ባታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በ2015 ዓ.ም. የተመሠረተውን ማኅበር የሚመሩት አቶ ዮናታን፤ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን በሚገኘው ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ መሆናቸውን አቶ መለሰ ገልጸዋል።   ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንደሚናገሩት አቶ ዮናታን እሁድ ከሰዓት የተያዙት ከመኖሪያ ቤታቸው ነው። "ከመያዙ በፊት ከትናንት ወዲያ [ቅዳሜ] የሚሠራበት ሆስፒታል አካባቢ እና በሚኖርበት ሰፈር [በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ] ለምርመራ እንደሚፈለግ ደውለው እንዳስታወቁት ነግሮኝ ነበር" የሚሉት አቶ መለስ፤...

ለፖለቲካ እስረኞች ማን ይሆን ጠበቃው? ስለምንስ ከአጀንዳ ውጪ ሆኑ???? #አልገባኝም።

  ለፖለቲካ እስረኞች ማን ይሆን ጠበቃው? ስለምንስ ከአጀንዳ ውጪ ሆኑ???? #አልገባኝም ።   "የቤትህቅናት በላኝ።"   በሁሉም ዘርፍ ያለውን ሁነት ስከታተለው የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ #ባለቤት #አጥቶ ነው እምመለከተው። ሁሉንም አቅጣጫ ዳስሱት። በዬእስር ቤቱ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች አጀንዳ የሚሆኑት በስሱ #የፍርድ #ቤት ቀጠሮ ሲኖራቸው ብቻ ነው። ይህ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል #ያልተለመደ ተመክሮ ነው።    ምክንያቱም የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ በዬትኛውም የትግል መስመር ያሉ ተቋማት፤ ንቅናቄወች፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ #በኽረ #አጀንዳ ሆኖ ነበር እማውቀው። ከእስር ይለቀቁ ዘንድ ህብረ ድምጹ #አህቲ ነበር። አሁን ግን ያ ህብረ ድምጽ የለም። ለምን ይሆን? ጥናት ስላላደረኩበት ያ ነው፤ ይሄ ነው ልል አልችልም። የሆነ ሆኖ ቢያንስ #የእስረኛ ቤተሰቦች እንግልት ላይ ስለመሆናቸው እንኳን ጉዳይ ሊሆን አለመቻሉ ይጨንቃል። ልጆች ያላቸው የፖለቲካ እስረኞችም አሉ። እነኝህ የእስረኛ ልጆች በትምህርት ገበታቸው ላይ ሊያሳድር የሚችለው የሥነ ልቦና ጫናም ከፍተኛ ነው።   በሌላ በኩል ሁሉም እናት አለው እና ይህቺ #እናት በልጇ ሃዘን እንደ ተጎሳቆለች የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና አንድ ነገር ብትሆን #እርግማን ይሆናል። ጭራሽ በአብይ ዘመን የእስረኛ ፍቺ ድፍንፍን ያለ ጉድ ነው የሆነው። ምንም ፍንጪ የለም። ቢያንስ ለቤተሰቦቻቸው ተስፋ ይሆን ዘንድ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ በግልም ሆነ በጋራ በሰባዊነቱ አጀንዳ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ። እርግጥ ነው #የቅን እና #ቀና ዜጎች #ስጋት በስሱም ቢሆን ትንሽ ይገባኛል። ልፋታቸው ሆነ ድካማቸው አድማጭ ማጣቱ፤ ከእስር የሚፈቱ ወገኖች ለህዝብ ድካም ዕውቅና ለ...

ጥንቃቄ በማስተዋል ቢሆን ……

  ጥንቃቄ በማስተዋል ቢሆን ……   ሃኪም ቀስብለው ተራምደው አያውቁም ችግርን ለመፍታት፤ ለህይወት ለመድረስ መጣደፍ ነው። ይህ ጸጋ ግሎባልም ነው። ጥሪያቸውም ነው። #ብሩኮች ።    "ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋል ይጸናል።" (ምሳሌ ምዕራፍ 24 ቁጥር ፫)   የኢትዮጵያ ሃኪሞች እጅግ ሐዋርያ ከሆነ ትዕግሥት በኋላ፤ ዕውነት የሆነ ጥያቄያቸውን ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ለአብይዝም መንግሥት አቅርበዋል። ጥያቄው ትክክለኛ እና ዕውነትን የገለጠ አቤቱታ ነው። ነገር ግን ጥያቄው አቅጣጫውን ስቶ ካለስኬት ተዳፍኖ ጉዳት አምራች እንዳይሆን ብርቱ ጥንቃቄን ይሻል።   "ጠቢብ ሰው ብርቱ ነው፤ ዓዋቂም ሰው ኃይሉን ያበዛል።"    ከሃኪምነት በላይ ምድራዊ ልቅና ያለው የለም የሚል እምነት አለኝ። ከእግዚአብሄር በታች ሩኃችን በህክምና ባለሙያወች መዳፍ ላይ ነውና። ለእነሱ በምንም ሁኔታ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልጋቸው። ለገኃዱ ዓለም የሩህ መሪ ናቸውና። አዛኞች፤ አጽናኞችም። አይደለም ስለራሳቸው ስለእኛም የቅዱስ ሩፋኤል ሥልጣን የተሰጣቸው ናቸው እና። ፀጋቸው ሰማያዊ። ጥሪያቸው ሰባዕዊ ነውና። በአቤቱታቸው ላይም የጋመ ነዲድ፤ ወይንም እንክርዳዳ መቀዬጥ የተገባ አይመስለኝም። ታቅዶም ይሁን ሳይታቀድ። አቤቱታቸው #ንጽህናውን የጠበቀ ድንግል ነውና ምንም ቅጥያ ፍላጎት ሊቀጣጠልበት አይገባም።    #ሦስት ጉዳዮችን ለማጣቀሻ አቀርባለሁኝ።   1) ታስታውሱ ከሆነ በአንድ ወቅት አዲስ አበባ ከተማ ላይ "ለመስቀሉ እሮጣለሁ" የሚል መንፈሳዊ መልዕክትን በቅድስና የያዘ መሰናዶ ተጀመረ። እራሳቸው ሠርተው አቅም #መፍጠር የተሳናቸው ፖለቲከኞች፤ ቲ ሸርቱን አሰርተው መሪው እኛ ነን የማለት ያህል ማህበራዊ ...